Get Mystery Box with random crypto!

'በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለተፈታኞች ፍተሻ ሲደረግ የነበረው ብዙ ተማሪዎች ድልድዩ ላይ እንዲሰለፉ እና | 🌱መርጌታ መንግስቱ የባህል መዳኒት ቀማሚ 🌿

"በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለተፈታኞች ፍተሻ ሲደረግ የነበረው ብዙ ተማሪዎች ድልድዩ ላይ እንዲሰለፉ እና እንዲቆሙ ተደርገው ነው።" - የአይን እማኞች

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ኢንትራስ ፈተና የሚፈተኑ ተማሪዎች ዛሬ ጠዋት ከዋናው ግቢ ወደ ቴክኖ ኢንስቲትዩት ግቢ የሚያሻግረው ድልድይ ላይ እንዳሉ ነበር ፍተሻ ሲደረግላቸው የነበረው። ተማሪዎቹን ሌላ ቦታ ላይ ፈትሸው ማሻገር ሲገባቸው ድልድዩ ላይ አስቁመው መፈተሻቸው ነው ከአይን እማኞች የተሰማው።

"ዩኒቨርስቲው ከሚገባው በላይ ተማሪዎች ድልድዩ ላይ ስለወጡ አደጋ መድረሱን እንደ ምክንያት መግለፁ ተገቢ አይደለም የዩኒቨርስቲው ህንፃ አስተዳደር አካላት ድልድዩ የሚችለዉን የጭነት መጠን ከግምት በማስገባት የጥንቃቄ እርምጃዎች መውሰድ ነበረባቸዉ" ሲሉ በአከባቢው የነበሩ የአይን እማኞች እና የተማሪ ወላጆች ገልፀዋል።

በአደጋው የተደናገጡ በሺዎች የሚቆጠሩ የከተማው ህዝብ፣ ወላጆች፣ ተማሪዎች በሀዋሳ መንገዶች ላይ ሁኔታውን በጭንቀት እና ሀዘን ውስጥ ሆነው ሲከታተሉ ውለዋል።

@Esat_tv9
@Esat_tv9