Get Mystery Box with random crypto!

ዕንቅዮጳግዮን

የቴሌግራም ቻናል አርማ enkeyopaghion — ዕንቅዮጳግዮን
የቴሌግራም ቻናል አርማ enkeyopaghion — ዕንቅዮጳግዮን
የሰርጥ አድራሻ: @enkeyopaghion
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 987
የሰርጥ መግለጫ

°°°°°°°°ዕንቅዮጳግዮን°°°°°°°°
ሀገራችን ኢትዮጵያ በስልጣኔ ፈር ቀዳጂ በጥበብ አስደናቂ በታሪክ አስደማሚ በእውቀት አነጋጋሪ ሀገር ናት ከኋላ የመጡት ኋላ ቀር ቢሉንም እኛ ግን ኋላ ቀር አይደለንም😎
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች🙏
ለመወያየት 👉 @Enkuyopaghion
ለአስተያየት @NYYC_bot

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-29 21:41:21 ስምፍስሐ ጽዮን በኋላ ተክለሃይማኖትየተወለዱበት ቀንታኅሣሥ ፳፬ ፲፩፻፺፯የትውልድ ቦታቡልጋየአባት ስምቅዱስ ጸጋዘአብየእናት ስምቅድስት እግዚእ ኃርያየአቡን ስያሜበእስክንድሪያው አቡነ ቄርሎስያረፉበትነሐሴ ፳፬[1]ንግሥነሐሴ ፳፬የሚከበሩት በወላጅ አባታቸው በካህኑ ቅዱስ ጸጋ ዘአብ ግብረ ዲቁናን ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ሲያጠኑ ቆይተው በአሥራ አምስት ዓመታቸው ከእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ቄርሎስ /ጌርሎስ/ ዲቁናን ተቀብለዋል፡፡ በዚህም ቅድስት ቤተክርስቲያንን በወጣትነት ዕድሜያቸው ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡
ከዕለታት በአንዱ ቀን ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከጓደኞቻቸው ጋር ወደ ዱር አደን ሄደው ሳለ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጾ ለኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ሐዲስ ሐዋርያ አድርጎ መረጣቸው። ስማቸውንም «ተክለ ኃሃይማኖት» አለው፡፡ ትርጓሜውም የኃይማኖት ፍሬ ማለት ነው፡፡
አባታችንም ሐዋርያዊ ጉዟቸውን ሲጀምሩ

«አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! የመንግሥተ ሰማያትን በር ትከፍትልኝ ዘንድ እነሆ ቤቴን እንደተከፈተ ተውኩልህ . . . ደካማ ለሆንኩ ለእኔ ያለ አንተ የሚያፀናኝ የለም። ለምፍገመገም ለእኔ ያለ አንተ ደጋፊ የለኝም። ለወደቅሁ ለእኔ ያለአንተ የሚያነሳኝ የለም። ለአዘንኩ ለእኔ ያለአንተ የሚያረጋጋኝ የለም። ለድሀው ለእኔ ያለ አንተ መጠጊያ የለኝም፡፡»
/ገድለ ተክለ ሃይማኖት ምዕ ፳፰ ቁ ፪ - ፫

ይህን ብለው ትሕትና በተሞላበትና በተሰበረ ልብ ወደ ፈጣሪያቸው ከለመኑ በኋላ በልዩ ልዩ የኢትዮጵያ ክፍለ ሀገራት ከኃጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ፣ ከክህደት ወደ ሃይማኖት መልሰዋል፡፡ በዚህም የተነሣ ለኢትዮጵያውያን ብርሃን ፀሐይ ተብለዋል፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ በዕብራውያን ክታቡ ስለ ቅዱሳን መንፈሳዊ ተጋድሎ ሲገልፅ:-

«እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሱ» /ዕብ. ምዕ ፲፩ ቁ ፴፫ / እንዳለ አባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖትም በመንፈሳዊ ተጋድሎ እንዲሁም በትህትና በተአምራት አላዊ የነበረውን ንጉሥ ሞቶሎሚን ወደ ክርስትና መልሰዋል፡፡

