Get Mystery Box with random crypto!

★ ደሀ ነኝ ብለህ ታስባለህ?? አብዛኛው ሰው እኔ ደሀ ነኝ ሲል ይሰማል ለመደሰትም ገንዘብ እስኪያ | «ሰሊም<=> ሚድያ»

★ ደሀ ነኝ ብለህ ታስባለህ??
አብዛኛው ሰው እኔ ደሀ ነኝ ሲል ይሰማል ለመደሰትም
ገንዘብ እስኪያገኝ ይጠብቃል!! አይገርምም ሀብታም
ገንዘብ ሲፈልግ በጣም ያስቃል ፡፡ ሁላችንም ሀብታም
መሆናችንን ብነግራችሁስ ምን ትላላችሁ ?
ለምሳሌ፡- አሁን ይህንን ፅሁፍ እያነበባችሁ
ነው !! ይህንን ፅሁፍ የምታነቡበትን አይን አንድ ሀብታም
በ 10 ሚሊየን ብር ሽጡልኝ ቢላችሁ ትሸጡለታላችሁ ??
በእርግጠኝነት አታደርጉትም ምክንያቱም <<አያዋጣማ>>
ከ10 ሚሊየን ብሩ ይልቅ አይናችን ይጠቅመናልና::
አያችሁ አሁን በ10 ሚሊየን ብር እንኳን የማይተመን
ውድ ሀብት አለን ማለት ነው፡፡ ችግሩ ይህንን ሀብት መጠቀም አለመጠቀማችን ነው ስለዚህ እነዚህን ሀብቶች
ስንጠቀም ሀብታም ነን ማለት ነው ስለዚህ ደሀ ነኝ ብለህ
አትዘን ገንዘብና እንቅልፍ በራሳቸው ጊዜ ይመጣሉ ካንተ
የሚጠበቀው መስራት ብቻ ስለዚህ ገንዘብ ማጣት
ደስታህን አያጠፋውም ምክንያቱም አንተ ሀብታም
ስለሆንክ ደስተኛ ሆነህ ኑር

@Eross_eross