Get Mystery Box with random crypto!

መዝሙር ዮም ንወድሳ ከነሐሴ ፩ - ነሐሴ ፯ ዮም ንወድሳ ለማርያም በእንተ ዘተወልደ እምኔሃ መን | የበኵረ ሰባኪያን መምህር ምህረተአብ አሰፋ ትምህርቶች የማንቂያ ደወል 🔔

መዝሙር ዮም ንወድሳ

ከነሐሴ ፩ - ነሐሴ ፯

ዮም ንወድሳ ለማርያም በእንተ ዘተወልደ እምኔሃ መንክር ግርማ ኃይለ ልዑል ጸለላ ፆረቶ በከርሣ ውእቱኒ ቀደሳ (መ) እግዚኣ ለሰንበት ወአቡሃ ለምሕረት መንክር ግርማ ኃይለ ልዑል ጸለላ አማን መላእክት ይኬልልዋ

ትርጉም፦

ዛሬ (ኑ) ማርያምን እናመስግናት (ጌታችን) ከሷ ስለተወለደ በሚያስደንቅ ግርማ የልዑል ኃይል ጋረዳት በማኅፀኗ ወሰነችው እሱም አከበራት የሰንበት ጌታ የይቅርታ አባት በሚያስደንቅ ግርማ የልዑል ኃይል ጋረዳት በእውነት መላእክት ያመስግኗታል

ምስባክ፦

እምነ ጽዮን ይብል ሰብእ
ወብእሲ ተወልደ በውስቴታ
ወውእቱ ልዑል ሣረራ መዝ ፹፮፥፭

ትርጉም፦

ሰው እናታችን ጽዮን ይላል
በውስጧ ሰው ተወለደ
እርሱ ራሱ ልዑል መሠረታት

ምሥጢር፦

ሰው ሁሉ ቤተ መቅደስ እናታችን እግዚአብሔር አባታችን ይላል

ተወልደ በውስቴታ ተወልደ በውስቴታ ሲል ነው። ሕዝቅያስ በኢየሩሳሌም ተወልዶ በኢየሩሳሌም ይነግሣል አንድም ዘሩባቤል በባቢሎን ተወልዶ በኢየሩሳሌም ይነግሣል

ልዑል እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን በረድኤት አጸናት

አንድም በጸጋ ከሥላሴ የተወለደ ሰው ሁሉ እመቤታችን፤ ቤተ ክርስቲያን እናታችን እግዚአብሔር ወልድ አባታችን ይላል

ጌታ ከእመቤታችን ተፀነሰ ፅንሱን ልደት ልደቱን ፅንስ ይለዋልና አንድም በሥጋ ተወለደ አንድም ምእመናን ከቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ልደትን ተወለዱ

እግዚአብሔር እመቤታችንን በንጽሕና በቅድስና አጸናት ማለት እንድትችለው አደረጋት አንድም ቤተ ክርስቲያንን በደሙ አከበራት

የዕለቱ ወንጌል፦

ማቴ ፲፪፥፴፰ - ፍ

ቅዳሴ - ዘእግዝእትነ ማርያም