Get Mystery Box with random crypto!

┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓ '. #ሀፍሲ '. ✎ፀሐፊ፦ መግፊራ ቢን | 📖//እስላሚክ⚡️⚡️TŰB€//📖

┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓
". #ሀፍሲ ".
✎ፀሐፊ፦ መግፊራ ቢንት ፉላን
┗─━─━─━∞◆∞━─━─━─┛
#እውነተኛ_ታሪክ

┯━━━━━▧▣▧━━━━━┯
#ክፍል_አራት ʕ❹ʔ
┷━━━━━▧▣▧━━━━━┷

ዝምታቸው ለደቂቃዎች ቀጥሏል ማን ምን ብሎ መጀመር እንዳለበት ግራ የተጋቡ ይመስላሉ፤ ሀፍሲ ግን በፀጥታው ውስጥ የሆነ ጥልቅ ሀሳብ ውስጥ እንዳለች ገፅታዋ ያስታውቃል፤ አይኖቿ እንባን አቅርረዋል፤ አንድ ቦታ የተተከለው አይኗ ሰው የናፈቀ ይመስላል፤ እኔ ምልሽ ሀኑ ሰውን ከመጠበቅ እና ከመለየት ግን ከባዱ የቱ ነው?
ሀኑ ጥያቄው ድንገት ስለሆነባት ምን ብላ መመለስ እንዳለባት እንኳን አላስተዋለችም
"እንዴ ሀፍሲ ዛሬ ደሞ ስለምን መለያየት ነው ምታወሪው?"
"እስቲ የጠየኩሽን መልሽልኝ እና ስለምን እንደማወራ ነግርሻለው" የሀፍሲ ንግግር ውስጥ ቁጣ ነበር.
ሀኑ ደነገጠች ሀፍሲን ለማረጋጋት እየሞከረች "ምን መሰለሽ እንደኔ አስተሳሰብ ከሆነ ሰዎችን ከመጠበቅ ይልቅ መለያየቱ የበለጠ ጥቅም አለው ምክንያቱም............... ሀፍሲ አቋረጠቻት "እኔኮ ላጣው አልፈልግም፤ እሱን ማጣትን ሳስብ ህይወት ትጨልምብኛለች፤ እሱን ማጣትን ሳስበው ውስጤን ማላውቀው ፍርሀት ይወርሰዋል፤ የኔ እንዲሆን ነው ምፈልገው፤ የኔ ብቻ በቃ የግሌ፤ አልጨረሰችም ተንሰቀሰቀች
ሀኑ ሀፍሲ በምታወራው ነገር ተደንቃለች፤ እንደዛ ጠንካራ የነበረችን ሴት ማነው እንደዚ እንክትክቷን ያወጣው? ስትል አሰበች ካቀረቀረችበት ቀና አደረገቻት "ለምን ታጪዋለሽ ሀፍሲ? ለምን ያንቺ አይሆንም? ንገሪኝ እስቲ የግልሽ እንዳታደርጊው የሚያደርግሽ ምክንያት ምንድነው?"
"አይሆንማ! አይፈልገኝም ኮ! እሱ ጊዜያዊ መዝናናትን ነው ሚያየው! ለሱ ሚታየው የኔ በሱ ፍቅር እንደዚ እራሴን ማጣቴ ሳይሆን የቤተሰቦቼ ክብር ነው! እሱ ሚያሳስበው ገንዘብ እንጂ ፍቅር አይደለም! ያፈቀርኩት ሰው እብድ ነው! ሀኑ ጊዜያዊ ደስታን የመረጠ እብድ! በቃ እኔን ለማፍቀር የማይችል መውደዱን ግን በግልፅ የሚነግረኝ፤ እኔጋ ሲሆን እንደፍቅረኛው ሚንከባከበኝ፤ ቤተሰቦቹ ጋር እና ቤተሰቦቼ ፊት ሲቀርብ ጭራሽ ትዳር የሚባል ነገር እንደማያስብ ደረቱን ነፍቶ የሚናገር ልበ ደንዳና፤ "ምፈልግሽ ለጊዜያዊ ለመዝናናት እንጂ ለቁምነገር አይደለም፤ አንቺ ማግባት ያለብሽ ሀብታም ወንድ ነው።" እያለ በግልፅ የሚነግረኝ እብድ! እኔጋ ሌላ ሌሎች ጋር ሌላ ነው። ለቅሶዋ ንግግሮ በልጦ አሸነፋት ሀኑ አረጋጋቻት "እስቲ ንገሪኝ ሀፍሲ ማነው እሱ? ለምንድነው እንደዚ ያፈቀርሽው? ስለፀባዩ ንገሪኝ? እንዳፈቀርሽው ሲያውቅ ነው የተቀየረው ወይስ መጀመርያም በዚ ፀባዩ ነው ያፈቀርሽው?" ሀናን ልበ ደንዳናዋን፣ ጠንካራዋን፣ ሀፍሲን እንደዚ በፍቅር ወጥመድ ያሸነፈውን ወንድ ለማወቅ በጣም ጓግታለች። በአባቷ ሞት ያልሸረሸረው ልቧን ለወንድ ልጅ ይህን ያህል በቀላሉ ትሰበራለች ብላ ለሰከንዶች አስባ አታውቅም። ቤተሰቦቿ ቢሰሙ ምን ይሉ ይሆን? እውነት የሀኑ የባህሪ ለውጥ ፍቅር ነው ቢባሉ አምነው ይቀበሉ ይሆን? ሀናን የሀፍሲን በፍቅር መውደቅን አልጠላችውም፤ ግን ማይሆን ሰው ይሆን ወይ ብላ ተጨንቃለች? በዚም ደግሞ እርግጠኛ ነች ይህንን ደሞ ከሀፍሲ አነጋገር ተረድታለች..............
