Get Mystery Box with random crypto!

እሰይ ነጋ እሰይ ነጋ ላመሰግንህ ነው አይኔን የከደንኩት አንተን አምኜ ነው(፪) በበደሌ ሳትፈር | ሐመረ ኖኅ(የኖኅ መርከብ)

እሰይ ነጋ እሰይ ነጋ ላመሰግንህ ነው
አይኔን የከደንኩት አንተን አምኜ ነው(፪)

በበደሌ ሳትፈርድ ስትጠብቀኝ አለህ
ከኔ በላይ ለኔ ታስብልኛለህ
የማታንቀላፋው ትጉህ እረኛዬ
ብርሃኑን ያየሁት ባንተ ነው ጌታዬ

ቀናቶቼን ሰጠሁ ላንተ አሳልፌ
በሰላም እተኛለሁ በክንድህ አርፌ
ተመስገ ማለትን በብርሃን ጨለማ
ታስተምረኛለህ በወፎቹ ዜማ

ትናንት ትናንት አልፎ ስላየሁ አዲስ ቀን
ከእንቅልፌ ስነቃ እላለሁ ተመስገን
አንተ ባታነጋው የጨለመውን
አልኖርም ነበረ ዛሬ ባልኩት ቀን

ሁሉም የሚሆነው እንደየ ስርዓቱ
ባንተ ብቻ እኮ ነው መጨለም መንጋቱ
ስላደረግህልኝ ምኔን ልክፈልህ
ተመስገን ብቻ ነው ሥላሴ ዋጋህ

በብርሃን ተተካ አስፈሪው ጨለማ
እንደኔማ ሳይሆን ምሕረትህ ቀድማ
የኔ ያልኳት ዛሬ ነግታ የምትመሸው
በጥበቤ አይደለም በበጎነትህ ነው

ሊቀ መዘምራን



መዝ፶፱፥፲፮
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮

╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