Get Mystery Box with random crypto!

ቅዱስ ሲኖዶስ በ3ኛ ቀን ውሎው በተለያዩ ጉዳዮች ውሳኔ አሳልፏል። (EOTC TV//ኢኦተቤ ቴቪ // | EOTC TV

ቅዱስ ሲኖዶስ በ3ኛ ቀን ውሎው በተለያዩ ጉዳዮች ውሳኔ አሳልፏል።
(EOTC TV//ኢኦተቤ ቴቪ // ግንቦት ፬    ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም )
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
ለኢኦተቤ ቴቪ (EOTC TV) ዕለታዊ ማብራሪያ የሰጡት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በሦስተኛ ቀን  የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ  ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን በተመለከተ ውሳኔ ማሳለፉን ገልጸዋል።
በዚህም ብፁዕ አቡነ ዲዎስቆሮስ የደቡብ ትግራይ ማይጨው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ብፁዕ አቡነ ቶማስ የአዊና መተከል ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ቀደም ሲል ያገለግሉባቸው በነበሩ አህጉረ ስብከቶች አገልግሎታቸውን እንዲቀጥሉ ጉባኤው ወስኗል።
ጉባኤው በዛሬው ውሎው እንዲነጋገርበት ተይዞ የነበረው የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ጉዳይ የጉባኤው የመጨረሻ አጀንዳ እንዲሆን የአጀንዳ ሽግሽግ አድርጓል።
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ  ለኢኦተቤ ቴቪ (EOTC TV) በሰጡት ዕለታዊ ማብራሪያ ጉባኤው የዋልድባ ዳልሻህ ኪዳነምሕረት ማህበረ ደናግል ገዳምን በተመለከተ፣ የያዘው አጀንዳ ላይ መወያየቱን እና ለውሳኔ በይደር መቆየቱን አረጋግጠዋል።
የብፁዕነታቸውን ማብራሪያ በዩቲዩብ ገጻችን እንድትመለከቱ እንጋብዛለን ።
EOTC TV
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++
             


        "የቤተክርስቲያን የሆነውን ብቻ" 
          የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት
                       የዲጂታል ሚዲያ ገጾች
ለመረጃ  +251985585858
➽ የዩቲዮብ ገጻችን
http://www.youtube.com/c/eotctv
➽ የፌስ ቡክ ገጻችንን
https://www.facebook.com/eotctvchannel
➽የቴሌግራም ገጻችን
https://t.me/eotctvchannel
➽ የቲክ ቶክ ገጻችን
https://vm.tiktok.com/ZMFSxXdUf/
➽ የዩቲዮብ ገጻችን Eotc tv 2



➽የትዊተር ገጻችን
https://twitter.com/EotcT/
➽የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/p/CknRF0MtB77/?igshid=MDJmNzVkMjY=