Get Mystery Box with random crypto!

ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መሰጠት ይጀምራል ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግ | ETHIO STUDENTS NEWS™

ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መሰጠት ይጀምራል

ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ በሚጀምረው አዲሱ ስርአተ ትምህርት ( ካሪኩለም) መሰረት ለ6ኛ ክፍል ተማሪዎች የማጠናቀቂያ ፈተና መውሰድ የሚጀምሩ ይሆናል።

ለሁሉም ክልሎች ትምህርት ቢሮዎች ከተላከ ፋይል እንደተረዳነው የ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ካላንደር የተገለጸ ሲሆን ከሰኔ 12 እስከ ሰኔ 16 /2015 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት ውስጥ ሁሉም ተማሪዎች የሁለተኛው መንፈቅ ዓመት ማጠቃለያ ፈተና ሲወስዱ 6ኛ ክፍል ተማሪዎች ደግሞ በልዩ ሁኔታ የ6ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና መውሰድ ይጀምራሉ።

በ2009 ዓ.ም የመጨረሻው የ10ኛ ልፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከተሰጠ እና የ10ኛ ክፍል መልቀቂይ ብሔራዊ ፈተና ( ማትሪክ) መሰጠት ካቆመና ተማሪዎች በክፍል ውጤታቸው ብቻ ማለፍ ከጀመሩ ወዲህ ጥቂት ጊዜያት በኋላ የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መሰጠት እንደሚጀምር ሲገለጽ ቆይቶ ነበር።

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

@ET_STUDENT_NEWS
@ET_STUDENT_NEWS