Get Mystery Box with random crypto!

Ermi sport & Tirapi

የቴሌግራም ቻናል አርማ ermisportfitness — Ermi sport & Tirapi E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ermisportfitness — Ermi sport & Tirapi
የሰርጥ አድራሻ: @ermisportfitness
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 278

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-05-08 12:21:32 ቦርጭን ለማጥፋት የሚጠቅም ምክሮች

፦ በሰዉነታችን ላይ የስብ መከማቸት የተለያዩ የጤና ችግሮች እንደሚያስከትሉ የሚታወቅ ነው ። ለምሳሌ
        ~ ለልብ ሕመም
        ~ ለስኳር ሕመም
        ~ ለደም ግፊት መጨመር
        ~ ለከፍተኛ ኮሌስትሮል
፦ በአብዛኛው ስብ የሚከማችበት ቦታ ሆድ አካባቢ ሲሆን ይህም በአማርኛ ቦርጭ ብለን የምንጠራው ነው ። ቦርጭን ሊያመጡ የሚችሉ ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው ።
     _ ሊተኙ ሲሉ መመገብ
     _ ሰአትን ጠብቆ አለመመገብ
     _ በሰዉነታችን የሚገኙ ሆርሞኖች ለዉጥ
     _ ጭንቀት
     _ ቅባት የበዛባቸው ምግቦችን መመገብ
     _ በተፈጥሮ የሚመጣ
             ፦ ቦርጭን ለማጥፋት
1)ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ አንድ ብርጭቆ ሎሚ ያለው ዉሃን መጠጣት
2) አርንጓዴ ሻይ መጠጣት ፦ በዉስጡ የያዘው ንጥረ ነገር ምክንያት አላስፈላጊ ስብን የማሶገድ አቅም እንዳለዉ ጥናቶች ያሳያሉ ።
3)ስብ የማቃለል ችሎታ ያላቸው ምግቦችን መመገብ እነዚህም እንደ ብሮክሊ ፤ ካሮት ፤ ጎመን ፤ ያሉ አትክልቶችን እንዲሁም ፖም ፤ ሀብሀብ ፤ ፓፓያ ያሉ ፍሬፍሬወችን ማዘዉተር
4) ጤናማ የሆኑ አመጋገብ እንዲኖርን ማድረግ የተመጣጠነ እና አትክልት የበዛበት ምግብ ባህል ማድረግ
5) በቀን ዉስጥ የምንጠጣው የዉሃ መጠን መጨመር
6)ቁርስን በሚገባ መመገብ ፦ ይህንን ማድረግ የርሀብ ስሜት እንዳይሰማን ማስታገሻ የሚሆኑ ተጨማሪ ስኳር እና ቅባት የበዛበት ምግብችን እንዳንመገብ ይረዳሉ
7) የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ ዋና መዋኘት ማዘዉተር በቀን ለ 30ደቂቃ ያህል የእግር መንገድ መህድ
            * እንቅልፍ አለማብዛት
            * ጭንቀት ማሶገድ
            * ......
https://t.me/ermisportfitness
https://t.me/ermisportfitness
63 viewsedited  09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 10:11:44 አንዲት ሴት በአንድ ወቅት እንዲህ ተብላ ተጠየቀች: አዘውትረሽ ወደ እግዚአብሔር በመጸለይሽ ምን "ትርፍ" ታገኛለሽ?
እሷም መለሰች፡- ብዙውን ጊዜ "ምንም አላገኘሁም", ይልቁንም "ነገሮችን አጣለሁ".
እናም ወደ እግዚአብሔር በመጸለይ ያጣችውን ሁሉ ጠቀሰች፡-

ኩራቴን አጣሁ።
ትዕቢቴን አጣሁ።
ስግብግብነት አጣሁ።
ፍላጎቴን አጣሁ።
"ቁጣዬን" አጣሁ።
ፍትወት አጣሁ።
የመዋሸት ደስታ አጣሁ።
የኃጢአት ጣዕም አጣሁ።
ትዕግሥት ማጣት፣ ተስፋ መቁረጥ፣ እና ተስፋ መቁረጥ ።

