Get Mystery Box with random crypto!

ኢርከብ ማዓና إركب معنا

የቴሌግራም ቻናል አርማ erkebmeana — ኢርከብ ማዓና إركب معنا
የቴሌግራም ቻናል አርማ erkebmeana — ኢርከብ ማዓና إركب معنا
የሰርጥ አድራሻ: @erkebmeana
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 568
የሰርጥ መግለጫ

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
በቴሌ ግራም መረጃዎች ልዩ ልዩ ኢስላማዊ ስነ ፅሁፎች ፤ ሙሓደራዎች ፤ የተለያዮ ቂርዓቶች እንዲደርሳችሁ ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉን
http://t.me/erkebmeana
ለሀሳብና ለጥቆማ 👇
@ErkebmeanaBot

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-03 22:13:09 አስቸኳይ የድጋፍ ጥሪ

በሰጋጆች ድርቅ የተመታውን የዱራሜውን ቢላል መስጂድ ሁላችንም ለመታደግ እንረባረብ

አቡ ዳውድ ኡስማን

መዕክቱን አንብበው ሲጨርሱ ለሌሎችም ሼር ያድርጉት

በደቡብ ክልል በከምባታ ጠምባሮ ዞን በዱራሜ ከተማ በካሻ ቀበሌ አሮጌ ሰፈር የሚገኘው ቢላል መስጂድ አካባቢው የነበሩ ሙስሊሞች እንዲሁም የመስጂዱ ኢማም ሚስታቸው እና ልጃቸው ሳይቀር ከፍረው የመስጁዱ ሙዓዚን እና ኢማም የሆኑት ሼይኽ መሐመድ ኑር ብቻቸውን በመስጂዱ እየሰገዱ እንደሚገኙ መገለፁ ይታወሳል::

በዚህ ትልቅ መስጂድ ውስጥ ብቻቸውን አዛን እያወጡ ብቻቸውን ኢቃም ብለው እንደሚሰግዱ መገለፁን ተከትሎ ከፍተኛ ቁጭት እና ሀዘን በሁላችንም ላይ ተፈጥሯል::

መስጁዱ በእድሳት እጥረት በመጎዳቱ ዝናብም እያፈሰሰ እንደሚገኝ እንዲሁም ሌሎች እድሳቶችም እንደሚያስፈልገው ተገልፆ ነበር::

የአካባቢውን ሙስሊሙ ማህበረሰብ ወደ ዲናቸው እንዲመለሱ፣ ባዶ የሆነው መስጂድም በጀምዓ እንዲሞላ፣ የከፈሩትንም ለመመለስ ህዝበ ሙስሊሙ በአንድነት ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቦ ነበር::

ይህን አሳሳቢ ጉዳይ ቀድሞ መረጃው የደረሳቸው በደቡብ ክልል የአክፍሮት ሃይላትን የኩፍር ዘመቻ ለመመከት መሬት ላይ የወረዱ በርካታ ፕሬጀክቶችን፣ መስጂዶችን እና መድረሳዎችን እያሰሩ የሚገኙት ተወዳጁ ኡስታዛችን ኡስታዝ ሷዲቅ መሐመድ(አቡ ሐይደር) ይህንንም የዱራሜ መስጂድ ጉዳይ መፍትሄ እንዲያገኝ እየለፉ ይገኛሉ::

በዚህም መሰረት ይህን መስጂድ ለመታደግ እና የአክፍሮት ሃይላትን እንቅስቃሴ በመመከት የአካባቢውን ህዝበ ሙስሊም ወደ ዲኑ ለመመለስ ይቻል ዘንድ ሁሉም ህዝበ ሙስሊም ያቅሙን ያህል ድጋፍ የሚያደርግበት ሁኔታ ተመቻችቷል::

በኡስታዝ ሷዲቅ መሐመድ (አቡ ሃይደር ) አስተባባሪነት
በዱራሜ ከተማ በካሻ ቀበሌ አሮጌ ሰፈር የሚገኘው በዚሁ የቢላል መስጂድን ማዕከል የሚያደርግ እንቅስቃሴ ተጀምሯል::

