Get Mystery Box with random crypto!

ብፁዕ አቡነ አብርሃም እና ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤትን ጎበኙ። ዘ | EOTC TV

ብፁዕ አቡነ አብርሃም እና ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤትን ጎበኙ።
ዘጋቢ ቀሲስ መዝገቡ ጌታቸው
(EOTC TV//ኢኦተቤ ቴቪ / ሰኔ ፳፮ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም )
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤት ዋና ስራ አስኪያጅና የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤትን ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ወቅት የማተሚያ ቤቱ አመሠራረት ታሪክ የተዘከረ ሲሆን ፫ኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ አቡነ ተክለሃይማኖት ክርስትያን ያልነበሩ ወላጅ አልባ ታዳጊዎችን አሰባስበው አስተምረው በድርጅቱ ሥራ ሰጥተው ልጆቹ ቁም ነገር ላይ ያደረሱ መሆናቸው ተወስቷል።
ብፁዕ አቡነ አብርሃም እንዲህ ያሉ አባቶችን ተግባር አሁን ያለነው ምን መሥራት እንደሚገባን ትልቅ አስተማሪ ታሪክ መሆኑን ጠቁመው ቢቻል በ፳፻፲፮ የበጀት ዓመት አለበለዚያ በ ፳፻፲፯ ዓ.ም በጀት ዓመት የድርጅቱ ሥራ መሠረታዊውን ለውጥ የሚያመጣ መሆን እንዳለበት ብፁዕ ጠቅላይ ስራ አስኪያጁ ጠቁመዋል።
የሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በበኩላቸው በታሪክ የምንሰማውን የማተሚያ ቤታችንን ሥራውን በማየታችን ትልቅ ትምሕርት ያገኘንበት ሲሆን ክርስቲያን ያልነበሩ እጓለማውታ እና የካህናት ልጆችን በዚህ እያሠራችሁ እዚህ ማድረሱ ተቋሙን የሚያስመሰግንነው በማለት ማተሚያ ቤትና ሰንበት ትምህርት ቤት ለግብጽ ቤተ ክርስቲያን የዕድገት መሠረት እንደሆኑ ጠቁመዋል ።
EOTC TV
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++



"የቤተክርስቲያን የሆነውን ብቻ"
የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት
የዲጂታል ሚዲያ ገጾች
ለመረጃ +251985585858
➽ የዩቲዮብ ገጻችን
http://www.youtube.com/c/eotctv
➽ የፌስ ቡክ ገጻችንን
https://www.facebook.com/eotctvchannel
➽የቴሌግራም ገጻችን
https://t.me/eotctvchannel
➽ የቲክ ቶክ ገጻችን
https://vm.tiktok.com/ZMFSxXdUf/
➽ የዩቲዮብ ገጻችን Eotc tv 2



➽የትዊተር ገጻችን
https://twitter.com/EotcT/
➽የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/p/CknRF0MtB77/?igshid=MDJmNzVkMjY=