አንዳንድ ጊዜ የምንጸልየው አንድን ነገር ለማግኘት ሳይሆን በመንፈሳዊ እንድናድግ የማይፈቅዱልንን ነገሮች እንድናጣ ነው።

ጸሎት ያስተምራል፣ ያጠናክራል እናም ይፈውሳል።
ተገኘ ከፌስቡክ መንደር
https://t.me/ermisportfitness
https://t.me/ermisportfitness
59 views07:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 06:09:30 የማስታወስ ችሎታችንን ከፍ ሊያደርጉልን የሚችሉ የምግብ አይነቶች
------------
1. አሳ፦ አሳ በውስጥ ለአእምሮ ጤና ጠቃሚ የሆነውን ኦሜጋ 3 /omega 3/ እዛይት በመያዙ ለአእምሮ ጤና በተለይ ደሞ ለልጆች አእምሮ እድገት ጠቃሚ ነው። እንዲሁም በአሳ ውስጥ የሚገኘው ኦሜጋ 3 የአእምሯችንን ሴሎች ከጉዳት ይከላከላል።

ስለዚህም አሳን አዘውትረን በመመገብ የአእምሯችንን ጤንነት በመጠበቅ የማስታወስ ችሎታችን ከፍ እንዲል ያደርጋል።

2. ለውዝ፦ ለውዝ ለአእምሯችን ጤንነት ጠቃሚ በሆኑ ንጥረ ነገሮች የበለጸገ በመሆኑ የማስታወስ ችሎታችንን ከፍ ሊያደረጉልን ይችላሉ ከሚባሉ የምግብ አይነቶች ይመደባል።

በተጨማሪም ለውዝ በውስጡ ለአእምሮ ነርቭ ጤንነት ጠቃሚ የሚባሉትን እንደ ቪታሚን ሲ እና ቪታሚን B6 አይነት ንጥረ ነገሮች የበለጸገ በመሆኑም የማሳታወስ ችሎታችንን ከፍ ያደርጋል ተብሏል።

3. አቮካዶ፦ በአቮካዶ ውስጥ የሚገኙት የፋቲ አሲድ ቅባቶች አእምሯችን ንቁ እና ጤነኛ እንሆን በማድረግ ከፍ ያለ የማስታወስ ችሎታ እንዲኖረን ይረዳሉ።

4. ቀይ ሽንኩርት፦ ሻል ያለ የማስታወስ ችሎታ እንዲኖረን ከፈለግን በምጋባችን ውስጥ በርከት ያለ ሽንኩትር ጨምሮ መመገብ ይመከራል ምክንያቱ ደግሞ ሽንኩርት በውስጥ በያዘው አንቲኦክሲዳንት ንጥረነገር አእምሯችንን ከጉዳት ስለሚከላከል ነው።

5. አፕል፦ አፕል ወይም ፖም በውስጡ ኩዌርስቲን የተባለ አንቲ ኦክሲዳንት ንጥረ ነገር የበለጸገ በመሆኑ አእምሮን ከጉዳት በመከላከል የማስታወስ ችሎታችን እንዲጨምር ያደርጋል።

6. ቀይ ስር፦ ቀይ ስር በአይረን የበለጸገ በመሆኑ ደማችን በቂ ሄሞግሎቢን እንዲያገኝ በማድረግ አእምሯችን በቂ ኦክሲጅን አግኝቶ ጤነኛ እንዲሆን በማደረግ ለማስታወስ ችሎታችን መጨመር አይነተኛ ሚና አለው።

7. ማር፦ ማር በተፈጠሮ ሀይል ሰጪ ምግብ በመሆኑ አዘውትረን የምንወስድ ከሆነ የአእምሯችንን የማሳታወስ አቅም ከፍ እንዲል ያግዛል።

8. ውሃ፦ ውሃን አዘውትሮ መጠጣት ለአእምሯችን ጤንነት እና የማስታወስ ችሎታን ከፍ በማድረግ ረገድ ያለው ሚና ከፍተኛ በመሆኑን ውሃን አዘውተረን መጣጣት ይመከራል።
https://t.me/ermisportfitness
https://t.me/ermisportfitness
39 views03:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-12 00:29:34
27 views21:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-12 00:27:50 የራሱን ምናብ መፍጠር የማይችል ጭንቅላት የሌሎች ጭንቅላት ባሪያ ነው!
(እ.ብ.ይ.)