ሀፍሲ እንባዋን ጠራርጋ ንግግሯን ቀጠለች።፤ "ይሀውልሽ ሀኑ ልጁ ማን እንደሆነ ስነግርሽ በጣም ልትገረሚ ትችይ ይሆናል። ግን አደራ ይህንን ሚስጥር ላንቺ ብቻ ነው የተናገርኩት ለማንም ትንፍሽ እንዳትይ! ደግም አንድ ሰው ስለእኔና ስለእሱ ታሪክ ቢሰማ ጭራሽ ላገኘው አይደለም ላየው የማልችልበት ቦታ እንደሚጠፋብኝ አስጠንቅቆ ብዙ ጊዜ ነግሮኛል፤ ታውቂያለሽ እኔ ደሞ አይደለም ሳላገኘው ሳላየው መዋል አልችልም።" ሀኑ በእሺታ አንገቷን ነቀነቀችላት
"ልጁ ሰሚር ነው የተከራያችን የእትዬ አስማ ልጅ" ሀኑ ደነገጠች በፍፁም ያላሰበችው ነገር ነበር። ሰሚር ቤተሰቡ ሙሉ በጣም የሚወዱት፣ የሚሳሱለት፣ እንደልጃቸው የሚቆጥሩት፤ ለሀፍሲም በጣም ጥሩ ወንድሟ እንደሆነ ሚያስቡት፤ በሀፍሲ በኩል በጣም የሚያምኑት፤ በተለይ እናቷ ሰሚር ካለ የትስ ብትሄድ? ምንም አትሆን!" እያሉ ሚመሰክሩለት የተከራያቸው ልጅ ነው። ሰሚር የማግባት ፍላጓት እንደሌለው ሙሉ የሀፍሲ ቤተሰብ ቢያውቅም ግን ምክንያቱ ግን ጠንክሮ ሰርቶ ያለ አባት ያሰደጉትን እናቱን ለመቀየር ትምህርቱን አቁሞ ስራ ላይ የሚንተፋተፋ ልጅ እንደሆነ ነው። ዛሬ ግን ሀኑ ከሀፍሲ የሰማችው ነገር አስገርሟታል፤ ሰሚርን በፍፁም ጊዜያዊ ደስታ ያሸንፈዋል ብላ ለአፍታም አስባም አታውቅም ነበር።
ሀፍሲ ንግግሯን ቀጥላለች "ያው ሀኑ እንደምታውቂው እኔና ሰሚር በመሀከላችን የ3 አመት እድሜ ልዩነት ቢኖረንም እሱ ብዙ ጊዜ ት/ት ያቋርጥ ስለነበር ለመጨረሻ ጊዜ እስካቋረጠበት 11ኛ ክፍል ድረስ አብረን ነበር የተማርነው። አብረን ስንማር ታድያ አንድም ቀን እሱም ያለእኔ፤ እኔም ያለሱ ት/ት ቤት አንሄድም ፤ የመጀመርያ ጊዜ ሁሉም ሚያውቀው ፍቅረኛሞች እንደሆንን ነበር፤ ለዚህም ሲባል ያው አንቺም እንደምታውቂው ሰሚር ጉልበተኛ ስለነበር ማንም ወንድ ደፍሮ እኔጋ አይጠጋም፤ እኔም በጣም ነበር ምኮራበት! ሰዎች ባልሽ ነው እያሉ ሲጠይቁኝ አዎ! ብዬ በድፍረት ነበር ምመልሰው። ግን ይህንን ነገር እሱ አያውቅም ነበር እኔም አዎ ምለው አይደለም ካልኩኝ ወንዶቹ ወደኔ ትኩረታቸውን ያደርጋሉ ብዬ በማሰብ ከነሱ ለመሸሽ ነው እሱ ግን ሚስትህ ናት ሲባል በጣም ይናደዳል የሆነ ቀን ምን ተፈጠረ መሰለሽ..........
ሀፍሲን እንደዚ ያስከፋት ተስፋ ያስቆረጣት ምን ተፈጥሮ ይሆን?..............

╬╬═════════════╬╬
#ክፍል_አምስት ʕ❺ʔ ይቀጥላል
╬╬═════════════╬╬

╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
@eslamik_tube
@eslamik_tube
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