በቀዳሚነት ለመስጂዱ ቋሚ ኡስታዝ መቅጠር እንዲሁም መስጂዱ በሚገኝበት በዱራሜ ከተማ በዱራሜ ዩኒቨርሲቲ ለሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች በዚህ መስጁድ ላይ ታላቅ የዳዕዋ ኮንፍረንስ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል::

ይህ ኮንፍረንስ ከነሐሴ 13-15/2014 ለሶስት ቀናት ኢማሙ ብቻቸውን ሲሰግዱበት በነበረው ቢላል መስጂድ የሚሰጥ ይሆናል::

ይህ ታላቅ ኮንፍረስ ሙስሊም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ማዕከል በማድረግ በአካባቢው ያለውን የኩፍር ዘመቻ ለመመከት እና ሰዎች ወደ ዲናቸው እንዲመለሱ እንዲሁም የመስጁዱን ጀምዓ በማጠናከር ሰፊ ስራዎችን ለመስራት የሚያግዝ ነው::

አሁን ላይ የሁላችንንም ርብርብ እና ድጋፍ የሚሹ ወጪዎች ያሉ ሲሆን እነዚህም:-

1/ ቋሚ የኢማም ደሞዝ ክፍያ
2/ የመሰጂዱ አጥርን ማሳጠር
3/ መስጁዱ የጎደለውን ነገር ሁሉ ማሟላት እና
4/ ለታሰበው ታላቅ የዳዕዋ ኮንፍራንስ ወጪውን መሸፈን ይገኝበታል:

በአሁኑ ሰዓት ብቸኛ የነበሩትን ሼይኽ መሐመድኑርን የሚያግዝ በመስጁዱ በቋሚነት ሊያገልግል የሚችል ብቁ ኡስታዝ የተገኘ ሲሆን በዋናነት ኡስታዙም የመስጁዱ ኢማም በቋሚነት በመሆን እንዲያገለግል፣ ከዐሱር በኋላ ልጆችን እንዲያቀራ እንዲሁም ለካምፓሱ ተማሪዎች ኪታብ እንዲያቀራ ታስቧል::

እነዚህን አስቸኳይ ስራዎች በመስጂዱ ለመስራት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሃገር ውጪ ያላችሁ የበኩላችሁም ድጋፍ ታደርጉ ዘንድ በአላህ ስም እንጠይቃለን::

በተከሰተው ነገር ከንፈር መምጠት እና ማዘን ብቻ ሳይሆን የመፍትሄ ሃሳብ ሲቀርብም ሁላችንም በቻልነው ያህል ማገዝ ይጠበቅብናል:: መፍትሄው በአንድነት መሬት ላይ ሊወርድ የሚችል ስራ መስራት ስንችል ብቻ ነው::

ለተዘረዘሩት ወጪዎች ድጋፍ ማድረግ ለምትፈልጉ ሁሉ በኡስታዝ ሷዲቅ መሐመድ ስም በተከፈተው አካውንት ድጋፍ ማድረግ ትችላላችሁ

1. COMMERCIAL BANK OF ETHIOPIA
1000317507589
SADIK MOHAMMED AHMED

2. ABYSSINIA BANK
83047178
SADIK MOHAMMED AHMED

3. ኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ
1011300008645
SADIK MOHAMMED AHMED

ለበለጠ መረጃ በዚህ ስልክ መደወል ትችላላችሁ
0911103231

ይህን መልዕክት ሁላችንም ሼር በማድረግ እናዳርስ!
18 viewsHamid Al - Ghazali , 19:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 12:24:03 @ErkebmeanaBot

መመዝገብ ለምትፈልጉ ይህን ሊንክ በመጫን ስማችሁን በመላክ ይመዝገቡ
127 viewsHamid Al - Ghazali , 09:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 08:58:38 ፎቶ የተፈለገው ለመታወቂያ ሲሆን ኮርስ እንደመሆኑ ስርአት ባለው መልኩ የተመዘገቡ ተማሪዎች እንዲከታተሉ ስለተፈለገ ነው ።
ሆኖም ግን ሙተነቂብ የሆኑ እህቶችና በተለያየ ምክንያት ፎቶ መነሳት የማይችሉ አካሎች በፎቶ ምክንያት ኮርሱ እንዲያመልጣቸው ስለማንፈልግ በዚህ ጉዳይ እንዳትጨነቁ ለማለት እንወዳለን
149 viewsHamid Al - Ghazali , 05:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 17:10:04 @ErkebmeanaBot