ሰው ኑሮው የሚለወጠው፣ ሃሳቡ የሚበለፅገው፣ አካባቢውን የሚያሳድገው፣ አኗኗሩን የሚያቀላጥፈው፣ ሕይወቱን የሚያዘምነው በቴክኖሎጂ ሳይሆን ቴክኖሎጂውን ሊፈጥርበት በቻለው ምናቡ ነው፡፡ ቴክኖሎጂን በበአዲስ ቴክኖሎጂ የሚተካው ምናብ ነው፡፡ ምናብ ጥቅም የሌለውን አጉል ባህል በሚጠቅም አዲስ ባህል የሚቀይረው ምናቡ በፈጠረው አስተሳሰብ ነው፡፡ የሰው ሕሊናዊ ስዕል አሁን ለደረሰበት ዕድገት መሠረቱ ነው፡፡ ሃሳብ ምን ያህል እንደሚያነሳ ያወቅነው ሰው ከሃሳቡ የተነሳ ጨረቃ ላይ መውጣቱን፣ ጠረፉን መመራመሩን፣ ሊደረስበት የማይቻል የማይመስለውን ደርሶበት ስናይ ነው፡፡ የዚህ ሁሉ ምንጭ ሃሳብ ነው፡፡ ሃሳብ አስተሳሰብን ይቀርፃል፤ አስተሳሰብ ደግሞ አመለካከትን ይወልዳል፡፡ አመለካከት ሊታይ የማይችለውን ማየት እንድንችል የሚያደርገንን ምናብ ይፈጥራል፡፡ ምናባዊ መሆን ማለት ሃሳብን ማስፋት ማለት ነው፡፡ ምናባዊ መሆን ማለት ራስን ጥሎ በአጉል ፍልስፍና ከራስ ጋር መፋታት አይደለም፡፡ እውነተኛ ምናብ የማይደረስበት ላይ መድረስ፣ ሊነካ የማይቻለውን መንካት ማለት ነው፡፡
የሰው ልጅ ዕውቀት ብቻውን የትም አያደርሰውም፡፡ ዕውቀት በአንድ ነገር ላይ የሚኖረን የተወሰነ ምክንያታዊ ሃሳብ ነው፡፡ ምናብ ግን ሰፊ ነው፡፡ ምናብ የመሬቱን ብቻ ሳይሆን የሰማዩን ሃሳብ በሃሳባችን የምንደርስበት የአእምሮ መነፅራችን ነው፡፡ ሰው ተኝቶ ብቻ ሳይሆን በእውኑም ሆኖ በምናቡ ብዙ ነገር ያስባል፡፡ ሰፊውን ዓለም ይቃኛል፡፡ ከየት ተነስቶ ወደየት እንደሚሄድ መድረሻውም ምን እንደሚመስል በአዕምሮው ያካልላል፡፡ ብዙ የሳይንስ ሰዎች ሳይንሳዊ ግኝታቸውን ዕውን ከማድረጋቸው በፊት ስለሚመረምሩት ጉዳይ ቀድመው በምናባቸው የአዕምሮ ንድፍ ያወጣሉ፤ በሃሳባቸው ይስላሉ፣ ቅርፅ ያወጣሉ፡፡ ዓለም እዚህ የስልጣኔ ርቅቀት ላይ የደረሰችው ምናባቸውን በተግባር በለወጡ ምናባዊ ሰዎች ነው፡፡ የማይታየውን የሚያዩ፣ የማይሰማውን የሚያዳምጡ፣ የማይታሰበውን የሚያስቡ ምናባዊ ሰዎች ናቸው፡፡ ብዙ ሰው ከሚያየው ርቀው ያልታየውን ለማየት የአዕምሯቸውን ቴሌስኮፕ የሚጠቀሙ ዓለምን በምናባቸው ለመረዳት የሚጥሩ አሳቢያን ናቸው፡፡

ታዋቂው ሳይንቲስት አልበርት አንስታይን፡-

‹‹ምናብ ከዕውቀት የበለጠ አስፈላጊ ነው፡፡ ዕውቀት ውስን ነው፡፡ ምናብ ግን ዓለሙን ሁሉ ያካልላል (Imagination is more important than knowledge. Knowledge is limited. Imagination encircles the world)፡፡›› ያለው ለዚህ ነው፡፡

