Get Mystery Box with random crypto!

የፀሐይ ግርዶሹ በርካታ የአሜሪካ ከተሞችን በእኩለ ቀን ማጨለሙ ተነገረ የፀሐይ ግርዶሹ በርካታ | ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

የፀሐይ ግርዶሹ በርካታ የአሜሪካ ከተሞችን በእኩለ ቀን ማጨለሙ ተነገረ

የፀሐይ ግርዶሹ በርካታ የአሜሪካ ከተሞችን በእኩለ ቀን ሙሉ በሙሉ እንዳጨለማቸው ተገልጿል፡፡

ሙሉ የጸሐይ ግርዶሹ ማዛትላን የተባለችውን የሜክሲኮ ከተማ ጨለማ አልብሷት ከለፈ በኃላ ወደ ዳላስ፣ ቴክሳስ እና ሌሎች የአሜሪካ ግዛቶች ተሸጋግሯል፡፡

በአንዳንድ የአሜሪካ ግዛቶች የጸሐይ ግርዶሹ እስከ 4 ደቂቃ መቆየቱም ተጠቁሟል፡፡

የጸሐይ ግርዶሹ በሚቀጥሉት ሰዓታት ወደ ሰሜን አሜሪካ ሰሜናዊ እና ምስራቃዊ ክፍሎች እንደሚዞርም ተመላክቷል፡፡

በሰሜን አሜሪካ ክስተቱን ለማየት በ10 ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች አደባባይ መውጣታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ክስተቱን በልዩ ሁኔታ እየተከታተለ የሚገኘው የአሜሪካ የጠፈር ምርምር ተቋም (ናሳ) ያለ ጸሐይ መነጽር ግርዶሹን ለማየት መሞከር እጅግ የዓይን ብርሃንን እስከማሳጣት የሚደርስ ችግር ሊያመጣ እንደሚችል በማስገንዘብ ላይ መሆኑም ተነግሯል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1