Get Mystery Box with random crypto!

ፍኖተ-ወራዙት ዘኦርቶዶክስ ⛪

የቴሌግራም ቻናል አርማ eotcone_holy_synod — ፍኖተ-ወራዙት ዘኦርቶዶክስ ⛪
የቴሌግራም ቻናል አርማ eotcone_holy_synod — ፍኖተ-ወራዙት ዘኦርቶዶክስ ⛪
የሰርጥ አድራሻ: @eotcone_holy_synod
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.35K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ፍኖተ-ወራዙት ቻናል መንፈሳዊ ትምህርቶችን የሚያገኙበት ሃይማኖታዊ ቻናል ነው። በዚህ ቻናል በመንፈሳዊ ሕይወትዎ የሚበረቱባቸውን መንፈሳዊ ጽሑፎችና መልእክቶች ባሉበት ሆነው መከታተል ይችላሉ።
    መልእክት ወይም አስተያየትና ጥቆማ ካለዎት
https://t.me/Tadiweszefinotewerazut
https://t.me/TadiwesTeshager
✞ይላኩልን
@Fenotewerazuteotc 👈ለግሩፕ

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-02-09 10:46:08
203 views07:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-09 08:32:12
ቀጥሎስ????
ወደ እግዚአብሔር ስንጮህ ሰንብተናል ፦ጸሎታችንን ልመናችንን ሳናቋርጥ ቀጥሎስ ምንድን ነው የምንሠራው??
#1ኛ፦የብልጽግና መንግሥት በኦርቶዶክሳውያኑ ላይ እያደረገ ባለው ፍጅት የተናበበ የመረጃ ልውውጥ ያስፈልገናል ፦ምንም ነገር ሳንንቅ የሰማነውን፣ ያየነውን፣የሆነውን፣ ጥርጣሬያችንን ለሚመለከተው ክፍላችን በፍጥነት ማሳወቅ ይጠበቅብናል፡፡ ሁሉም ነገራችን ንቁ መሆን አለበት፡፡
#2ኛ፦የቤተ ክርስቲያናችንን ድምጽ ብቻ በመስማት መተግበር ይጠበቅብናል፦ የተለያዩ ድንፋታዎችን በመስማት ምንም መጨነቅ የለብንም፦የማንሞትለት ሃይማኖት የለንምና፡፡
#3ኛ፦ የተሰለቡ ሀሳቦችን ማስወገድ ወይም ማራቅ፦ለምሳሌ ስንምት እንበዛለን፣ሊሆን ግድ ነው፣ምን ይደረግ ዘመኑ ነው፣እሱ ይሁነን፦ እና የመሳሰሉ ውስጣዊ አቅማችንን የሚሰልቡብንን ማራቅ፡፡
#4ኛ ፦ የተናበበ ኦርቶዶክሳዊ አደረጃጅት ማዘጋጀት ፦ ያሉንን አጠናክረን የሌሉንን ሠርተን በየአህጉረ ስብከታችን ክርስቲያናዊ ኅብረት ማዘጋጀት ያስፈልገናል፡፡
ኦርቶዶክሳዊነት ዘለዓማዊነትን በምድር ላይ የመኖር ጅማሬ ነው፡፡
የክርስቲያኖች አሁን የነገ ኑሯቸው ነው፡፡
212 views05:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 15:12:58
ጎንደር

ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተክ
245 views12:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 15:11:01
ልዩ ሐይሉ

ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተክርስቲያን
224 viewsedited  12:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 15:09:00
የሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሕገ ወጡን ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት እንደማትቀበልና ቤተክርስቲያንን የመክፈል ሙከራን እንደምታወግዝ አስታወቀች፡፡

ከስድስቱ ኦሬንታል እህት አብያተክርስቲያናት አንዷ የሆነችው የሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በፓትርያርኳ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ አግናጢዎስ ኤፍሬም ፪ኛ በኩል ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በጻፈችው ይፋዊ ደብዳቤ ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ በለየው ሕገ ወጥ ቡድን የተፈጸመውን ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት የጨረቃ ሹመት በማውገዝ ከቅድስት ሐዋርያዊት ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያ ጎን መቆሟን ገልጻለች፡፡
የሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖትን ሕጋዊ እና ሐዋርያዊ ቅዱስ መሪነት ብቻ የምትቀበል መሆኑን በመግለጽ ቤተክርስቲያኗ ላይ ተከሰተው ፈተና እንዲያፍ በጸሎት እንደምትለምን ገልጻለች፡፡
EOTC TV
220 views12:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 13:13:43 አቤሴሎም አባቱን ለመግደል እና በአባቱ አስከሬን ላይ ለመፎከር እያዋጋ በጫካ ሲያልፍ የሚመካበትን የውበቱ መገለጫ የሆነውን ጸጉሩ እሾህ ያዘውና በቅሎው ሲሔድ እርሱ በዛፉ ላይ ተንጠልጥሎ ቀረ። “አቤሴሎምም በበቅሎ ተቀምጦ ነበር፥ በቅሎውም ብዙ ቅርንጫፍ ባለው በታላቅ ዛፍ በታች ገባ፥ ራሱም በዛፉ ተያዘ፤ በሰማይና በምድር መካከል ተንጠለጠለ፥ ተቀምጦበትም የነበረ በቅሎ አለፈ” /2ኛ ሳሙ 18 ፤ 9/ ተብሎ እንደተጻፈ ምሳሌያዊ በሆነ መንገድ በሰማይና በምድር መካከል ተንጠለጠለ። አስተውሉ ክርስቲያኖች ሁላችንም ቢሆን እንዲሁ በመካከል ሆነን ወይ ከምድር ወይ ከሰማይ ሳንሆን እንዳንቀር መጠንቀቅ አለብን።
እግዚአብሔር የቲፎዞ፣ የብሽሽቅ፣ የሽንገላ፣ የማስመሰል እና በአጠቃላይ ምድራዊ በሆኑ ነገሮች የታጀበን ሁሉንም ነገር አይቀበልም። እነዚህ እንዲያውም የነፍስ ቫይረሶች እና መንፈሳዊነትን የሚያበላሹ የሰይጣን ባክቴሪያዎች ናቸውና እነዚህን በመሰሉት ተለከፈን ጾም ጸሎታችንን እንዳናበላሸው እንጠንቀቅ። ከለፍላፊነት እና ከተሳዳቢነት በሽታም እንፈወስ። ይልቁንም ጦርነታችን የአቤሴሎም ጦርነት መሆኑን አወቀን የዳዊትን ልቡና ገንዘብ በማድረግ በመንፈሳዊነት እንዋጋ። ያን ጊዜ ጉልበተኛውን፣ ሸንጋዩን እና እንደ አቤሴሎም የሰውን ልብ ለጊዜው በማስመሰል የሰረቁትን ሁሉ ራሱ ፈጣሪያችን እንደ አቤሴሎም ያንጠለጥላቸዋል። አምላካችን የዳዊትን የንስሐ እና የማስተዋል ልቡና ለሁላችን አድሎን ከአምላካችን ጋር ታርቀን ጠላታችን ዲያብሎስን ድል የምንነሣበት ሱባኤ ያድርግልን፣ አሜን።
234 views10:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