አዎ ምናብ ሐገሩ ሰፊ ነው፡፡ ምናባዊ ሰው በኖረበት፣ ባደገበትና ሕብረተሰቡ በጋተው ሃሳብ ብቻ አይወሰንም፡፡ አልፎ ይሄዳል፡፡ የማይርስበት የዓለም ጥግ የለም፡፡ ምናብ የምታየውን ነገር ቅርፅ የምታሲዝበት፤ የምትሰማውን አዳምጠህ ትርጉሙን የምትፈታበት የረቀቀ ሃሳብ ነው፡፡ በሚታየው ውስጥ የማይታየውን ፍቺ መፈለግ ነው ምናባዊነት፡፡ ምናብ ያለው ሰው የሚታመነው ዓለሙ ባሰቀመጠለት ትርጉም ብቻ ሳይሆን በገዛ ሃሳቡ ከፍቺው በላይ ያለውን ሚስጥር በመፈለግ ነው እውነታውን የሚቀበለው፡፡ በሚሰማው ብቻ ጆሮውን አይዘጋም፤ ከሚሰማው በላይ ያለውን የተፈጥሮ ዝምታ እስከማዳመጥ ይደርሳል ምናባዊነት፡፡ የፀጥታውን ድምፅ መፈለግ ነው ምናባዊነት፡፡ ከሚታየው በላይ ማየት መቻል ነው የምናብ ሰው መሆን ማለት፡፡ አልፎ ማየት፣ ርቆ መስማት፤ አሻግሮ መመልከት፣ እንደነብይ ዘመናትን ቀድሞ መረዳት ነው ምናባዊነት፡፡ ምናባዊነት መሠረቱ ማሰብ ነው፡፡ በማሰቡ ሃይል እየተመራ ብዙ ሰው ያልደረሰበትን ይመረምራል፡፡

ምናብ ባይኖር ደራስያን አይኖሩም ነበር፡፡ የፊልም ሰዎች ያለምናብ የተለየ ትዕይንት አያሳዩንም፡፡ ምናብ የሌላቸው ደራሲዎች አዲስ ነገር አይፅፉም፡፡ ልብ ውልቅ ናቸው! የኖርንበትን እውነት ቀለም ቀብተው ከማቅረብ ውጪ የተለየ ያላየነውን አይተው ለማሳየት አይችሉም፡፡ ምናብ ባይኖር የሳይንስ ሰዎች ዓለምን እዚህ አያደርሷትም ነበር፡፡ ምናብ ባቡር ነው፤ ዓለምን በፍጥነት በመንታ የሃሳብ ድልድይ ይዞ የሚነጉድ፡፡ ይሆናል እና አይሆንምን በጀርባው አዝሎ ከድብቁ ዓለም ሚስጥሩን የሚተነትንና የሚመረምር ነው ምናብ ማለት፡፡

አንዳንድ ሰው ምናባዊ ነኝ ለማለት ከሰውነት ጎዳና ሲወጣ ይታያል፡፡ ምናባዊነት ራስን መዘንጋት አይደለም፡፡ ምናባዊነት በአዕምሮ መደንዘዝ፣ በሃሳብ መፍዘዝ አይደለም፡፡ ምናባዊነት በሱስ ጅረት መፍሰስ ሳይሆን በሃሳብ ባህር ውስጥ መቅዘፍ ነው፡፡ ምናባዊነት ራስን ይዞ ዓለምንም ማሳደግ ነው፡፡ ራስን ጥሎ አዲስ ነገር መፍጠር አይቻልም፡፡ አንዳንዶች ተፈላሰፍን ብለው ተልፈስፍሰው ይወድቃሉ፡፡ አዲስ ነገር አገኘን ብለው ራሳቸውን ይጥላሉ፡፡ የፍልስፍና ሀሁ ራስን አውቆ ራስን መጠበቅ ነው፤ ሲከተልም ዓለሙን መረዳት፤ ሲሰልስም የማይታየውን ማየት፣ ሲቀጥልም የማይደረስበት ላይ መድረስም ጭምር ነው፡፡

የሰው አዕምሮ ማሰብ እስከሚችለው ድረስ እንዲያስብና አዲስ ነገር መፍጠር እንዲችል ተደርጎ ነበር የተፈጠረው፡፡ ግና ግን ማሰቢያውን የተጠቀመ ጥቂት ነው፡፡ ምናብ የሌለው ሰው ግን የሌሎች ጭንቅላት ባሪያ ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሰው ጭንቅላቱ ሰርቶ እንዳይበላ አዕምሮውን የበይ ተመልካች ያደርገዋል፡፡ ከሌሎች ኮርጆና ቀድቶ መኖርን አንጂ አስቦ አዲስ ነገር መፍጠርን አያስተምረውም፡፡ ጭንቅላትን አጎንባሽ ባሪያ ማድረግ ራስን ማዋረድ ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው ለዓለም የሚያዋጠው የራሱ እሴት ከሌለው ከሞተው በምንም አይሻልም፡፡ በመኖርህ ለዓለም የምትጨምረው አዲስ ዕውቀት፣ ልዩ ሃሳብ ከሌለህ የመኖርህ ትርጉም ምንም ይሆናል፡፡

