Get Mystery Box with random crypto!

በግብጽ ፍቅረኛዬ ፈተና ወደቀች በሚል ትምህርት ቤቱን ያቃጠለዉ አፍቃሪ በቁጥጥር ስር ዋለ፤ ከፈተና | Ertalepost ኤርታሌ ፖስት

በግብጽ ፍቅረኛዬ ፈተና ወደቀች በሚል ትምህርት ቤቱን ያቃጠለዉ አፍቃሪ በቁጥጥር ስር ዋለ፤ ከፈተና መዉደቋ የሰርጋችንን ቀን ይገፋል ሲል ተናግሯል

በግብጽ ሜኑፊያ ግዛት ነዋሪ የሆነዉ የ21 ዓመት ወጣት ፍቅረኛዉ የነበረባትን የትምህርት ፈተና ማለፍ ባለመቻሏ ትምህርት ቤቱን በእሳት አጋይቷል፡፡የሀገሪቱ ጠቅላይ አቃቤ ህግ እንደገለጸው በእሳት አደጋዉ የሞተ ሆነ የተጎዳ ሰው የለም ብሏል፡፡

ግለሰቡ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን እጮኛው የትምህርት ቤቱን ፈተና መዉደቋ ክፍል እንድትደግም የሚያስገድዳት ሲሆን ይህ ደግሞ የሰርጋችንን ቀን ይገፋብናል ሲል ተናግሯል።ድርጊቱን ከፈጸመ በኃላ ከአካባቢዉ ተሰዉሮ የነበረ ሲሆን የዓይን እማኞች ለፖሊስ በሰጡት መረጃ በቁጥጥር ስር ዉሏል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Via ዳጉ ጆርናል

#Ertalepost

Telegram t.me/ertalepost
Twitter twitter.com/ErtaleP
Facebook www.facebook.com/Ertale-post-ኤርታሌ-ፖስት-108469121804711/
Instagram instagram.com/ertalepost
youtube youtube.com/channel/UCn5U0OZQ_SEOcLfmTjMlKng