Get Mystery Box with random crypto!

የኢድ አል ፈጥር በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር ዝግጅት ተጠናቅቋል የፀጥታና ደኅንነ | ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

የኢድ አል ፈጥር በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር ዝግጅት ተጠናቅቋል

የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል

ሕዝበ ሙስሊሙ የኢድ አል ፈጥር በዓልን ያለምን የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲያከብር በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱም ከተማ አስተዳደሮች የጋራ ግብረ ኃይሉ ከወዲሁ ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ተግባር በመግባት ተልዕኮውን በተገቢው እየተወጣ እንደሚገኝ አስታወቀ።

የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል የኢድ አል ፈጥር በዓልን አስመልክቶ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፏል፡፡

በመልእክቱም፤ ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ያለምን የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲያከብር የጋራ ግብረ ኃይሉ ከወዲሁ ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ተግባር መግባቱን አስታውቋል፡፡

ሰላም ወዳዱ የሀገራችን ሕዝብም ለሰላምና ደኅንነት እንቅፋት የሆኑ ነገሮችን ለማስወገድ በሚካሄደው የፀጥታ ማስከበር ሥራ ውስጥ በባለቤትነት እያደረገ ያለውን ተሳትፎ የበለጠ አጠናክሮ እንዲቀጥል የጋራ ግብረ ኃይሉ አሳስቧል፡፡

ማህበረሰቡ የአካባቢውን ሰላምና ደኅንነት የሚያደፈርሱ አጠራጣሪ ነገሮችን ሲመለከት ለፀጥታ አካላት ጥቆማ በመስጠትና አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ ከጋራ ግብረ-ኃይሉ ጎን በመሆን የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣውም ግብረ-ኃይሉ ጥሪውን አቅርቧል።

ለመላው የዕምነቱ ተከታዮች እንኳን ለ1445ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ያለው የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል፤ በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር እና የአብሮነት እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልጿል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1