ቸር ምናብ!
ለወዳጆ ሼር ያርጉላቸው
https://t.me/ermisportfitness
https://t.me/ermisportfitness
https://t.me/ermisportfitness
28 views21:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 12:39:04 ከመጠን ያለፈ ውፍረት
በአፍሪካ ከመጠን ያለፈ ውፍረት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው
የዓለም ከመጠን ያለፈ ውፍረት  ፌደሬሽን (ኦቢሲቲ ፌዴሬሽን) አዲስ ባወጣው ሪፖርት በ2035 ከዓለም ሕዝብ መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆነው ወፍራም ወይም ከመጠን በላይ ወፍራም እንደሚሆን ተንብይዋል ፡፡

በመሆኑም  መንግሥታት እርምጃ እንዲወስዱ ፌዴሬሽኑ አሳስቧል።

አዲስ የወጣው ሪፖርት ከመጠን በላይ ውፍረት ሳብያ ከአራት ቢሊዮን የሚበልጡ ሰዎች ጉዳት እንደሚደርስባቸው እና በተለይ ችግሩ በልጆች ላይ በፍጥነት እየጨመረ እንደሆነ ይገልጻል ።

አነስተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው የአፍሪካ እና ኢሲያ አገራት  ከልክ ያለፈ ውፍረት ያላቸው ሰዎች ከፍተኛ ጭማሪ የሚታይባቸው አገራት እንደሚሆኑ  ሪፖርቱ ያመላክታል።

በመላው ዓለም በውፍረት ምክንያት ከፍተኛ ችግር ከሚገጥማቸው ቀዳሚ 10 አገራት መካከል 9ኙ በአፍሪካ እና በኢሲያ የሚገኙ አስተኛ ገቢ ያላቸው አገራት መሆናቸው በሪፖርቱ ተገልጿል።
ለችግሩ  መንስዔ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል በፋብሪካ የተቀነባበሩ ምግቦችን አዘውትሮ መመገብ ፣ የአካል እንቅስቃሴ ያለማድረግ ፣ የምግብ አቅርቦት እና ገበያ ፖሊስ ቁጥጥር ደካማ መሆን እንዲሁም ክብደትን መቆጣጠር እና የጤና ትምህርት ትኩረት አለማግኘት ይገኙበታል።
ቢቢሲ
https://t.me/ermisportfitness
https://t.me/ermisportfitness
33 views09:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-27 22:10:36 1."ባለ ትላልቅ አእምሮ ሰዎች በሃሳብ ላይ ይወያያሉ ፣ መካከለኞቹ በድርጊትና ሁኔታዎች ላይ ይወያያሉ ባለትናንሾች ግን ቁጭ ብለው ሰው ያማሉ ፡፡"
--ሪያኖር ሮዝቪልት

2.‹‹ መብረር ካልቻልክ ሩጥ ፡፡ መሮጥ ካልቻልክ ተራመድ ፡፡ መራመድ ካልቻልክ ዝግ ብለህም ቢሆን ሂድ ፡፡ ምንም ነገር ስታደርግ ወደፊት መሄድህን አታቋርጥ ፡፡››
--ማርቲን ሉተር

3.«ወደፊት የሚመጣውን ማንም አያውቅም ። ቁምነገሩ የሚመጣውን በልበሙሉነት ለመቀበል እንችል ዘንድ ዛሬን በብልሃትና በአግባቡ ተጠቅመን ፣ ነገን በናፍቆትና በደስታ መጠበቅ ነው ፡፡››
--ቻኒንግ ፓሎክ

4."እምነት አላማችንን የሚገነባበት መሰረት ነው ። የምንፈልገው ነገር ምንም ይሁን ምን እምነት ከሌለን ነዳጅ የሌለው መኪናን ለመንዳት እንደመሞከር ይሆንብናል ።"
--ናፖሊዮን ሂል

