Get Mystery Box with random crypto!

የበኵረ ሰባኪያን መምህር ምህረተአብ አሰፋ ትምህርቶች የማንቂያ ደወል 🔔

የቴሌግራም ቻናል አርማ eotc_wengel — የበኵረ ሰባኪያን መምህር ምህረተአብ አሰፋ ትምህርቶች የማንቂያ ደወል 🔔
የቴሌግራም ቻናል አርማ eotc_wengel — የበኵረ ሰባኪያን መምህር ምህረተአብ አሰፋ ትምህርቶች የማንቂያ ደወል 🔔
የሰርጥ አድራሻ: @eotc_wengel
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 742
የሰርጥ መግለጫ

ይህ በቤተ ክርስቲያን መምህር በሆነው በምህረተአብ አሰፋ ስም የተከፈተው ቻናል በአድናቂው እና በወዳጁ የተከፈተ እንጂ በመምህር ምህረተአብ የተከፈተ አይደለም ቻናሉ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፅሁፎች
የማንቂያ ደወል መረጃዎች🔔
እና ሌሎችም ይቀርቡበታል
ለአስተያየት @EOTC_Wengel_bot
« ነዋ ወንጌለ መንግስት»

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-10 20:40:24 #ስለጾም

ጾም (ጦም) ማለት ሰውነትን ከመብል ከመጠጥና ከክፉ ስራ ከሐሜት ከመጥፎ ንግግርና ከኃጥያት ሁሉ መከልከል ማለት ነው ፡፡የጾም ጊዜ ራስን የማዋረድ የኃዘን የጸሎት የንስሐና የኑዛዜ ጊዜ እንደሆነ መጽሀፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡፡
  -  በአምላካችን ፊት ራሳችንን እናዋርድ ዘንድ፥ ከእርሱም የቀናውን መንገድ ለእኛና ለልጆቻችን ለንብረታችንም ሁሉ እንለምን ዘንድ በዚያ በአኅዋ ወንዝ አጠገብ ጾም አወጅሁ።(ዕዝ 8፡21)
  -  ይህንም ቃል በሰማሁ ጊዜ ተቀምጬ አለቀስሁ፥ አያሌ ቀንም አዝን ነበር በሰማይም አምላክ ፊት እጾምና እጸልይ ነበር፥(ነህ 1፡4)
  -  ማቅ ለብሼ በአመድም ላይ ሆኜ ስጾም እጸልይና እለምን ዘንድ ፊቴን ወደ ጌታ ወደ አምላክ አቀናሁ።(ዳን 9፡3)

የሚጾሙ ሰዎች በ 2 ይመደባሉ

  -  1.የጾም ጊዜያቸው እስኪፈጸም ድረስ ያለምንም እህል ውሃ በባዶ ሆድ የሚጦሙ ሲሆን
  -  2.ከስጋ ከቅቤ ከእንቁላልና ለስጋ ሃል ሰጪ ያልሆኑ ምግቦች እንዲሁም ከሚያሰክር መጠጥ በመከልከል እስከ ተወሰነ ሰዓት በባዶ ሆድ ቆይተው ሰዓታቸው ሲደርስ የሚመገቡ ናቸው፡፡

ያለ ምንም እህል ውሃ የሚጾሙ

  -   ሄደህ በሱሳ ያሉትን አይሁድ ሁሉ ሰብስብ፥ ለእኔም ጹሙ ሦስት ቀን ሌሊቱንና ቀኑን አትብሉም፥ አትጠጡም እኔና ደንገጥሮቼ ደግሞ እንዲሁ እንጾማለን(አስ 4፡16)

  -  የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ ለጾም አዋጅ ነገሩ፥ ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ።(ዮናስ 3፡1-10)
  -  ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ አለም የመጣውና በስጋ የተገለጠው ለ2 ዐበይት ነገሮች ነው 1ኛ ራሱን መስዋእት አድርጎ እኛን ለማዳን ሲሆን 2ኛው ለእኛ ለክርስቲያኖች ማድረግ የሚገባንን ነገር ሊያሳየንና አርአያ ሊሆነን ነው፡፡ ስለዚህ እየሱስ ክርስቶስ አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከጦመ በኋላ ተራበ።(ማቴ 4፡1-5)

