Get Mystery Box with random crypto!

በኩዌት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 10ኛ ዓመት የምስረታ በዓል እየተከበረ ነው። | EOTC TV

በኩዌት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 10ኛ ዓመት የምስረታ በዓል እየተከበረ ነው።
ኢኦተቤ ቴቪ ሰኔ ፪/፳፻፲፭ ዓ/ም

የኩዌት ደብረ ምሕረት አቡነ ተክለ ሃይማኖትና ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን 10ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ብፁዕ አቡነ ድሜጥሮስ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በኩዌት የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶ/ር ሰይድ ሙሁመድ የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተወካዮች አባቶች በመከራ የተፈተኑ ሊቃውንትና ምዕመናን በተገኙበት እየተከበረ ይገኛል።

የበዓሉ ዋዜማ በተለያዩ መርሐ ግብራት እየተከበረ ይገኛል ከነዚህም ትምህሬተ ወንጌል እንዲሁም የዐሥር ዓመት ጉዞን የሚያሳይ ዐውደ ርእይ ለእይታ ክፍት ሆኗል።

በዓሉ ነገ ሲቀጥል በተለያዩ በመርሐ ግብራት እንደሚከበረም ከወጣው መርሐ ግብር ለማወቅ ተችሏል።

ዝርዝር መረጃ ቆየት ብለን እናደርሳለን።

መ/ር ኃይሉ በላይ (ኩዌት)