Get Mystery Box with random crypto!

በፌዴራል ፖሊስ የእውቅናና ምስጋና ምርሀ ግብር ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ያስተላለፉት መ | Ethio Smart market

በፌዴራል ፖሊስ የእውቅናና ምስጋና ምርሀ ግብር ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ያስተላለፉት መልዕክት ዋና ዋና ነጥቦች

የእኛ አላማ ለእውነት የሚሰሩ፣ በእውቀት የሚመሩ ፣ በስነ ምግባር የዳበሩ፣
ሙያቸውን የሚያከብሩ ፣ ለህዝብ የሚኖሩ ፖሊሶችን ለኢትዮጵያ ማበርከት ነው፤

ሰዎች ሁሉ ፀጥ ረጭ ባለው ሌሊት በሰላም ተኝተዋል ምክንያቱም የማይተኙ ሰላም ጠባቂዎች ያለዕንቅልፍ ስለሚያድሩ ነው ይባላል ለዚህ ደግሞ ግንባር ቀደሙ የፌደራል ፖሊስ ነው፤

ሰላም እፈልጋለሁ ችግር የሚመጣ ከሆነ ግን በእኔ ዘመን እንዲመጣ እፈልጋለሁ፤ ምክንያቱም የእኔ ልጆች በሰላም እንዲኖሩ ስለምፈልግ የሚባለው አባባል በትክክል የሚሰራው ለኢትዮጵያ ፖሊስ ነው፤

የኢትዮጵያ ፖሊስ በጎችን ከተኩላዎች ለመጠበቅ 24 ሰአት የሚሰራ ሃይል ነው፤ ብዙ ተኩላዎች ሲጮሁ ይሰማል፤ የጩኸቱ ትርጉም በጎችን እንደፈለግነው እንብላ ተዉን ነው፤ ፖሊሶች ከተኩላዎች ምስጋና አይገኝምና ስራችሁን አጠናክራችሁ እንደትቀጥሉ እላለሁ ፤ ኢትዮጵያ አትፈርስም፤ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚፈልጉ ሃይሎች ይፈርሳሉ፤

ኢትዮጵያ ህልውናዋና ሉአላዊነቷ ለአደጋ በተጋለጠ ጊዜ ሁሉ ፖሊስ ግንባር ቀደም ተሰላፊ ነውና ክብር ይገባዋል፤ እናንተ የሰላም ዘቦች የብርሃን ጥቅም የሚታወቀው ጨለማ በሚሆበን ወቅት እንደ ሆነ ሁሉ የህግ አስከባሪዎች ሚና የሚታየውም ሰላምና ደህንነታችን አደጋ ሲወድቅ ነው፤

የሰላምን ዋጋ ብንገነዘብ ላፍታም ቢሆን ወደ ግጭት አናመራም ሰዎች ወደ መከራ ወደ ግጭት ሲገቡ የሰላም አስፈላጊነትን የሚገነዘቡ ቢሆንም የሰላም ዋጋ የረከሰ በመሆኑ ለእናንተ ሚናና ጥረት እምብዛም ክብር ያልሰጠን ቢሆንም ተኝተን የምናድረው ፣ አርሰን የምንበላው፣ ሀገራችን ለማበልፀግ የምንጥረው እናንተን ተማምነን ነው፤

በፖሊሶች የከሸፉ ወንጀሎችን ሳይሆን ከፖሊስ ዕይታ ያመለጡ ወንጀሎችን አግዝፎ የሚመለከት ባህል አለን፤ በየዘመናቱ፣ በየጊዜያቱና ቀናቱ ፖሊስ ለእኛ የማይነግረንን ብዙ ወንጆሎችን ያከሽፋል፤ ነገር ግን ያከሸፈውን የለፋበትንና መሰዋዕትነት የከፈለበትን ሳይሆን አልፎ አልፎ ከፒሊስ ዕይታ ያመለጠውን አብዝተን እንናገራለን፤

ፀጥታና ሰላማችንን ለማረጋጋጥ ሲዋደቁ ያላከበርናቸውን ፖሊሶች ወንጀል ሲፈፀምብን ጣታችን ልንቀስርባቸውና ልንወቅሳቸው አይገባም፤ ኢትዮጵያ በእጅጉ ለሚያገለግሏት ፖሊሶች በቂ ደሞዝ መክፈል ባትችልም እንኳን ማክበር መለማመድ ይኖርባታል፤

ኢትዮጵያ ከፍተኛ ዋጋ የከፈለችላቸው ያስተማረቻቸው ከምንም ወደ ገዘፈ ማንነት ያደረሰቻቸው ግለሰቦች የፖሊስን ግማሽ ዋጋ ቢከፍሉ ኢትዮጵያችን ምን ልትሆን እንደምትችል ላፍታ እንድታሰቡ እጠይቃለሁ።

@Esat_tv1
@Esat_tv1