ከሀይል ሰጪ ምግብ የሚጾሙ

  -  በዚያም ወራት እኔ ዳንኤል ሦስት ሳምንት ሙሉ ሳዝን ነበርሁ።ማለፊያ እንጀራም አልበላሁም፥ ሥጋና ጠጅም በአፌ አልገባም፥ ሦስቱም ሳምንት እስኪፈጸም ድረስ ዘይት አልተቀባሁም።(ዳን 10፡2-3)
  -  ጕልበቶቼ በጾም ደከሙ ሥጋዬም ቅቤ በማጣት ከሳ።(መዝ 108/109፡24)
ሌላው ጸሎትና ጾም አጋንንትን ማሸነፊያ እንደሆነ ጌታችን በ(ማቴ 17፡21) ተናግሯል፡፡

ሰባቱ(7) አጽዋማት

#1ኛ_ዐቢይ_ጾም(አርባ ጾም)

  -  ይህ ጾም በማቴ 4፡1 እና በሉቃ 4፡1 እንደተጻፈው ጌታ ራሱ የጾመው አርባ ጾም የሚባለው ነው፡፡ አርባ ጾም የተባለው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ ምንም ሳይቀምስ ለአርባ ቀንና አርባ ሌሊት ስለጾመው ስለጾመው እና ዲያብሎስን ድል እንዳረገው እኛም የሱን አርአያ በመከተል ነው የምንጾመው፡፡

#2ኛ_ጾመ_ሐዋርያት

  -  ከአብይ ጾም ቀጥሎ ሁለተኛው ጾም ጾመ ሐዋርያት(የሰኔ ጾም) ይባላል፡፡ ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ለስብከተ ወንጌል ከመሰማራታቸው በፊት የጾሙት ጾም ነው፡፡በዚህም የወንጌል ስራቸው ሰምሮላቸዋል፡፡ ስለዚህ አልጫ የነበረውን ዓለም በወንጌል ለማፋጠን ሐዋርያት ከጾም ከጸሎት ጋር የቱን ያህል እንደተጋደሉና መንፈስ ቅዱስም በሐዋርያት አድሮ የሰራውን ድንቅ ስራ ለማሰብ ነው፡፡

#3ኛ_ጾመ_ፍልሰታ

  - ይህ ጾም ከነሐሴ 1 ቀን እስከ ነሐሴ 15 ቀን የሚጾም ነው፡፡ ይህ ጾም የእመቤታችን መታሰቢያ ነው፡፡ይህም እመቤታችን ከሞት ተነስታ በክብር ወደ ገነት ስታርግ ሐዋርያው ቶማስ ከተልዕኮ ሲመለስ ተገናኝተው የከፈኗን ጨርቅ ለበረከት ሰጥታዋለች፡፡ሐዋርያት ይሄንን ዜና ከቶማስ በሰሙ ጊዜ እነሱም የቶማስ ያየውን ያዩ ዘንድ አምላካችንን ከ ነሐሴ 1-15 ቀን በጾም ለምነውት ክርስቶስም ለጥያቄያቸው መልስ ሰጥቷቸዋል፡፡ስለዚህ ይህን ድንቅ ነገር ለማሰብና ይህን ጾም ምክንያት በማድረግ የተሰወረው መንፈሳዊ ሚስጢር ሁሉ በቸርነቱ ለቤተክርስቲያን የተገለጠ እንዲሆን በማለት ምእመናን በየአመቱ ጾመ ፍልሰታን ይጾማሉ፡፡

#4ኛ_ጾመ_ነብያት(የገና ጾም)

  -  ይህ ጾም ከሕዳር 15 እስከ ታህሳስ 28 ያለው ጊዜ ሲሆን በዓሉ(ልደት) በዘመነ ዮሐንስ ታህሳስ 28 ቀን ይውላል፡፡ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ ከመገለጡና ሰው ከመሆኑ በፊት ነብያት የጌታን መምጣት በናፍቆት በጾምና በጸሎት ሲጠባበቁ ነበር፡፡ስለዚህ የነብያትን የጾም ድካም ለማሰብና አሁንም የአዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች ደግሞ የሚመጣ ክርስቶስን በናፍቆት ሲጠባበቁ እንደ ነብያት መንፈሰ ኃይልን ለመልበስ በእምነት ለመጽናት ኃጢያትን ለመዋጋት ሲባል ይህን ጾም ክርስቲያኖች ይጾሙታል፡፡

