Get Mystery Box with random crypto!

በሰሜን አሜሪካ በዳላስ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን እኤአ የ2023 የሁለተኛ ደረጃ | EOTC TV

በሰሜን አሜሪካ በዳላስ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን እኤአ የ2023 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ወጣቶች የምርቃት መርሐ ግብር ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ተከናወነ።
በእለቱ ሥርዓተ ቅዳሴው በእንግሊዝኛ ቋንቋ ተከናውኗል።
(EOTC TV//ኢኦተቤ ቴቪ / ሰኔ ፳፬ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም )
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
በዳላስ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል በተከናወነው የምርቃት መርሐ ግብር ብፁዕ አቡነ ሣዊሮስ በሰሜን አሜሬካ የቴክሳስና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ; ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ የማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጩ የብዙኃን መገናኛ ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ የተመራቂዎች ቤተሰቦች እና ተመራቂ ወጣቶች እንዲሁም ምእመናን በተገኙበት ከተለያዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ትምህርታቸውን ያጠናቀቁና ወደ ከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት የሚገቡ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዩጵያውያን ተማሪዎች የምርቃት መርሐ ግብር ተከናውኗል።
በእለቱ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ሥርዓተ ቅዳሴው ተከናውኗል። መርሐ ግብሩን የመሩት መጋቤ ሃይማኖት ዶክተር አንዱዓለም ዳግማዊ " በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ" በሚለው የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት መነሻነት ወጣቶች አምላካቸውን ይዘው ሕይወታቸውን ስኬታማ ለማድረግ ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው ገልጸዋል።
ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ የማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በዕለቱ ባስተላለፉት መልዕክት የወጣቶች በትምሕርት እና በሥነ ምግባር ተኮትኩቶ ለዚህ መድረስ ለወላጅ ለቤተክርስቲያንና ለሀገር ተስፋ ነው ያሉ ሲሆን "የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው" በሚለው አምላካዊ ቃል መነሻነት ትምሕርተ ወንጌል ሰጥተዋል።
ብፁዕ አቡነ ሣዊሮስ በሰሜን አሜሬካ የቴክሳስና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁ የመልካም ምኞት መግለጫ ያስተላለፉ ሲሆን ተመራቂዎች በቀሪ ሕይወታቸው ከቤተክርስቲያን እንዳይለዩ አደራ ብለዋል። በዕለቱ ለተመራቂዎች ከቤተክርስቲያኗ የመታሰቢያ ስጦታ ተበበርክቷል።
EOTC TV
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++



"የቤተክርስቲያን የሆነውን ብቻ"
የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት
የዲጂታል ሚዲያ ገጾች
ለመረጃ +251985585858
➽ የዩቲዮብ ገጻችን
http://www.youtube.com/c/eotctv
➽ የፌስ ቡክ ገጻችንን
https://www.facebook.com/eotctvchannel
➽የቴሌግራም ገጻችን
https://t.me/eotctvchannel
➽ የቲክ ቶክ ገጻችን
https://vm.tiktok.com/ZMFSxXdUf/
➽ የዩቲዮብ ገጻችን Eotc tv 2



➽የትዊተር ገጻችን
https://twitter.com/EotcT/
➽የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/p/CknRF0MtB77/?igshid=MDJmNzVkMjY=