Get Mystery Box with random crypto!

ነፃነትህን አትጣ! የማይመለከታቸው ሰዎች ስላንት ስላወቁ ከጉዳት ውጪ የምትጠቀመው ነገር የለ | ermi ye hawii.....✍

ነፃነትህን አትጣ!

የማይመለከታቸው ሰዎች ስላንት ስላወቁ ከጉዳት ውጪ የምትጠቀመው ነገር የለም ። በገዛ ፍቃድህ ነፃነትህን ማጣት ከፈለክ ሁሉ ነገርህን ግልፅልፅ ማድረግ ትችላለህ ። በነፃነት የእራስህን ህይወት ብቻህን ማጣጣም ከፈለክ ግን የግል ጉዳይህን በየቦታው ከማውራት ተቆጠብ ። ምናልባት የመናገርህ ምክንያት ምንያክል ደስተኛ እንደሆንክ ሰዎች እንዲያውቁልህ ሊሆን ይችላል ፤ ከእነርሱ የተሻለ ነገር እንደምታገኝ ለማሳወቅም ይሆናል ። ነገር ግን ዝምታቸው ካንተ በታች እንደማያደርጋቸው አስታውስ ። እንዳንተ ያደረጉትን ፣ ያሳለፉትን ነገር ሁሉ ካልተረኩ ካንተ እንደማይሻሉ ልታውቅ አትችልም ።

አዎ! ጀግናዬ..! ነፃነትህን አትጣ ፤ ዋጋውን አታጉድለ ። እያንዳንዱን ጉዳይህን መንገድ ላይ አታውጣው ፤ እወቁልኝ አታብዛ ። የማይመለከታቸውና ላንተ ህይወት መቃናት ምንም አስተዋፅኦ የማያደርጉ ሰዎች ስላንተ አዲስ ስራ መጀመር ብታሳውቃቸው ምን ታገኛለህ ? ምንም ፤ ነገር ግን ምናልባት ስራው እንዳሰብከው ባይሆንና ባይሳካልህ ሃፍረቱና ሰቀቀኑ መግቢያ ያሳጣሃል ። ስላንተ ህይወት ቅንጣት የማይገዳቸው ፣ ያንተ ደስታ ፣ ያንተ መረጋጋት ፣ ያንተ ወዳጅ ማፍራት ምናቸውም ያልሆኑ ሰዎች የፍቅር ህይወት መጀመርህን ቢያውቁ ምን ይጠቅምሃል ? ምንም ። ይልቅ በፈቃድህ የይሉኝታ ጥርስ ውስጥ ትገባለህ ፤ ነፃነትህን ታጣለህ ፤ ከእራስህ ደስታ በላይ የእነርሱን ወሬ ትፈራለህ ።

አዎ! ሁሉ ነገርህን ለማርከስ አትጣደፍ ። በሚስጥር የተያዘና በብዙዎች አፍ ያልገባ ነገር ቢበላሽም በቀላሉ ይታረማል ፤ ባይሳካም ሳይታወቅ ይቀራል ። ገሃድ መውጣት ያለበቻው ነገሮች በጊዜያቸው ገሃድ ይወጣሉ ። ያንተ ያለጊዜው አደባባይ ማውጣት ሌላ ጣጣ ይዞብህ እንደሚመጣ አትጠራጠር ። በግልህ ማጣጣም ያለብህን ነገር አጣጥም ፤ መሰረቱን ስትይዝና በጣም እርግጠኛ ስትሆን ብቻ በኩራት ማውራት ትጀምራለህ ። ከሰዎች ጫና መዳን ከፈለክ ለእራስህ ሚስጥረኛ ሁን ፤ ብትጠየቅም ጊዜውን ጠብቅ ፤ ብትገደድም ለምታገኘው ንፁ ደስታ ቅድሚያ ስጥ ።

አዎ! የምታሳውቀው እርግጠኛ ስትሆን ፣ ለምታምነውና ሊረዳህ ለሚችል ሰው ብቻ ነው ። ከሁሉም ቀዳሚው ከሁኔታው ጋር እራስህን ማቆራኘትና ማወዳጀት ነው ። ፍቅሬን እወቁልኝ አትበል ፤ ዝናዬን አክብሩልኝ አትበል ፤ ሃብቴን እዩልኝ አትበል ፤ ንብረቴን ቁጠሩልኝ አትበል ። "በለፈለፉ በአፍ ይጠፉ" ከሚለው ድንቅ አባባል ተማር ። በግል ጉዳይህ አትደራደር ፤ ለጊዜ ደስታህንም በሚስጥር አጣጥም ፤ ህይወትህን ለእራስህ ኑር ። በጊዜና በሰዓቱ ነገሮች በእራሳቸው ግልፅ እየሆኑ ይመጣሉ ።
═════════❁✿❁ ═════════
አንብባችሁ #ሼር አላደርግ ስትሉ #ብሞት እንኳን #የማትቀብሩኝ አይነት ስሜት ነው የሚሰማኝ #ልሙትላችሁ ሆሆ ፣ ለማንኛውም አሁንም #ሼር አድርጉልን የቴሌግራም ቻናላችንንም ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/ermiyee1