Get Mystery Box with random crypto!

የካዕባ ልብስ ኪስዋ በአዲሱ አመት መግቢያ ላይ ተቀየረ ስለካዕባ ልብስ ኪስዋ ትንሽ መረጃዎችን ላ | 🇹🇷Dirilis Ertugrul Ethiopia🏹⚔🗡🇪🇹



የካዕባ ልብስ ኪስዋ በአዲሱ አመት መግቢያ ላይ ተቀየረ

ስለካዕባ ልብስ ኪስዋ ትንሽ መረጃዎችን ላካፍላችሁ


የካዕባ ልብስ ኪስዋ በየአመቱ የሚቀየር ሲሆን ከዚህ ቀደም በዙልሂጃ 9 ጠዋት ሀጃጆች ወደ አረፋ በተጓዙበት ወቅት ነበር የሚቀየረው:: አሁን ላይ ግን በአዲሱ አመት መግቢያ የመጀመሪያው ምሽት ሙሐረም 1 ላይ እንዲቀየር ተወስኗል::

የካእባ ልብስ ኪስዋ የአለማችን ውዱ ልብስ ነው::

የልብሱ ክብደት 850ኪ. ግ የሚመዝን ሲሆን አጠቃላይ የካዕባን ልብሱን ለማዘጋጀት የዘንድሮ ወጪው $6.5ሚሊዮን ዶላር ነው::

ይህ የካዕባ ልብስ በንጉስ አብዱልአዚዝ ኮምፕሌክስ የሚዘጋጅ ሲሆን ኪስዋውን ለማዘጋጀትም 200ባለሞያዎች ይሳተፉበታል::

በአለም ረጅሙ እና ኮምፒውተራይዝ የሆነው የስፌት ማሽን ይህን የካዕባን ልብስ ለማዘጋጀት አገልግሎት ላይ የሚውል ሲሆን የስፌት ማሽኑም
16 ሜትር የሚረዝም ነው::

የከዕባ ልብሱ ኪስዋ 670 ኪሎ የሚሆነው ጥቁር ሀር ሲሆን በሀሩ ላይ ለሚፃፈው የቁርኣን አንቀፆችም 120 ኪሎ 21ካራት ወርቅ እና 100ኪሎ ብር አገልግሎት ላይ ይውላል::

በልብሱ ላይ የሚፃፈው የቁርዓን አንቀፆችም በሰዎች እጅ በጥንቃቄ የሚጠለፍ ነው:

የዘንድሮ አመት 1444 የካእባ ልብስ ኪስዋ የመቀየር ስነ ስርዓትም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሙስሊሞች በቀጥታ የቴሌቭዢን ስርጭት ተከታትለውታል


@osmanethiopia
@osmanethiopia