#5ኛ_ገሃድ

 ገሀድ ማለት ግልጥ የሆነ ለውጥ ማለት ነው፡፡ገሃድ የጥምቀት ብቻ ነው፡፡ ይኸውም ጥምቀት ረቡዕና ዓርብ ቀን በሚውልበት ጊዜ በኋላው የሚገኙ ማክሰኞና ሐሙስ የፍስክ ቀንነታቸው ወደ ጾምነት ተለውጦ ይጾማሉ፡፡ሆኖም ጥምቀት በሌላም ቀን ቢውል የዋዜማው ቀን ይጾማል፡፡

#6ኛ_ጾመ_ነነዌ

  -  የዚህ ጾም ጊዜ ሦስት(3) ቀን ብቻ ነው፡፡ቀኖቹም በየዓመቱ ሰኞ ማክሰኞና ረቡዕ ናቸው፡፡ የነነዌ ጾም በመባጃ ሐመር (አቆጣጠር) ከፍና ዝቅ ስለሚል አንድ ጊዜ በጥር አንድ ጊዜ በየካቲት ይሆናል፡፡የቤተ ክርስቲያን አባቶች ይህን ጾም የወሰኑት ልትጠፋ የነበረች ነነዌን በጾም ምክንያት እግዚአሔር ይቅር ስላላት ይህን አምላካዊ ይቅርታውን ለዘለዓለም ለማሰብና ዛሬም በዚህ ዓለም ከነነዌ የከፋ ርኩሰትና ኃጥያት ስላለ የነነዌን ሕዝብ ይቅር ያልክ አምካክ ዛሬም ይቅር በለን ለማለት ነው፡፡

#7ኛ_የረቡዕ_ዓርብ_ጾም

  -  ሰባተኛውና የመጨረሻው ጾም ረቡዕና ዓርብ ነው፡፡ አይሁድ ክርስቶስን በእንጨት ሰቅሎ ለመግደል የተፈራረሙበት ዕለት ረቡዕ ስለሆነ እና ዓርብ ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እኛ ይህ ነው የማይባል መከራ የተቀበለበት የተሰቀለበትና የሞተበት እኛን ያዳነበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡

@EOTC_Wengel
23 views17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 10:40:36 መዝሙር ዮም ንወድሳ

ከነሐሴ ፩ - ነሐሴ ፯

ዮም ንወድሳ ለማርያም በእንተ ዘተወልደ እምኔሃ መንክር ግርማ ኃይለ ልዑል ጸለላ ፆረቶ በከርሣ ውእቱኒ ቀደሳ (መ) እግዚኣ ለሰንበት ወአቡሃ ለምሕረት መንክር ግርማ ኃይለ ልዑል ጸለላ አማን መላእክት ይኬልልዋ

ትርጉም፦

ዛሬ (ኑ) ማርያምን እናመስግናት (ጌታችን) ከሷ ስለተወለደ በሚያስደንቅ ግርማ የልዑል ኃይል ጋረዳት በማኅፀኗ ወሰነችው እሱም አከበራት የሰንበት ጌታ የይቅርታ አባት በሚያስደንቅ ግርማ የልዑል ኃይል ጋረዳት በእውነት መላእክት ያመስግኗታል

ምስባክ፦

እምነ ጽዮን ይብል ሰብእ
ወብእሲ ተወልደ በውስቴታ
ወውእቱ ልዑል ሣረራ መዝ ፹፮፥፭

ትርጉም፦

ሰው እናታችን ጽዮን ይላል
በውስጧ ሰው ተወለደ
እርሱ ራሱ ልዑል መሠረታት

ምሥጢር፦

ሰው ሁሉ ቤተ መቅደስ እናታችን እግዚአብሔር አባታችን ይላል

ተወልደ በውስቴታ ተወልደ በውስቴታ ሲል ነው። ሕዝቅያስ በኢየሩሳሌም ተወልዶ በኢየሩሳሌም ይነግሣል አንድም ዘሩባቤል በባቢሎን ተወልዶ በኢየሩሳሌም ይነግሣል

ልዑል እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን በረድኤት አጸናት

አንድም በጸጋ ከሥላሴ የተወለደ ሰው ሁሉ እመቤታችን፤ ቤተ ክርስቲያን እናታችን እግዚአብሔር ወልድ አባታችን ይላል

ጌታ ከእመቤታችን ተፀነሰ ፅንሱን ልደት ልደቱን ፅንስ ይለዋልና አንድም በሥጋ ተወለደ አንድም ምእመናን ከቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ልደትን ተወለዱ

