Get Mystery Box with random crypto!

የተዋሕዶ ልጅ

የቴሌግራም ቻናል አርማ eotch — የተዋሕዶ ልጅ
የቴሌግራም ቻናል አርማ eotch — የተዋሕዶ ልጅ
የሰርጥ አድራሻ: @eotch
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.11K
የሰርጥ መግለጫ

https://t.me/themonkintheworld
https://t.me/lllibrary

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-11-29 15:34:53
ልብህ እሱን ከመዘከር አይለይ።(ልብህ) የጣዕሙ መገኛ ይሆን ዘንድ መልክህ በፍቅሩ ብዛት ከእሳት እንደገባ ብረት የተለወጠ ይሁን። ጣዕሙ በልቦናህ ያድር ዘንድ። ሕዋሳተ ነፍስ ሕዋሳተ ሥጋ ደስ በሚላቸው ገንዘብ፤ እሱን በመሻት ብታዝን አግኝተኸው ደስ ይልሃል። እያለቀስህ መከራ እየተቀበልህ እሱን ለማየት መንፈሳዊ ቅንዓትን ብትቀና መልኩን በዓነ ነፍስ ታየዋለህ። ሐዘንህን ትዘነጋለህ።
....
በተዘክሮ ጸንተህ የኖርህ እንደሆነ የፀሐይ ብርሃን ከክበቡ ጋር እንዲዋሐድ ብርሃኑን ተዋሕዶህ ታያለህ። ምሉእ ስፉሕ ወደሚሆን ወደ ጌትነቱ ብትገባ በነፍስ በሥጋ በውሥጥ በአፍአ መላእክት በብርሃናቸው ይሸፍኑሃል። ወዲያ ወዲህ ባልህ ጊዜ ምድርን በፊትህ እንደሌለች አድርጋት።

አረጋዊ መንፈሳዊ (ድርሳን 24)
297 viewsedited  12:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-27 07:11:42
ሕማሜን በሕማምህ አድን፤ በቁስልህም ቁስሌን ፈውስ፡፡ ደሜን ከደምህ ጨምር፤ ሕይወት የሆነ የቅዱስ ሥጋህን መዓዛም በሥጋዬ ጨምር፤ በጠላቶች /በአይሁድ/የጠጣሃው ከርቤም ክፉ ሐሞትን የጠጣች ነፍሴን ያጣፍጣት፡፡ በሰፊው መስቀል ላይ የተዘረጋው ሥጋህም ሕሊናዬን ወደ አንተ ያድርገው:: በጠላት /በዲያብሎስ ድል ተነስቻለሁና። በመስቀል ላይ የዋለው ራስህ በርኩሳን ዘንድ የተቀጠቀጠ ራሴን ከፍ ያደርገው፡፡ በከሀድያን የተቸነከሩ ቅዱሳት እጆችህም ወደ አንተ ይንጠቁኝ፡፡

በወንጀለኞች ምራቅንና ጉስቁልናን የተቀበለ ፊትህ በኃጢአት የጐሰቆለ ፊቴን ያብራልኝ፡፡ የተሰቀለች ሰውነትህም ወደ አባትህ ዐረገች:: ጸጋህም ወደ አንተ ታድርሰኝ፡፡ አቤቱ ለመማጸን ዕንባ የለኝም፡፡ ለመለመንም ያዘነ ልብ የለኝም፡፡ ልጆችህን ወደ ርስታቸው የሚሰበስብ ንስሐና ኀዘንም የለኝም። ከጥፋት ብዛት የተነሣም ሕሊናዬ ጠቆረ፡፡ በእነዚህና በመሳሰሉትም ልቡናዬ ተሸፈነ፡፡ ወደ አንተ እመለከት ዘንድም ኃይል የለኝም፡፡ ከክፋት የተነሣም አዕምሮዬ ቀዘቀዘ፡፡ በተቃጠለ ፍቅር ዕንባን ማፍሰስም ተሳነው፡፡

የመልካም ነገር ሁሉ መዝገብ ክርስቶስ ሆይ፤ አንተና ለመፈለግ በፍቅር እወጣ ዘንድ ፍጹም ንስሐንና ትጉ ልቡናን ስጠኝ፡፡ ስለ አንተም ከሁሉ የተለየሁ ሆንሁ: ቸር ሆይ፣ ከባሕርዩ የወለደህ ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞም በባሕርዩ የነበርህ የአብን ጸጋ ስጠኝ፡፡ አርአያህና አምሳልህም ውስጤን ያድሰው:: እነሆ ተውሁህ፤ አንተ ግን አትተወኝ፤ ወደ አንተ መጣሁ፤ አንተም እኔን ለመፈለግ ውጣ፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
(ውዳሴ አምላክ ዘሐሙስ)
692 views04:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-17 20:49:44
በሥጋ ደመና ተጭኖ መመላለስን እንማያውቅ፤
ወደ ግብጽ ምድር ሲወርድ ደክሞ አላበው፤
የአበባ  ከንፈሮቹ ውበትም በፀሐይ ሐሩር ጠወለገ፤
መከታ የሆኑ የእናቱን ጡቶች ለመጥባት በወደደ ጊዜ! ወተት አጥቶ እንደሕፃናት አለቀሰ፤
ስለወልድ እንባ መፍሰስ የእኔም እንባ ይፍሰስ፡፡

....

