Get Mystery Box with random crypto!

ጠንካራ የግል ዳታ ጥበቃ ስርዓት ለመፍጠር ያስችላል የተባለ አዋጅ ፀደቀ በምክር ቤቱ የሰው ሀብ | ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

ጠንካራ የግል ዳታ ጥበቃ ስርዓት ለመፍጠር ያስችላል የተባለ አዋጅ ፀደቀ

በምክር ቤቱ የሰው ሀብት ልማት፣ ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አዋጁን አስመልክቶ እንደገለጸው÷ አዋጁ የግል ዳታ ጥበቃ ተቆጣጣሪ ተቋምን በመሰየም ጠንካራ የግል ዳታ ጥበቃ ስርዓት እንዲፈጠር ለማድረግ ወሳኝ ነው፡፡

የግል ዳታን ማሰባሰብ አስፈላጊ እየሆነ መምጣቱ እና በዲጂታል አገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ውስጥ የተሰበሰቡ የግል ዳታዎችን ማቀናበር ለማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት ያለው ሚና እያደገ በመምጣቱ አዋጁ እንደተዘጋጀ ተጠቁሟል፡፡

እንዲሁም ዳታ በሚሰበሰብበት እና በሚቀናበርበት ወቅት የግል ዳታ መብት ጥሰት እንዳይፈጠር ለመቆጣጥር የሚያስችል የግል ዳታ ጥበቃ አዋጅ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱም አዋጁ እንደተዘጋጀ ቋሚ ኮሚቴው ገልጿል፡፡

በተጨማሪም አዋጁ ከግል ዳታ ጋር የተያያዙ የመብት ጥሰቶች ሲከሰቱ ውጤታማ መፍትሔ ለመስጠት እንዲሁም ከዳታ ማቀናበር ስራ ጋር የተያያዘ አደጋን ለመቀነስ እና ሀላፊነት የሚሰማው ዳታ የማቀናበር ባህልን ለማሳደግ ወሳኝ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡

በኢትዮጵያ የግል ዳታ ላይ መብትን ዝርዝር የሚደነግግ ሕግ ባለመኖሩ እና የግል ዳታ ጥበቃ ተቆጣጣሪ ተቋም ባለመሰየሙ ጠንካራ የግል ዳታ ጥበቃ ስርዓት እንዳይፈጠር ማድረጉ ተነስቷል፡፡

በዚህም ዳታ በሚሰበሰብበት እና በሚቀናበርበት ወቅት የግል ዳታ መብት ጥሰት እንዳይፈጠር ለመቆጣጠር የሚያስችል አዋጅ ማውጣት አስፈልጓልም ነው የተባለው፡፡

በረቂቅ አዋጁ ላይ ከህዝብ ጋር እንዲሁም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት መካሄዱንም ቋሚ ኮሚቴው አስታውሷል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1