Get Mystery Box with random crypto!

ዱባይ በጎርፍ ተጥለቀለቀች በዱባይ ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መጠን ነፋስ የቀላቀለ ከባድ ዝ | ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

ዱባይ በጎርፍ ተጥለቀለቀች

በዱባይ ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መጠን ነፋስ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ መዝነቡን ተከትሎ ከተማዋ በጎርፍ ተጥለቅልቃለች።

ጎርፉን ተከትሎ የዱባይ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያን ጨምሮ የከተማዋ ዋና ዋና ጎዳናዎች ከባድ ጎርፍ እያስተናገዱ መሆኑ ተገልጿል።

በተለይም ከዚህ ቀደም በርከታ በረራዎችን ሲያስተናግድ በነበረው የዱባይ አየር መንገድ በረራዎች ተስተጓጉለዋል።

ነፋስ የቀላቀለው ከባድ ዝናብ በኦማን ተከስቶ 18 ሰዎች ህይወታቸው ካለፈ በኋላ አሁን ደግሞ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና በባህሬን ጉዳት እያስከተለ እንደሚገኝ የአልጀዚራ ዘገባ ያመለክታል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1