ያንጊዜ በስደቱ ከእሱ ጋር ብኖር፤
እሱን በጀርባዬ ማዘልን በተመኘሁ ነበር፤
የእግሩንም ትቢያ በምላሴ እልስ ዘንድ፤
በዐለት ላይ የተሳለ የእጁን ምልክትም በአፌ እስም ዘንድ፤
የዮሴፍ በትር በተተከለበትም ከእሱ ጋር አርፍ ዘንድ፤
በማርያም ልጅ የፍቅር ጦር ልቤ ቆሰለ፡፡


ሰቆቃወ ድንግል
654 views17:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-17 20:24:43
የኢየሩሳሌም ቆነጃጅት ሆይ!
ማርያምን በቍስቋም ተራራ፣ በጫካውም ካገኛችኋት በመከረኛ ዓለም በጭንቀት ያለሁ፤
የጐስቋላ አገልጋይዋን ልቅሶ ትነግሯት ዘንድ፤
በኃያሉ አምላክ ስም አምላችኋለሁ።

ሰቆቃወ ድንግል 7
560 viewsedited  17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-17 20:18:29
ወደ ሩቅ ሀገር መፍለሴን ከዚህም ወደኋላ ወደ ማልመለስበት መሄዱንም ባሰብኩ ጊዜ
ድንግል የስደትሽ ልቅሶ መዝሙር ሆነኝ።ማርያም ሆይ ከአንቺ በቀር ሌላ አዋቂ አማካሪ የሚሆነኝ የለኝምና በልብሽ የማድር በሕሊናሽም የምኖር በአፍሽም የምነገር የምታሰብ አድርጊኝ፡፡

በእውነት መለኮታዊ እሳትንበወሰነ ጀርባሽ ተማፀንኩ።ድንግል ሆይ! በኀዘን የተፈተነ ኀዘንን ያውቃልና ሕፃን ልጅ አዝለሽ ወደ ደብረ ቊስቋም ስለመሄድሽ ብለሽ፤
ተመልከችኝ ፈጥነሽም አረጋጊኝ፡፡

ሰቆቃወ ድንግል (54-55)
498 viewsedited  17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 19:34:25
እመቤቴ ሆይ ለእኔም መልካሙን ስደት አስለምጂኝ። ስለ ልጅስ ስለወዳጅሽ ብለሽ የተሰደድሽ የክርስቶስ እናቱ እኔ ልጅሽን ተመልከቺኝ አንቺ ስለ ልጅሽ ተሰደድሽ እኔ ግን ከልጅሽ ተሰደድኩ። መልካሙን ስደት ዘነጋሁት ክፉውን ስደት ግን ተያያዝኩት። ስለ ልጅሽ ሳይሆን ከልጅስ ተሰደድኩ ማዳኑንም ሁሉ ዘነጋሁት። እመቤቴ ሆይ ለእኔም መልካሙን ስደት አስለምጂኝ ከሃጢአት ሀገር ወደ እውነተኛ ሀገር ወዳቺ ቅዱስ ስደት እሰደድ ዘንድ ስጪኝ።

ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ክፉን ስደት ከአንተ እርቄ እሰደድ ዘንድ ኀጢአቴ ግድ አለቺኝ ባዶ እግሬንም አስቀረቺኝ ለልቦናዬ(እግሮች) ንሰሃ የተባለ ቅዱስ መንገድን ሰራህለኝ ልመላለስበት ግን አልወደድሁም ። ስለ እኔ በምድር እንደተሰደድህ እኔም ወደ አንተ እንድሰደድ ቅዱስ መሰደድን ስጠኝ። ጌታዬ ሆይ ይህንንም ጊዜ ከሰጠኸንም ዘንድ መልካም የተመስጦ የፅሞና የንሰሐ ጊዜ አድርግልኝ። ከአንተ የምርቅበት ክፉ ስደት ሳይሆን ወደ አንተ የምቀርብበት ቅዱስ ስደትን እሰደድም ዘንድ ስጠኝ።

“ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።”
  — ማቴዎስ 5፥10

1.2K views16:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 21:19:33
አቤቱ የፊትህን ፀዳል በእኔ ላይ አብራ። ዓለም እና አምሮቷን የሚያየውን አይኔን ያሳውርልኝ ዘንድ። በፍቅርህም ገስጸኝ ልቦናዬ አለማዊ እንቅስቃሴ መንቀሳቀስን ያቆም ዘንድ። እንድወድህ ግድ የምትለኝ አንተ ማነህ? አይህም ዘንድ ተገለጥ የምትገለጠው ከሌላ አይደለም ከልቦናዬ ውስጥ ነው እንጂ።
634 views18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-02 23:44:19
ከአንተ ጋር እየተጨዋወተ የአለምን ጨዋታ የዘነጋ ሰው ብፁእ ነው።

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
639 views20:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 22:41:49 ...ወገኖቼ ሆይ ድንቅ ለሚሆን ለዚህ ለደገኛ ፍቅር አንክሮ ይገባል።

አረጋዊ መንፈሳዊ ድርሳን ፳፩
531 viewsedited  19:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 22:39:19
መልክህን ማየት ተለል ተለል ያደርገኛል።ፍቅርህም ያዝለኛል፤ አንተን መዘከር ያቃጥለኛል። ሁል ጊዜ ስራ ለመስራት ያነቃቃኛል ።አቤቱ ፍቅርህ በልቦና ፈጥኖ አደረ በሰውነቴ ተሰራጨ።ሕዋሳቴን ጸጥ አደረጋቸው።

አረጋዊ መንፈሳዊ ድርሳን ፳፩
530 viewsedited  19:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