ያለአግባብ ከተወሰደው ብር 96 ነጥብ 3 በመቶው ተመልሷል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባሳለፍነው መጋቢት ወር ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ ባጋጠመ ችግር ምክንያት 801 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ያለአግባብ መወሰዱን ባንኩ አስታውሷል፡፡ ከዚሁ የገንዘብ መጠንም እስከ አሁን 96 ነጥብ 3 በመቶ (771 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር) ተመላሽ መደረጉን የባንኩ መረጃ አመላክቷል፡፡ ቀሪውን ያለአግባብ የተወሰደ ብር የማስመለስ ሥራም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው የተመላከተው፡፡ @Esat_tv1 @Esat_tv1 39.5K views14:40