Get Mystery Box with random crypto!

የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በምልዓተ ጉባኤው ውሳኔ መሠረት ለኤጲስ ቆጶስነት ሹመት የተመረጡትን ፱(9) | EOTC TV

የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በምልዓተ ጉባኤው ውሳኔ መሠረት ለኤጲስ ቆጶስነት ሹመት የተመረጡትን ፱(9)ኙ መነኮሳት በአካል ተገኝተው ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረበ፡፡

ኢኦተቤ ቴቪ ሰኔ ፳፱/፳፻፲፭ ዓ/ም

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ግንቦት 14 ቀን 2015 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ ለዘጠኝ ክፍት አህጉረ ስብከት ኤጲስ ቆጶሳት እንዲሾሙ ውሳኔ በማስተላለፍ አስመራጭ ብፁዓን አበው ሊቃነጳጳሳት በኮሚቴነት መሰየሙ ይታወቃል፡፡

በዚህም መሠረት ሰኔ 28 ቀን 2015 ዓ.ም. የተሰየመው አስመራጭ ብፁዓን አበው ሊቃነጳጳሳት ኮሚቴ ለምልዓተ ጉባኤ ካቀረባቸው እጩዎች መካከል 9ኙን ቆሞሳት ለተለያዩ አህጉረ ስብከት በኤጲስ ቆጶስነት እንዲሾሙ መርጧል፡፡

በመሆኑም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በወሰነው መሠረት ከሐምሌ 1 ቀን 2015 ዓ.ም. እስከ ሐምሌ 7 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ በሚሰጠው ሥልጠና እንዲሳተፉ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም. በቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ተገኝተው ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ መተላለፉን ከጽ/ቤቱ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
EOTC TV
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++



"የቤተክርስቲያን የሆነውን ብቻ"
የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት
የዲጂታል ሚዲያ ገጾች
ለመረጃ +251985585858
➽ የዩቲዮብ ገጻችን
http://www.youtube.com/c/eotctv
➽ የፌስ ቡክ ገጻችንን
https://www.facebook.com/eotctvchannel
➽የቴሌግራም ገጻችን
https://t.me/eotctvchannel
➽ የቲክ ቶክ ገጻችን
https://vm.tiktok.com/ZMFSxXdUf/
➽ የዩቲዮብ ገጻችን Eotc tv 2



➽የትዊተር ገጻችን
https://twitter.com/EotcT/
➽የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/p/CknRF0MtB77/?igshid=MDJmNzVkMjY=