«ጽድቅን አደረጉ» እንዳለው አባታችን ወንጌልን በተጋድሎ ሕይወታቸው ተርጉመዋል፡፡

«የአንበሶችን አፍ ዘጉ» ምዕ ፲፩ ቁ ፴፫ /ምዕ ፲፩ ቁ ፴፬ /እንዳለው አባታችንም የአውሬውን ፥ የዘንዶውን ራስ ቀጥቅጠዋል።

«ከሰይፍ ስለት አመለጡ» እንዳለው አባታችንም ሞቶሎሚ ከወረወረው ጦር በተአምራት ድነዋል፡፡

«ከድካማቸው በረቱ» እንዳለው አባታችንም ያለ ዕረፍት በብዙ ተጋድሎ በጾምና በስግደት በብዙ መከራ በርትተዋል፡፡

ይህን ሁሉ ገድልና ትሩፋት እየፈጸሙ ዕረፍታቸውም በደረሰ ጊዜ ደቀመዝሙሮቻቸውን «ልጆቼ ሆይ ሁሉም መነኮስ መንግሥተ ሰማይ ይገባል ማለት አይደለም፤ ዓለምን በሚገባ የናቀ ብቻ ይገባል እንጂ መጀመሪያ የእግዚአብሔርን ጽድቁን ብቻ ፈልጉ፤ ጾምና ጸሎትን አዘውትሩ፤ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ፤ ትእዛዛቱንም አጥብቃችሁ ጠብቁ እያሉ ይመክሯቸው ነበር. . .» በኋላም «ለዓለም ጨው ለራሴ አልጫ ሆንኩ፤ ለዓለም ብርሃን ለራሴ ጨለማ ሆንኩ፣ ከእውነተኛው ዳኛ ከጌታዬ ፊት ስቆም ምን እመልሳለሁ?» እያሉ በፍጹም ትህትና እና በልዩ መንፈሳዊ ተመስጦ ይጸልዩ ነበር፡፡
በመጨረሻም አባታችን በነሐሴ ፳፬ ቀን ዕረፍታቸው ሆነ። በዚህም መሠረት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን ለእኚህ ዕረፍታቸው በእግዚአብሔር ፊት ለከበረና ብዙ ክብር ለተሰጣቸው ለጻድቁ ተክለ ሃይማኖት በየዓመቱ በነሐሴ ፳፬ ቀን በዓለ ዕረፍታቸውን በታላቅ ድምቀት ታከብራለች፡፡ እኛንም ከጻድቁ ረድኤት በረከት ይክፈለን፡፡
በበለጠ ለማወቅ ስለ አባታችን ሰፊውን ገድላቸውን ማንበብ እጅግ አርጎ ይጠቅማል ።
ደብረ አሚን ተክለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን የምክሖ ደናግል ማርያም ወጣቶች መንፈሳዊ ማኅበር አዲስ አበባ
54 views ፍቅርተ ስላሴ ስንት ሰዓት ነው ሰዓቱ ስንት ነው አሁንስ ስንት ሰዓት ነው ???, 18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 23:40:45 + ለምን ትቀናለህ? +

በዜና አበው ላይ አጋንንት አንድን መነኩሴ ለማሰናከል ሲማከሩ የሚያሳይ ታሪክ ተጽፎአል፡፡ መነኩሴው ለብዙ ዘመናት በተጋድሎ አሳልፎ ከብቃት የደረሰ መናኝ ነበር፡፡ የአጋንንቱ ጭፍራ በአለቃቸው ተመርተው ይህንን መነኩሴ ለማሳት ዘመቱ፡፡ ተራ በተራ ወደ እርሱ እየሔዱ የፈተና ወጥመዳቸውን ዘረጉበት፡፡ በዝሙት ሊፈትኑት ሞከሩ፡፡ አልተሳካም፡፡ በምግብም ሞከሩ ድል ነሣቸው፡፡ የሚያውቁትን የፈተና ስልት በተለያየ መንገድ እየተገለጹ አንዴ ሰው አንዴ መልአክ እየመሰሉ ሊጥሉት ቢሞክሩም አልቻሉም፡፡

አለቃቸው ይኼን ጊዜ በሉ እኔ የማደርገውን ተመልከቱ አላቸውና መንገደኛ መስሎ ወደ መነኩሴው ቀረበ፡፡ በጆሮው የሆነ ነግሮት ወዲያው ተሰናብቶት ወጣ፡፡ ይህንን ጊዜ አጋንንቱ እያዩት መነኩሴው መንፈሳዊ ገጽታው ተገፍፎ ፊቱ በቁጣና በንዴት ሲለዋወጥ ተመለከቱት፡፡ በዚህም ተደንቀው ምን ብለህ ነው ያሸነፍከው? ብለው አለቃቸውን ጠየቁት፡፡ እርሱም እንዲህ አላቸው፦ ‘ከአንተ ጋር ያደገውና ከአንተ ጋር የተማረው ጓደኛህ እኮ የእስክንድርያ ፓትርያርክ ሆኖ ተሾመ’ ብዬ ነገርኩትና ወጣሁ፡፡ አሁን ልቡ በቅናት እየነደደ ነው አላቸው፡፡ አጋንንቱ በደስታ ጨፈሩ፡፡

ሰይጣን የቅናትን ኃይል ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ መጽሐፈ ቅዳሴ ሞትን ሲገልጸው ‘በሰይጣን ቅናት ወደ ዓለም የገባ’ ይለዋል፡፡ ሰይጣን በሰው ልጅ ጸጋ ቀንቶ አዳምና ሔዋንን በፈጣሪያቸው እንዲቀኑና አምላክ መሆን እንዲመኙ አድርጎ ዓለምን ያመሰቃቀለ ነውና ይህንን መነኩሴ ለመጣል ለሺህ ዓመታት ብዙዎችን ወግቶ የጣለባትን ሰይፉን መዘዘበት፡፡ መነኩሴው የእኩያውን መሾም ሲሰማ ቅናቱን መቋቋም አቃተው::

