Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ነዳጅ አዳዮች ማህበር ፥ በአዲስ አበባ ከተማ የነዳጅ ዕጥረት መከሰቱንና ምክንያቱ ደግሞ | ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

የኢትዮጵያ ነዳጅ አዳዮች ማህበር ፥ በአዲስ አበባ ከተማ የነዳጅ ዕጥረት መከሰቱንና ምክንያቱ ደግሞ ጅቡቲ ላይ የዘነበ ከባድ ዝናብን ተከትሎ የመንገድ መቆራረጥ በመፈጠሩ መሆኑን ገልጿል

በተጨማሪም አስቀድሞም ከቦታዉ በበቂ ሁኔታ ነዳጅ እየተጫነ ባለመሆኑ መሆኑን አመልክቷል።

የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ደሳለኝ አበባየሁ ፥ እነዚህ ምክንያቶች ከነዳጅ አቅራቢ ኩባንያዎች የተነገራቸዉ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ችግሩ ለመስተካከል ጊዜ ይወስድ እንደሆን የተጠየቁት አቶ ደሳለኝ " ጉዳዩ ትልቅ ነዉ፤ እንደ ቀላል የሚታይ አይደለም ያሉን ሲሆን፤ በእርግጠኝነት መንግስትም ሌት ተቀን ርብርብ አድርጎ ነገሮችን ያስተካክላል ብለን ተስፋ እናደርጋለን " ብለዋል።

ከጅቡቲ ከሚመጣዉ በተጨማሪ ክምችት ውስጥ ነዳጅ አልነበረም ወይ ? የተባሉት አቶ ደሳለኝ፤ " ቤንዚን ከአዋሽ ፣ ከሱሉልታ ዲፖዎች ነው እየተጫነ ያለዉ ፤ አሁን ላይ ግን ከክምችት ለመጫን ያልፈለጉበት የራሳቸዉ ምክንያት ይኖራቸዋል ፤ መንግስትም ይህንን አይቶ መፍትሄ ይሰጣል ብለን እንጠብቃለን " ብለዋል።

" አንድ ያለን መንገድ የጅቡቲ ብቻ ነዉ " ብለው " መንገዱ የተበላሸ በመሆኑ ደግሞ የመቆራረጥ ችግር ያጋጥማል ከባድ ዝናብ ሲዘንብ ደግሞ ችግሩን ከፍ ያደርገዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

" እንደዚህ ዓይነት ችግሮች የሚያግጥሙ በመሆኑ ለተወሰነ ጊዜ በትዕግስት ማለፍ አስፈላጊ ነው " ብለዋል።

ከሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ ረጃጅም የነዳጅ ሰልፎች እየተስተዋሉ ይገኛል።

ይህ መረጃ የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@Esat_tv1
@Esat_tv1