እግዚአብሔር እመቤታችንን በንጽሕና በቅድስና አጸናት ማለት እንድትችለው አደረጋት አንድም ቤተ ክርስቲያንን በደሙ አከበራት

የዕለቱ ወንጌል፦

ማቴ ፲፪፥፴፰ - ፍ

ቅዳሴ - ዘእግዝእትነ ማርያም
96 views07:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 16:58:38 ​ #ሰውን_ወዳጁና_ርህርሁ_እግዚአብሔር

ሰው ጨካኝ ሲሆን #እግዚአብሔር ግን ሁሉን የሚወድ ቸርና ርህርህ ነው፡፡ ለዚህም ነው ንጉስ ዳዊት ከሦስቱ ቅጣቶች መካከል አንዱን እንዲመርጥና አማራጩ ሲቀርብለት የተናገረው ቃል ድንቅ ነው፡፡ " ምህርቱ ብዙ ነውና በእግዚአብሔር እጅ እንውደቅ በሰው እጅ ግን አልውደቅ፡፡" 2ኛ ሳሙ 24 ፥ 14፡፡ ጻድቁ እዮብም በሦስቱ ባልደረበቹ እጅ በወደቀ ጊዜና እነርሱም እርሱን መውቀሳቸውን ባላቋረጡ ጊዜ እንዲህ ነበር ያላቸው ፡- "ነፍሴን የምትነዘንዙ በቃልስ የምታደቅቁኝ እስከ መቼ ነው? ይኸውም ስትሰድቡኝ አሥር ጊዜ ነው፡፡" ኢዮ 19 ፥ 2 - 3፡፡ #እግዚአብሔር ግን ከሰው በእጅጉ በተለየ መልኩ መሐሪና ርህርህ መሆኑን በሚከተሉት ውስጥ እንመለከታለን፡፡

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
166 views13:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 17:47:38 <እጅህ ላይ ባለው ነገር ከታመንህ እግዚአብሔር አምላክ በእጁ ውስጥ ያለውን ነገር ይሰጥሃል።>

በውስጥህ ያለውን አቅም መጠቀም ከቻልህ እግዚአብሔር የአንተ ያልሆነ ተጨማሪ አቅም ይሰጥሃል።

ከእግረኞች ጋር ሳትደክም እኩል መራመድና መቅደም ከቻልህ እግዚአብሔር ፈረስን ለውድድር ይሰጥሃል። ኤር. 12፥5

የሚታዩ ኃጢአቶችን ለመዋጋት ታምነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር የተሸሸጉና የማይታዩ ኃጢአቶችን ድል እንድትነሣ ይሾምሃል።

በሕፃንነትህ በልጅነትህ ለእግዚአብሔር የታመንህ ሆነህ ከተገኘህ እርሱ በወጣትነትህ በምታደርገው ውጊያ ውስጥ ታማኝነትን ያድልሃል።

ልያን ለመቀበል ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር ራሔልን ሚስት አድርገህ ታገባት ዘንድ ይሰጥሃል። ዘፍ. 29፥27

በሲና ምድረ በዳ ለመቀመጥ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር አምላክ የተስፋይቱን ምድር ከንዓንን ያወርስሃል።

በዚህ በተወሰነና አጭር ሕይወት ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር መጨረሻ የሌለውን ዘላለማዊ ሕይወት ያድልሃል።

ትልቁ ቁም ነገር በእጅህ ውስጥ የገባው ነገር ትንሽም ይሁን ጥቂት በእርሱ መታመን መቻልህ ነው።

ስለሆነም ባለህ አንድ መክሊት ታምነህ ስትገኝ እግዚአብሔር አምስት መክሊቶችን በአደራ ይሰጥሃል።

አንተ በሚታዩት ነገሮች ላይ ታማኝ ሆነህ ስትገኝ እርሱ በማይታዩት ነገሮች ላይ ይሾምሃል።

በመሆኑም ዓይን ያላየችውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልብ ያልታሰበውን መንግሥቱን ያወርስሃል። 1ኛ ቆሮ 2፥9

(አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ - መንፈሳዊው መንገድ መጽሐፍ አያሌው ዘኢየሱስ እንደተረጎመው።)

የሕይወት ፡ እናቱ ፡ ሆይ፤ ተቀዳሚ ፡ ተከታይ ፡ በሌለው ፡ በአንድ ፡ ልጅሽና ፡ በእኛ ፡ መካከል ፡ አስታርቂን።
224 views14:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 16:29:35 አንድ ሰው ‹‹እግዚአብሔር የለም›› ማለት ይችላል፤ ‹‹ኢትዮጵያ የለችም›› ማለት ግን አይችልም!

"... 16 ዓመት ሙሉ ትምህርት ላይ ቆይቶ ጭንቅላቱ ምንም ያልተዘራበት ሆኖ ይገኛል። ምሁራን ገለልተኛ መሆን የለባቸውም፤ ማንም ከአገር ጉዳይ ገለልተኛ ሊሆን አይችልም። አገር ሲኖር ነው ሁሉም ነገር የሚሆነው። አገር ከሌለ ማንም ሊኖር አይችልም።

ለማበድ እንኳን አገር ያስፈልጋል፤ በአገር ጉዳይ ምሁራንም ሆኑ የሃይማኖት አባቶች ገለልተኛ መሆን አይችሉም። በአገር ጉዳይ ላይ ማንም ነው መሥራት ያለበት፤ የአስተሳሰብ ቀረጻ ላይ መሰራት አለበት። አንድ ኢትዮጵያዊ አሜሪካ ውስጥ ቢያብድ ማደንዘዣ ተወግቶ ቦሌ ይጣላል። አንድ ሰው ‹‹እግዚአብሔር የለም›› ማለት ይችላል፤ ‹‹ኢትዮጵያ የለችም›› ማለት ግን አይችልም። እግዚአብሔር የለም ቢል የሚመጣውን ራሱ ይቀበላል፤ ኢትዮጵያ የለችም ካለ ግን ሀገሩን ለቆ ኬንያ መግባት አለበት።"


❖ መጋቢ ሐዲስ እሸቱ ❖
252 viewsedited  13:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 16:28:16
207 views13:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 13:17:30 አይ የዘመኑ መልካም ወጣት

ከይስሐቅ ከዳንኤል ከሰለስቱ ደቂቅ ከህጻኑ ቄርቆስ ወዲያ መልካም ወጣት የለም

ይስሐቅ በበጎ ምግባሩ በትሩፋት ያጌጠ አባቱን ያስደነቀ ዓለምን ያስደመመ በሃይማኖቱ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘ የመልካም ወጣት ምሳሌ ብቻ ሳይሆን ውበት እና ጌጥ ነው ስለይስሐቅ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል

ዘፍጥ 22:7: ይስሐቅም አባቱን አብርሃምን ተናገረው፦ አባቴ ሆይ፡ አለ። እርሱም፦ እነሆኝ፥ ልጄ፡ አለው። እሳቱና እንጨቱ ይኸው አለ፤ የመሥዋዕቱ በግ ግን ወዴት ነው? አለ።
8: አብርሃምም፦ ልጄ ሆይ፥ የመሥዋዕቱን በግ እግዚአብሔር ያዘጋጃል፡ አለው፤ ሁለቱም አብረው ሄዱ።
9: እግዚአብሔር ወዳለውም ቦታ ደረሱ፤ አብርሃምም በዚያ መሠዊያውን ሠራ፥ እንጨትንም ረበረበ፤ ልጁን ይስሐቅንም አስሮ በመሠዊያው በእንጨቱ ላይ አጋደመው።የሚለውን እንመልከት

አባቱ የዛሬው መስዋዕት አንተ ነህ ሲለው እንዴት ይሆናል ብሎ ያልጠየቀ ቢላዋ አንስቶ ከአንገቱ ላይ ሲያሳርፍበት አንገቱን አመቻችቶ የሰጠ ነው ታዲያ ከይስሐቅ በላይ መልካም ወጣትነት ከየት የመጣ ይሆን

ሰለስቱ ደቂቅን ዳንኤልን እንመልከት በዘመኑ የነበሩት ዮናታናውያን ለጣዖት እንዲሰግዱ ሲያስገዱዷቸው እኛስ ዓይን እያለው ለማያይ ጆሮ እያለው ለማይሰማ አንሰግድም በማለታቸው ስለ ሃይማኖታቸው ለእሳት የተሰጡ ለተራበ አንበሳ የተወረወሩ ናቸው
ስለእነሱ መጽሐፍ ምን ይላል

ዳን 1:17: ለእነዚህም ለአራቱ ብላቴኖች እግዚአብሔር በትምህርትና በጥበብ ሁሉ እውቀትንና ማስተዋልን ሰጣቸው፤ ዳንኤልም በራእይና በሕልም ሁሉ አስተዋይ ነበረ።ይላል

እግዚአብሔር በጥበብ በእውቀት በማስተዋል በትምህርት ያከበራቸው ናቸው ታዲያ ከእነሱ በላይ ምን አይነት መልካም ወጣት ተገኝቶ ይሆን የአሳማ ባህርይ ያለው 24 ሰዓት ከመብላት ውጭ የስነምግባር ምልክት ከሌለው እና ከተራ አጭበርባሪ ስር መልመጥመጡ ምን አይነት ህይወት ተፈልጎ ይሆን

ሕጻኑ ቂርቆስ እኮ በእናቱ እቅፍ እያለ ክርስቶስን በቃል ሳይሆን በህይወት በተግባር የሰበከ ሃይማኖቱ በእሳት ተፈትኖ ነጥሮ ወርቅነቱ የተረጋገጠ የመልካም ወጣት ውበት እና ጌጥ የሆነውን ቂርቆስን አልፎ ማንን ፍለጋ ነው ሩጫው

ኦርቶዶክስ እረ ተው ግድ የለህም ንቃ

ትናንትና በመልካም ወጣት ስም ምስኪን ድሆች ወንድሞቻችን በሚበላ በውራጅ አሮጌ ልብስ እያታለለ ላይህ ላይ ሲሳለቅብህ አብረህ ትስቃለህ ተተኪ ፓስተሮችን መስቀል አሳስሮ እስካሁን ሰንበት ተማሪ ነበርኩኝ እስካሁን አገልጋይ ነበርኩኝ እስካሁን ገዳም ለገዳም እሄድ ነበር ገና ዛሬ መፍትሔ አገኘን እያሉ ለምስክርነት ሲሯሯጡ የነበሩት እጩ ፓስተሮች ናቸዉ ኦርቶዶክሳውያን አይደሉም በዚህ ልክ ሲያጭበረብርህ እንዴት ትስቃለህ ሰው እንዴት ሌላውን ማዳን ቢያቅተው ራሱን አያድንም

አንድ ጥቅስ ሌጨምርላችሁና ልጨርስ

1 ጴጥ1:3: የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና።ይላል

የተተላልንበት የተሸጥንበት የተሞኘንበት የተጭበረበርንበት ጊዜ ይበቃል መልካምነትን ከይስሐቅ ሃይማኖትን ጥበብን እውቀትን ማስተዋልን ከዳንኤል ከሰለስቱ ደቂቅ ጥብዓትን ከህጻኑ ቂርቆስ እንማር እግዚአብሔር በቃችሁ ይበለን ማስተዋሉን ያድለን አሜን
228 views10:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 15:40:32 ✞ሥላሴ መታመኛዬ✞

ሥላሴ መታመኛዬ(፪)
አምላኬ መጠለያዬ(፪)
ጉልበቴ ነህ ማሸነፊያዬ
ሥላሴ መታመኛዬ

ጠፈሩም እርሱ መሠረቱም እርሱ
ፍጥረታት በሙሉ ስሙን አወድሱ
ሱራፌልን ልክህ ከንፈሮቼን ዳሰኝ
ለምፄን ተመልክተህ አምላክ አትጣለኝ
ለምፄን ተመልክተህ ጌታዬ አትጣለኝ
አዝ= = = = =
እንዴት ያለ አንደበት ስምህን ይጠራል
ግርማህን አይቼ ልቤ ተሸብሯል
ኦዝያን አለፈ ክፋቱ እጅግ በዝቶ
አምላኬን አየሁት በዙፋኑ ጸንቶ(፪)
አዝ= = = = =
አልአዛር የአንተ ነው መንገድ የወደቀው
ከእጅ ያላመለጠ ነዌ ባለፀጋው
ነግሥታትም የአንተ በሥልጣን ያሉት
ለስምህ ይንበርክከ ይህ ሁሉ ፍጥረረት(፪)
አዝ= = = = =
በድቅድቅ ጨለማ ተስፋ በሌለበት
ብርሃን ሆኖ አየሁት የጌታዬን ምሕረት
ኃይልን ማሸነፍን ጽናትንም ስጠኝ
ጠላት እንዳይጥለኝ ጸጋህን አልብሰኝ(፪)


ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
•➢ ሼር

መዝሙር
ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
338 views12:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 15:50:58
በዩቱዩብ አዳዲስ እና ቆየት ያሉ ዝማሬዎችን፣የገዳማት ጉብኝትን፣ስብከቶችን፣ምስባኮችን ሁሉን ባንድ ይፈልጋሉ። እንግዲያውስ #SUBSCRIB በማድረግ ይቀላቀሉን።



https://m.youtube.com/channel/UCW3Rd1J45aHyZTBLHX1K0bQ?sub_confirmation=1000
737 viewsedited  12:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