Get Mystery Box with random crypto!

ከግብፅ የሚነሳ ጄት ወደ ጁባ ማቅናት ጀምሯል። ሁለት ቀናት በፊት Gulfstream G400 ከካይሮ | Esleman Abay የዓባይ ልጅ

ከግብፅ የሚነሳ ጄት ወደ ጁባ ማቅናት ጀምሯል። ሁለት ቀናት በፊት Gulfstream G400 ከካይሮ ተነስቶ ጁባ ገብቷል።
ጄቱ በመርህ ደረጃ የቢዝነስ አይሮፕላን ሲሆን እስከ 20 ተሳፋሪዎች መጫን ይችላል። በግለሰብ ደረጃ በጥቂቶች እጅ የገባ ነው። እንደ ኤለን መስክ እና ክ/ሮናልዶ የመሳሰሉ ታዋቂ ሰዎች የሚገዙት ዘመናዊ አይሮፕላን ነው።
ጄቱ የስለላ ቴክኖሎጂዎች ተገጥመውለት በተለያዩ ሀገራት ደህንነት ተቋማት አገልግሎት ላይ ይውላል። እነ አሜሪካ ሩሲያ እስራኤል ደህንነት ተቋማት ተጠቃሽ ናቸው።
ሩሲያ እና አሜሪካ በሶሪያ የተጠመዱ መሳሪያዎቻቸውን እና የአካባቢውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ለመቃኘት ይህንኑ ጄት ማሰማራታቸው በተለያዩ ጊዜያት የወጡ ዘገባዎች ያመላክታሉ። በዘገባዎቹ አንዱ ሌላኛውን(ዋሽንግተን እና ሞስኮ) ሲወቃቀሱ እንደነበር ተጠቅሷል።
Gulfstream G400 ለኤሌክትሮኒክስ ስለላ ELINT Electronic Intelligence ተልእኮዎች እንዲሁም ISR Intelligence Surveillance Reconnaissance የስለላ አገልግሎት ሲጠቀሙበት ይታወቃል።

ሌላው በአፍሪካ የአሜሪካ ጦር አፍሪካ ኮማንደር General Michale Lengley በምስራቅ አፍሪካ ሚስጥራዊ ጉብኝት ማድረጋቸው የታወቀው በዛሬው እለት ነው። ጀነራሉ ድብቅ ጉዟቸውን Aug 28፣ በጂቡቲ፣ ሶማሊያ እና በኬኒያ የ Manda bay የሚባለውን ወታደራዊ ቤዝ ጎብኝተው በ Aug31 መመለሳቸው ነው የተሰማው።

#HornOfAfrica
#የዓባይልጅ