Get Mystery Box with random crypto!

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ወደቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ለሚጓዙ የምእመናን መተሰቢያ ድርጅት አባላት | EOTC TV

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ወደቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ለሚጓዙ የምእመናን መተሰቢያ ድርጅት አባላት ጸሎትና ቡራኬ አስተላለፉ።
++++++++++++++++++++++++++++++++
ቅዱስነታቸው ጸሎተ ቡራኬውን የሰጡት መጋቢት 30 ቀን 2015 ዓ/ም በመንበረ ፓትርያርክ ጽርሐ ተዋሕዶ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ለተገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መታሰቢያ ድርጅት አባላት ሲሆን ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ለሚጓዙ ተሰላሚ ምእመናን ወምእመናት ነው።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን መታሰቢያ ድርጅት ለኢየሩሳሌም የቦርድ ጽሕፈት ቤት ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ ፓትርያርክ ባቀረበው የመልካም ምኞት መልእክት የምእመናን መታሰቢያ ድርጅቱ ያከናወናቸውን መንፈሳዊ የሥራ ተግባራት፣በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማት በዘንድሮው 2015 ዓ/ም የሚያበረክተውን ከሰባት መቶ ኪሎ ግራም በላይ የምግብ ቁሳቁስ ፣ለገዳማቱ መብት የሚያከናውነውን የጥብቅና ሥራ እና ወዘተ ያከናወናቸውን የሥራ ተግባራት አብራርቷል።
ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ለተሳላሚ ምእመናን ባስተላለፉት አባታዊ መልእክት የምእመናን መታሰቢያ ድርጅቱ በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ለሚገኙ ገዳማት ብዙ አገልግሎት የሰጠ ሲሆን ለወደፊቱም ብዙ የሚጠበቅበት ድርጅት ነው ብለዋል።
በመጨረሻም ቅዱስነታቸው ለተሰበሰበው ተሳላሚ ምእመናን ጉዟችሁ የተባረከ ይሁን በማለት ጸሎትና ቡራኬ ሰጥተው አሰናብተዋል።
መጋቤ ምስጢር ሣህሉ አድማሱ