Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለአግባብ ተወስዶ ከነበረው ገንዘብ 95 በመቶውን ማስመለስ መቻሉን አስታወ | ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለአግባብ ተወስዶ ከነበረው ገንዘብ 95 በመቶውን ማስመለስ መቻሉን አስታወቀ

የኢትዯጵያ ንግድ ባንክ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም ከተከሰተው የሲስተም ችግር ጋር በተገናኘ ያለአግባብ ተወስዶ ከነበረው ገንዘብ 95 በመቶ የሚሆነውን ማስመለሱን አስታውቋል።ባንኩ ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ በተጠቀሰው ዕለት በተፈጠረ ችግር ምክንያት ብር 801 ሚሊዮን 417 ሺህ 747.81 ያለአግባብ ተወስዶ እንደ ነበር መገለፁ ይታወሳል።

ከተወሰደው ገንዘብ 762 ሚሊዮን 941 ሺህ 341 ብር ማስመለስ መቻሉን ባንኩ በማኅበራዊ ትስስር ገፁ ባወጣው መረጃ አስታውቋል።ይህም መሰብሰብ ከነበረበት ገንዘብ ውስጥ 95 በመቶ የሚሸፍን ሲሆን ቀሪውን 38 ሚሊዮን 474 ሺህ 938 ብር የማስመለስ ስራ እንደሚቀጥልም ባንኩ ገልጿል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1