5.‹‹ ብርሃን ጨለማን ያሸንፋል እንጂ ጨለማ ጨለማን አይገፍም ፡፡ ጥላቻም በጥላቻ አይሸነፍም ፡፡ ያን ማድረግ የሚቻለው ፍቅር ብቻ ነው ፡፡ ››
--ማርቲን ሉተር

6."ወንዝ ድንጋይ ቦርቡሮ የሚገባው ሀይለኛ ስለሆነ ሳይሆን ያለማቋረጥ ስለሚፈስ ነው ፡፡"
--ጂም ዋትኪንስ

7."ህይወት በራሷ ፣ ምንም ያልተሳለባት ባዶ የሰዕል ሸራ ነች ። ስንፈልግ መከራን ፣ ስንፈልግ ሐሴትን የምንስልባት ባዶ ሸራ ።"
--ኦሾ

8."ጥንካሬና እድገት የሚመጡት (persistence) በተከታታይ ጥረትና ትግል ብቻ ነው ።"
--ናፖሊዮን ሂል

9."የሰው ልጅ ውድቀት አንደኛው መንስኤ የውሳኔ ማጣት ነው ። አንድ ሰው ምንም ያህል እምቅ እውቀት ቢኖረው ፤ ምንም ያህል የሚያሰደንቅ ሃሳቦችን ማመንጨት ቢችልም ውሳኔ መወሰን ካልቻለ ግን አቅሙ ሁሉ ከውስጡ አይወጣም ።"
--ናፖሊዮን ሂል

10." ለመጀመር ትልቅ መሆን አይጠበቅብህም ነገር ግን ትልቅ ለመሆን መጀመር አለብህ ፡፡"
--ዚግ ዚግላር

11."አንተ ጠንክረህ በዝምታ ስትሰራ ፣ ስኬትህ ጮኾ ይናገራል ፡፡ "
--ፍራንክ ኦሽን

12. ‹‹ እምነት ማለት ምንም እንኳን ሙሉው የሕይወት መሰላል ባይታይህም የመሠላሉን የመጀመሪያውን እርካብ መርገጥ ነው ፡፡ ››
--ማርቲን ሉተር

13." አንድ የደስታ በር ሲዘጋ ፣ ሌላ የደስታ በር ይከፈታል ። እኛ ግን አብዛኛውን ጊዜ ወደ ተዘጋው በር እንጂ ወደተከፈተልን አናይም ፡፡"
--ሔለን ኬለር
https://t.me/ermisportfitness
https://t.me/ermisportfitness
42 views19:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-19 07:28:28
42 views04:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 08:40:03
48 views05:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 08:35:39 አልማዝ የሚሆነው የድንጋይ ከሰል ነው !

አልማዝ በተፈጥሮ መንገድ እንዴት እንደሚሰራ ልንገራችሁ። አልማዝ የሚሰራው HPHT በሚባል Process ነው። HPHT ማለት High Pressure High Temperature ማለት ነው። አንድ አልማዝ አልማዝ ከመሆኑ በፊት አራት ደራጃዎችን ማለፍ ይኖርበታል።

አንደኛ ከምድር በታች ከ300 እስከ 600 ኪሎ ሜትር ዝቅ ብሎ መቀመጥ።

ሁለተኛ ከፍተኛ ሙቀት መታደል፣ ከ1200 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ቃጠሎ ውስጥ መቀመጥ።

ሶስተኛ ከፍተኛ ጭነት ማግኘት።

አራተኛ ለረዥም ጊዜ ውስጥ በነዚህ ሁኔታ ውስጥ መቆየት !

እንግዲህ አንድን የድንጋይ ከሰል ወስዳችሁ ከምድር በታች 600 ኪሎ ሜትር ብታወርዱት፣ 1200 ዲግሬ ሴንቲ ግሬድ ቃጠሎ ውስጥ ብታኖሩት፣ በከፍተኛ ፕሬዠር ውስጥ ብታስቀምጡት እና ለረዥም ጊዚያት በዚህ ሁኔታ ውስጥ ብትተዉት ከሱሉ አልማዝ ይሆናል ! ከሰሉ ወደ ዳይመንድ ይለወጣል።

አንዳንዶቻችሁ በህይወታችሁ ግራ ይገባችኋል፣ በጣም የሚወዳችሁ አምላካችሁ ከጓደኞቻችሁ በታች 600 ኪሎ ሜትር አውርዷችሁ ይሆናል።

በማይገባችሁ ፈተና 1200 degree centigrade ቃጠሎ ውስጥ አስቀምጧችሁ ፤ በማጣት፣ በመገለል፣ በመገፋት ለረዥም ጊዚያት እየፈተናችሁ "ምንድነው እየተካሄደ ያለው" ብላችሁ እስክትጠይቁ ድረስ ለአምስት አመት፣ ለአስር አመት ከሰው፣ ከወዳጅ፣ ከዘመድ፣ ከጓደኛ ዝቅ አድርጓችሁ ይሆናል። ....

