Get Mystery Box with random crypto!

የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ያስተላለፈው መልዕክት 1ኛ.በከተማችን የሚገኘው የጸጥታ መዋቅር የሀገ | ኢሳት(ትኩስ ትኩስ ዜናዎች)

የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ያስተላለፈው መልዕክት
1ኛ.በከተማችን የሚገኘው የጸጥታ መዋቅር የሀገር መከላከያ ሰራዊት
በመሆኑ የከተማችን ህዝብ ተረጋግቶ መደበኛ ህይወቱን እንዲመራ እንጠይቃለን

2ኛ. የሸዋሮቢትና አካባቢውን ህዝብ ትጥቅ ለማስፈታት ታስቧል በሚል የሚወራው ወሬ መሰረተ ቢስ በመሆኑ ህብረተሰቡ እንዲረጋጋ ለህዝባችን ማሳሰብ እንፈልጋለን

3ኛ. የከተማችንን ሰላምና ደህንነት እንዲሁም የህዝቡን እንቅስቃሴ የሚያውክ ማንኛውንም እንቅስቃሴ ባለማድረግ ባለመተባበር ህዝባችንን
ከጥፋት እንከላከል ሲል የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ጊዜያዊ ኮማንድ ፓስት መልእክቱን አስተላልፏል።
የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር
ሚያዝያ 25/2015 ዓ.ም
=======≠========
ለተጨማሪ መረጃዎች ቻናላችንን join ያድርጉ፣መረጃ ለሚፈልጉ ለሌሎች ጋብዙ
@esatchannal