መመዝገብ ለምትፈልጉ ይህን ሊንክ በመጫን ስማችሁን በመላክ ይመዝገቡ
152 viewsHamid Al - Ghazali , edited  14:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 20:40:31
170 viewsHamid Al - Ghazali , 17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 20:40:31 ልዮ የክረምት ኮርስ ፕሮግራም
በባዮሽ መስጂድ

በባዮሽ መስጂድ የተለያዮ የዲን ትምህርት ኮርሶችን ለመስጠት ተዘጋጅተዋል ።

ትምህርቱን የሚሰጡት ዑስታዞች መካከል
ዑስታዝ ማህሙድ ሀሰን ፣ ዑስታዝ ኻሊድ መሓመድ ኑር ሌሎችም


የመዝገቢያ መስፈርት
1 ጉርድ ፎቶ
እድሜ ከ 15 በላይ
የስልጠናው ሙሉ ክፍያ 200 ብር
ስልጠናውን በአካል መገኘት የሚችል

የምዝገባ ቀን ከሃምሌ 7 እስከ ሃምሌ 12

ትምህርቱ የሚሰጥባቸው ጊዜያቶች

ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጥዋቱ ከ 3፡30 እስከ 6፡30

የመመዝገቢያ አድራሻ ፡ በባዮሽ መስጂድ ቢሮ
ስልክ 0913667826
0979274717
0960280404

ማሳሰቢያ ፡ የዲን ኮርሱ 80 % ለሸፈነ ተሳታፊ የተሳትፎ ምስክር ወረቀት የሚበረከት ይሆናል ።
141 viewsHamid Al - Ghazali , 17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 22:54:04 በሙስሊም ህይወት ምርጥ ምሽቱ
ለይለቱል ቀድር ሲሆን ፤
ምርጡ ቀኑ ደግሞ የአረፋ 9ኛው ቀን ነው ።
153 viewsHamid Al - Ghazali , 19:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 17:52:26 አረፋህ ሊመን አረፈህ!
======================
ነገ ቤት የማፅጃ ወይ መጋረጃ የማውረጃ ቀን አይደለም። የኢድ ሸመታም ሆነ የመዝናኛ እንዲሁ!
ነገ አላህ የሰማይ ባለሟሎች ላይ በአረፋ ሰዎች የሚኩራራበት፤ የሰው ልጆች ከእሳት በገፍ ነፃ የሚባሉበት ከሁሉ በላይ ዱአዎች በሙሉ ተቀባይነት የሚያገኙበት እለት ነው።
ለይለቱል ቀድር ባትታወቅ የውሙ አረፋ ትታወቃለች። በለይለቱል ቀድር መላእክት ቢወርዱ በአረፋ አላህ (እሱን በሚመጥን አወራረድ) የሚወርድበት ነው!
ነገ አላህ በጊዜ ፀጋ ላጣቀማችሁ አንድ to do list ላካፍላችሁ

ጠዋት

ከፈጅር በፊት ከለይሉ ጥቂቱን መስገድ፣ ስሁር መመገብ እና ኢስቲግፋር ማብዛት!
ከሰላት በኋላ ቀጥታ ተክቢራ መጀመር ከዛም ፀሀይ እስክትወጣ ቁርአን፣ተህሊል፣ተህሚድ በአጠቃላይ በዚክር ማሳለፍ(አዝካረ ሰባህ ሳይረሳ)
ፀሀይ ስትወጣ የፀሃይ መውጣትን ሰላት እዛው ከመስገጃችን ሳንነሳ በመከወን ከረሱሉ (ሰ.ዐ.ወ) ጋር ሀጅ የማድረግን ምንዳ እንዲጎናጸፍ
ለቀን ኢባዳ ያግዘናል ብለን ካሰብን መጠነኛ እኝቅልፍ እንተኛ። ስንነሳ በትንሹ 4 ረክኣ ሰላተ ዱሃ እንስገድ!