"ምን ማለት ነው የሚወደኝ አምላክ ይሄን የሚፈቅደው?" ስትሉ ....

አልማዝ አድርጎ ሊሰራችሁ፣
ውብ አድርጎ፣ ሊሰራችሁ፣
የምታበሩ አድርጎ ሊያበጃችሁ፣
እንቁ፣ ዳይመንድ፣ አልማዝ ሊያደርጋችሁ ስላሰበ ነው !
አልማዝ ሰባት ባህሪዎች አሉት:-

አንደኛ ጠንካራ ነው። ወስዳችሁ በድንጋይ ቀጥቅጡት አይሰበርም። በሰይፍ ምቱት አይሰነጠቅም። በመጋዝ ገዝግዙት አይቆረጥም። በአልመዝ ግን ብረት ይቆረጣል፣ በአልማዝ ግን ሰይፍ ይቆረጣል። በአልማዝ ግን ድንጋይ ይፈርሳል። አልማዝ የሚቆረጠው በሌላ አልማዝ ነው።

ሁለተኛ የአልማዝ ባህሪ ልንገራችሁ። ከፍተኛ የማንጸባረቅ ባህሪ አለው። refractive index ይባላል። የተቀበለውን ብርሃን መልሶ የማብራት ባህሪ አለው። ያንጸባርቃል።

ሶስተኛው የአልማዝ ባህሪ የተቀበለውን የጸሐይ ብርሃን፣ ነጩን ብርሃን ወደ ተለያዩ በርካታ ቀለማት የመበተን ችሎታ አለው።

አራተኛ የአልማዝ ባህሪ ልንገራችሁ። እጅግ በጣም ንጹህ ነው። አልማዝ የሚታወቀው በነጹህነቱ ነው።

አምስተኛ የአልማዝ ባህሪ ልንገራችሁ። አልማዝ በእሳት አይቃጠልም። አንድ ቤት ውስጥ አልማዝ አለ እንበል ያ አልማዝ ያለበት ቤት ሙሉ ለሙሉ ቢቃጠል አልማዙ ምንም አይሆንም። ምንም። በነበረው ቅርጹ፣ በነበረው ንጽህናው እናገኘዋለን።

የሚያስገርመኝን ስድስተኛውን የአልማዝን ባህሪ ልንገራችሁ። ወርቅ ላይ አሲድ ድፉበት ወርቁ ይበላሻል። አልማዝ ላይ አሲድ አፍስሱበት ምንም አይሆንም። አይበላሽም።

የመጨረሻው እና ሰባተኛው የአልማዝ ባህሪ በጣም ውድ ነው። በጣም ውድ ነው። የአውራጣትህን ራስ የምታክል ዳይመንድ አንድ ትልቅ ፎቅ ይገዛል። በጣም ውድ ነው።

ከጓደኞቻችሁ በታች 600 ኪሎ ሜትር ወርዳችሁ ፣ በ1200 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ስቃይ ውስጥ ያለፋችሁ፣ በፕሬዠር ውስጥ ለበርካታ አመታት ያለፋችሁ እናንተ አልማዝ ሁናችሁ የተሰራችሁ ሰዎች ናችሁ።

ሰዎች ጠጠር ብትመስሏቸውም አልማዞች ናችሁ። ዋጋችሁ በጣም ውድ ነው።

... ከተማሩ ሰዎች ይልቅ፣ ብዙ ድግሪ ከተሳካላቸው ሰዎች ይልቅ፤ በመከራ ያለፉ ሰዎችን አከብራለሁ። ዋጋ የከፈሉ ሰዎችን አከብራለሁ። በስቃይ ውስጥ ያለፉ ሰዎችን አከብራለሁ። ምክንያቱም ዋጋቸው በጣም ውድ ነው።
https://t.me/ermisportfitness
https://t.me/ermisportfitness
50 viewsedited  05:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