2023-01-07 03:15:36
29/04/2015ዓ.ም
[ ስለ ልደት በዓል ምስጢር እና ትንታኔ በዲያቆን ኢዮብ ጌታቸው። ]
እንኳን ለጌታችን ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብርሐነ ልደቱ በሰላም እና በጤና አደረሳቹ።
"ዮም ተወልደ መድኀኔ ዓለም
ዮም ተወልደ ከሣቴ ብርሃን"
(የዓለም መድኃኒት ዛሬ ተወለደ
ብርሃንን የሚገልጥ ዛሬ ተወለደ) ማኅሌታይ ቅዱስ ያሬድ ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ስምረቱ ለሰብዕ ብለን የስብከት የትምህርት የምስጋናን ነገር እናገራለሁ።
ቅዱስ ያሬድ በማኅሌቱ
"ለዘተወልደ እም ቅድስት ድንግል ምንተ ንብሎ ናስተማስሎ ለመድኀኒነ ዓርዌ ገዳምኑ አንበሳ ወሚመ ከራድዮን" (ከእመቤታችን የተወለደውን ምን ብለን እንጠራዋለን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በምን እንመስለዋለን በዱር አውሬ አንበሳን ነው ወይስ ከራድዮን በሚባል ወፍ ነው።) አለ። አንበሳን እና ከራድዮንን ለምን ማንሳት አስፈለገ? አንበሳ፦ይህም የአንበሳን ዐዋቂነቱን ያስረዳል፤በዋሻው ውስጥ በተኛ ጊዜ ዐይኖቹን እና ቅድቦቹን ገልጦ ያልተኛ ይመስላል።ይህም ምሳሌ በመስቀል ላይ በሞተ ጊዜ ነፍሳትን የሸነገለ ሰይጣንን የተጠበበበት በኾነ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ይፈጸማል።ጠቢብ ሰሎሞን "እኔ የተኛኁ ነኝ፤ልቤ ግን ነቅታለች"ብሎ ገልፆታል። ከራድዮን፦ሁለመናው ነጭ ፀጉር የሆነ ወፍ ነው።በነገስታት ቤት ውስጥ ነው የሚገኘው።አንድ ሰው በጽኑ ህመም ከታመመ እና ለሞት የሚያደርሰው ከሆነ ከራድዮን ወደ ህመምተኛው ሄዶ ያየዋል የህመምኛውን በሽታ ተቀብሎ ወደ አየር ይበራል።የፀሐይ ግለት እስኪያቃጥለው፤
483 viewsEyob Getachew, 00:15