ከሰአት

ከዝሁር ሰላት በኋላ ቁርዐናችንን እንቀራለን። የአረፋ ኹጥባ(ከመስጂደ ነሚራህ የሚተላለፈውን) መልእክት በጥብቅ መከታተል
ልባችንን ሊያረጥብ የሚችል መፅሐፍ ወይም ቪድዮ እየተመለከትን እራሳችንን እናርጥብ!
ከአስር በጥሎ እንዲሁ በቁርአን እና በዚክር መግሪብ 1 ሰአት አቅራቢያ እስኪቀረው ማሰለፍ!
የእለቱ ወሳኝ ሰአት ይህ ነው።
የተሰበረ የሚጠገንበት፤ የታመመ የሚፈወስበት፤ ተስፋ የቆረጠ ተስፋው ነፍስ ሚዘራበት ድንቅ ሰአት!

ዱኣ!!! ዱኣ ብቻ!

በዚህ ቀን ከእሳት ነፃ አለመባል ኪሳራ ነው። ምኞት ኖሮን ምኞታችንን ሳናሳካ መቅረት ቂልነት ነው!
ነገ አላህ አልመረጥንም እና እየተመለከታቸው ከሚኮፈስባቸው ጌታቸውን ለማላቅ በነጭ ተውበው ከአረህማን ድግስ ከሚታደሙት አልሆንም!
"አረፋ ተራራ ላይ መቆም ያልቻለ
አላህ ያሳወቀው ድንበር ላይ ይቁም
ሙዝደሊፋ ላይ ማደር ያልቻለ
በአላህ ትእዛዝ ላይ ይደር...ያቀርበዋልና!
ሚና ላይ እርዱን መከወን ያልቻለ
ምኞቱን ይረድ! ከፍ ይላልና።
ወደ ቤቱ በርቀት ምክንያት መድረስ ያልቻለ
ከደም ስሩ ቅርብ ወደ ሆነው የቤቱ ጌታ ይከጅል!" ኢብኑ ረጀብ
እርቅ ይበጀናል!
Hamid
170 viewsHamid Al - Ghazali , edited  14:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 16:35:41 ቀደምት አረቦች

አንድ ሰው በሚስቱ ላይ በእጅጉ ከመቅናቱ የተነሳ እሷ የጋለበችውን ፈረስ ሌላ ወንድ እንዳይጋልበው ሲል ፈረሱን ከመሸጥ ይልቅ ያርደው ነበር ።

አንዲት ሴት ሙታ በምትቀበርበት ወቅት ባእድ ወንዶች ወደ አስክሬኗ እንዳይቀርቡ ሰግተው የሟች ቤተሰቦች የቀብሯን ቦታ ያጨናንቁ ነበር ።
ጀናዛውን ሸፍኑት ቀብሩን ሸፍኑት የሚሉ ድምጾች ይበራከቱ ነበር ይህ ሁሉ የሚሆነው እሷ ከፈኗ ውስጥ ሆና ለእርሷ ካላቸው ቅናቻ ነበር ።

በህይወት ያለች ሴት ከእርሷ በላይ ሊቀናባት አይገባም ?

የሴት ልጅ አለባበስ የአባቷን አስተዳደግ የእናቷን ጥቡቅነት የወንድሟን ቅናት የባሏን ወንድነት ያመላክታል ።

ለዚህም ነው አላህ መርየምን ሲያስታውስ
(يَاأُخْتَ هَارُونَ مَا ڪَانَ أَبُوكِ امْرَأَ سَوءٍ وَمَا ڪَانَت أُمُّكِ بَغِيًّا).

(አንቺ የሀሩን እህት ሆይ አባትች ክፉ ሰው አልነበረም እናትሽም ሴተኛ አዳሪ አልነበረችም) ሲሉ በአባቷ እና በእናቷ ያስታወሷት

ስልጣኔ ፣ ነፃነትና ዲሞክራሲ ማለት ሃይማኖትን፣ ሎጂክን፣ እሴትን፣ ጨዋነትን እና ሥነ ምግባርን መተው ማለት አይደለም።
128 viewsHamid Al - Ghazali , 13:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 15:40:39 Watch "''ሐጅ የተውሂድ አርማ''" on YouTube


145 viewsHamid Al - Ghazali , 12:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