Get Mystery Box with random crypto!

የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ የታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ተማሪዎቹን ቅዱስ | EOTC TV

የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ የታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ተማሪዎቹን ቅዱስ ፓትርያርኩ በተገኙበት አስመረቀ።
መ/ር ማርቆስ ተበቃ
(ኢኦተቤ ቲቪ ሐምሌ ፫ ቀን ፳፻፲፬ ዓ. ም : አዲስ አበባ )
++++++++++++++++++++++++++++++
ታሪካዊው የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ የታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም መንፈሳዊ ትምህርት ቤት በልዩ ልዩ የቤተክርስቲያን ሙያዎች ያስተማራቸውን ፻፷ (አንድ መቶ ስልሣ) ደቀመዛሙርት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ከብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ ዛሬ በደማቅ ሥነ ሥርዓት አስመርቋል። የታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ታላላቅ ሊቃውንት ከሚፈሩባቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የትምህርት ተቋማት መካከል አንዱ ነው።
EOTC TV
++++++++++++++++++++++++++++++++
የወቅታዊ መረጃ ከትክክለኛው ከቅድስት ቤተክርስቲያን ልሳን ለማግኘት ተከታዮን የዩቲዩብ የፌስ ቡክ ቴሌግራም እና ኢንስታግራም ሊንኮች በመጫን ሰብስክራይብ እና ላይክ ያድርጉ፡፡ ሌሎችም ሰብስክራይብ እንዲያደርጉ በማድረግ መንፈሳዊ ኃላፊነትዎን ይወጡ፡፡
የዩቲዮብ ገጻችን
http://www.youtube.com/c/eotctv
የፌስ ቡክ ገጻችንን
https://www.facebook.com/eotctvchannel
የቴሌግራም ገጻችን
https://t.me/eotctvchannel