Get Mystery Box with random crypto!

ማዕድን ሚኒስቴር የወርቅ ቀበኛ ሌቦችን እንደማይታገሰ አስታወቀ !! ኢትዮጲያ ኳሏት ሃብቶች መካከ | ሰበር ዜና ET🇪🇹

ማዕድን ሚኒስቴር የወርቅ ቀበኛ ሌቦችን እንደማይታገሰ አስታወቀ !!

ኢትዮጲያ ኳሏት ሃብቶች መካከል አንዱ በሆነው የወርቅ ሀብት ላይ ከህጋዊ አግባብ ውጪ የተሰማሩ ግለሰቦችን እንደማይታገስ ማዕድን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡
የማዕድን ሚኒስትሩ እንጂነር ታከለ ኡማ በይፋዊ የፌስ ቡክ ትስስር ገፃው ላይ ባሰፈሩት ማሳሰቢያ መሰረተ ‹‹በባህላዊ የወርቅ ማዕድን ምርት ላይ የተሰማሩትን የአከባቢ ወጣቶችም ይሁን ከውጭ ዜጎች ጋር በመመሳጠር የሚደርጉ ህገ ወጦች እንቅስቃሴዎችን ሥርዓት የማስያዝ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል።›› ብለዋል፡፡

ከእዚህ በተጨማሪ ‹‹በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ( አሶሳ ) ፣ በኦሮሚያ ( ሻኪሶ) ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ( ቤሮ), እና በጋምቤላ ( ዲማ) ወረዳ በህጋዊ መንገድ እየሰሩ ያሉትን ኩባንያዎች እና ባህላዊ የወርቅ አምራቾችን እናበረታታለን ሲሉ›› ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

ከእዚህ ባለፈ የወርቅ ቀበኛ የሆኑ ወንጀለኞች በህግ እየተጠየቁ እንደሚገኙ የጠቆሙት ሚኒስትሩ ‹‹ህገ ወጦችን በህግ ቁጥጥር ስር እያዋልን እንገኛለን:: ፤እርምጃ መውሰዳችን ይቀጥላል! ›› ሲሉ ማስጠንቀቃቸውን ብስራት ከሚኒስትሩ ይፋዊ የፌስ ቡክ ገፅ ያገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA