Get Mystery Box with random crypto!

አይ የዘመኑ መልካም ወጣት ከይስሐቅ ከዳንኤል ከሰለስቱ ደቂቅ ከህጻኑ ቄርቆስ ወዲያ መልካም ወ | የበኵረ ሰባኪያን መምህር ምህረተአብ አሰፋ ትምህርቶች የማንቂያ ደወል 🔔

አይ የዘመኑ መልካም ወጣት

ከይስሐቅ ከዳንኤል ከሰለስቱ ደቂቅ ከህጻኑ ቄርቆስ ወዲያ መልካም ወጣት የለም

ይስሐቅ በበጎ ምግባሩ በትሩፋት ያጌጠ አባቱን ያስደነቀ ዓለምን ያስደመመ በሃይማኖቱ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘ የመልካም ወጣት ምሳሌ ብቻ ሳይሆን ውበት እና ጌጥ ነው ስለይስሐቅ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል

ዘፍጥ 22:7: ይስሐቅም አባቱን አብርሃምን ተናገረው፦ አባቴ ሆይ፡ አለ። እርሱም፦ እነሆኝ፥ ልጄ፡ አለው። እሳቱና እንጨቱ ይኸው አለ፤ የመሥዋዕቱ በግ ግን ወዴት ነው? አለ።
8: አብርሃምም፦ ልጄ ሆይ፥ የመሥዋዕቱን በግ እግዚአብሔር ያዘጋጃል፡ አለው፤ ሁለቱም አብረው ሄዱ።
9: እግዚአብሔር ወዳለውም ቦታ ደረሱ፤ አብርሃምም በዚያ መሠዊያውን ሠራ፥ እንጨትንም ረበረበ፤ ልጁን ይስሐቅንም አስሮ በመሠዊያው በእንጨቱ ላይ አጋደመው።የሚለውን እንመልከት

አባቱ የዛሬው መስዋዕት አንተ ነህ ሲለው እንዴት ይሆናል ብሎ ያልጠየቀ ቢላዋ አንስቶ ከአንገቱ ላይ ሲያሳርፍበት አንገቱን አመቻችቶ የሰጠ ነው ታዲያ ከይስሐቅ በላይ መልካም ወጣትነት ከየት የመጣ ይሆን

ሰለስቱ ደቂቅን ዳንኤልን እንመልከት በዘመኑ የነበሩት ዮናታናውያን ለጣዖት እንዲሰግዱ ሲያስገዱዷቸው እኛስ ዓይን እያለው ለማያይ ጆሮ እያለው ለማይሰማ አንሰግድም በማለታቸው ስለ ሃይማኖታቸው ለእሳት የተሰጡ ለተራበ አንበሳ የተወረወሩ ናቸው
ስለእነሱ መጽሐፍ ምን ይላል

ዳን 1:17: ለእነዚህም ለአራቱ ብላቴኖች እግዚአብሔር በትምህርትና በጥበብ ሁሉ እውቀትንና ማስተዋልን ሰጣቸው፤ ዳንኤልም በራእይና በሕልም ሁሉ አስተዋይ ነበረ።ይላል

እግዚአብሔር በጥበብ በእውቀት በማስተዋል በትምህርት ያከበራቸው ናቸው ታዲያ ከእነሱ በላይ ምን አይነት መልካም ወጣት ተገኝቶ ይሆን የአሳማ ባህርይ ያለው 24 ሰዓት ከመብላት ውጭ የስነምግባር ምልክት ከሌለው እና ከተራ አጭበርባሪ ስር መልመጥመጡ ምን አይነት ህይወት ተፈልጎ ይሆን

ሕጻኑ ቂርቆስ እኮ በእናቱ እቅፍ እያለ ክርስቶስን በቃል ሳይሆን በህይወት በተግባር የሰበከ ሃይማኖቱ በእሳት ተፈትኖ ነጥሮ ወርቅነቱ የተረጋገጠ የመልካም ወጣት ውበት እና ጌጥ የሆነውን ቂርቆስን አልፎ ማንን ፍለጋ ነው ሩጫው

ኦርቶዶክስ እረ ተው ግድ የለህም ንቃ

ትናንትና በመልካም ወጣት ስም ምስኪን ድሆች ወንድሞቻችን በሚበላ በውራጅ አሮጌ ልብስ እያታለለ ላይህ ላይ ሲሳለቅብህ አብረህ ትስቃለህ ተተኪ ፓስተሮችን መስቀል አሳስሮ እስካሁን ሰንበት ተማሪ ነበርኩኝ እስካሁን አገልጋይ ነበርኩኝ እስካሁን ገዳም ለገዳም እሄድ ነበር ገና ዛሬ መፍትሔ አገኘን እያሉ ለምስክርነት ሲሯሯጡ የነበሩት እጩ ፓስተሮች ናቸዉ ኦርቶዶክሳውያን አይደሉም በዚህ ልክ ሲያጭበረብርህ እንዴት ትስቃለህ ሰው እንዴት ሌላውን ማዳን ቢያቅተው ራሱን አያድንም

አንድ ጥቅስ ሌጨምርላችሁና ልጨርስ

1 ጴጥ1:3: የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና።ይላል

የተተላልንበት የተሸጥንበት የተሞኘንበት የተጭበረበርንበት ጊዜ ይበቃል መልካምነትን ከይስሐቅ ሃይማኖትን ጥበብን እውቀትን ማስተዋልን ከዳንኤል ከሰለስቱ ደቂቅ ጥብዓትን ከህጻኑ ቂርቆስ እንማር እግዚአብሔር በቃችሁ ይበለን ማስተዋሉን ያድለን አሜን