Get Mystery Box with random crypto!

ትናንት ደሴ ላይ በትክክል አገልግሎት ሲሰጡ ከነበሩ ባንኮች መካከል ዘምዘም፣ ሂጅራ፣ አዋሽና አባይ | 📖//እስላሚክ⚡️⚡️TŰB€//📖

ትናንት ደሴ ላይ በትክክል አገልግሎት ሲሰጡ ከነበሩ ባንኮች መካከል ዘምዘም፣ ሂጅራ፣ አዋሽና አባይ ባንኮች ይገኙበታል። ሌላው'ማ «ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ» እንዳላለን ሁሉ ተጫውቶብናል። በሰላሙ ቀን በየመንገዱ ላይ እያስቆሙ አካውንት ክፈቱ በማለት እንዳልተማጸኑን ሁላ ዛሬ ያስቀመጥነውን ስጡን ስንል ፊታቸውን አጠቆሩብን። እኔ'ማ በተለይ 5 ኪሎና 6 ኪሎ አካባቢ መንገድ ላይ እያስቆሙ አካውንት ያስከፈቱኝን ባንኮች ዝርዝር ሁላ ረስቸዋለሁ። ብቻ ግን «ፎቶ የለኝም!» ስላቸው «ሐጂ፣ ሐጂ፣ ሸሁ፣ ሸሁ፤ ሌላ ቀን ታመጣለህ!» ብለው መቶ መቶ ብር መውሰዳቸውን ነው የማስታውሰው። አንዳንዶቹ አሁን ባለሁበት ሰፈር ጭራሽ ቅርንጫፍም የላቸው። ከሁሉም ጋር የሰጠሁትን መቶ ብር አውጥቼ አንድ ባንክ ላይ ባጠራቅመው ዘይት ይገዛልኝ ነበር'ኮ¡

ለማንኛውም ሰውን ስትፈልጉ ብቻ ሳይሆን ሰውም ሲፈልጋችሁ በቃላችሁ እየተገኛችሁ!