ቅናት እጅግ ክፉ ኃጢአት ነው፡፡ ሰው ቢዘሙት ቢሰክር በሥጋው ነው:: ቅናት ግን በምታስተውል ነፍሱ ውስጥ የሚበቅል መርዝ ነው፡፡ ቃየልን በየዋህ ወንድሙ ላይ ያስጨከነው ቅናት ነበር፡፡ የአቤል ስኬት ለቃየል ውድቀት መስሎ ስለተሰማው በግፍ ሊገድለው በቃ፡፡

ዮሴፍ የለበሳት ቀለምዋ ብዙ የሆነ ጌጠኛ ቀሚስ በወንድሞቹ ዘንድ የመረረ ጥላቻን አትርፋለት ነበር፡፡ አንዱ አጊጦ አምሮ ሲታይ ቢሞትና ቢገላገሉት ደስ የሚላቸው የዮሴፍ ወንድሞች በየዘመኑ አሉ፡፡

ዮሴፍም አርፎ አልተቀመጠም፡፡ እየሔደ ሕልሙን ይነግራቸው ነበር፡፡ ስለ ሕልሙም የበለጠ ጠሉት ይላል፡፡ ወዳጄ ሕልምህን ዝም ብለህ ለሰዎች አትዝራ፡፡ ሕልም ስልህ ተኝተህ የምታየውን ብቻ ማለቴ አይደለም፡፡ ራእይህን ፣ ተስፋህን ዕቅድህን ሲያውቁ የሚንገበገቡ የዮሴፍ ወንድሞች በየዘመኑ አሉ፡፡ ፍቺው ባይገባቸውም ባልተፈታ ሕልም ይጠሉሃል፡፡ ምንም ነገር ሳታደርግ እንኳን "ለምን አለምከው?" ብለው ጥርስ ይነክሱብሃል፡፡ ዮሴፍ ግን ይኼ ስላልገባው ነገራቸው፡፡ ወዳጄ አንተም ሕልምህን እንደ ዮሴፍ በየዋህነት የምትዘራ ከሆንህ እንግዲህ የዮሴፍ አምላክ ይጠብቅህ፡፡

ቅናት እጅግ ከባድ ነው፡፡ እረኛው ዳዊት ጎልያድን የገደለ ዕለት የተዘፈነለት መዘዘኛ ዘፈንም ነበረ፡፡ ‘ሳኦል ሺህ ገደለ ዳዊት እልፍ ገደለ’ ብለው ዘፈኑለት፡፡ ይህች ዘፈን በሳኦል ጆሮ ስትደርስ ዳዊት ላይ ብዙ ጦር አስወረወረች፡፡ ሳኦሎች ሌላ ሰው ከእነርሱ በላይ ሲመሰገን የሰሙ ዕለት በቅናት ታውረው ገበታ ላይ ሳይቀር ሰይፍ ይመዛሉ፡፡

የጠፋው ልጅ ወንድምን አስበው፡፡ (ሉቃ 15:20) ወንድሙ ከጠፋበት ተመልሶ ደስታ ሲደረግ እርሱ ግን ከፍቶት ውጪ ቁጭ አለ፡፡ ወዳጄ ቅናት ከቤተ ክርስቲያንና ከእግዚአብሔር መንግሥት ያስወጣል፡፡ የሌላው ስኬት ካበሳጨህ እንደጠፋው ልጅ ወንድም ውጪ ቁጭ ብለህ አፈር እየጫርክ ‘እምቢየው አልገባም’ እያልክ እያልጎመጎምክ ትቀራለህ፡፡

ክርስቶስ ላይ አይሁድ ያቀረቡት ትችት ሁሉ ለሕግ ከመቆርቆር ሳይሆን ከቅናት ነበር፡፡ ጲላጦስ እንኳን ‘በቅናት አሳልፈው እንደሠጡት ያውቅ ነበር’ ይላል፡፡ አንዳንዴ ሰዎች ቅናታቸውን በሌላ ነገር እንደ አይሁድ ሸፍነው ትችት ያቀርባሉ፡፡ ለእግዚአብሔር ሕግ እንደተቆረቆሩ ፣ ለሥርዓቱ እንዳዘኑ መስለው ውስጣቸው ያለውን ቅናትና ጥላቻ ያንጸባርቃሉ፡፡

የሰንበት መሻር ፣ ለቄሣር ግብር መከፈል ፣ የመቅደሱ በሦስት ቀን ፈርሶ መሠራት እንዳንገበገባቸው እርር እያሉ ቢናገሩም እውነታው ግን ቅናት ነው፡፡ ‘የቤትህ ቅናት በላኝ’ እንዳለው ጌታ በየዘመኑ የሰዎች ቅናት ብዙ ንጹሐንን ትበላለች፡፡

ወዳጄ በሌላው ትቀና እንደሆን አሁኑኑ ከዚህ ውስጥን በልቶ ከሚጨርስ ካንሰር ራስህን አድን፡፡

ራስህን ከሌሎች ጋር አታወዳድር፡፡ በምድር ላይ እግዚአብሔር የፈጠረው አንተን የሚመስል ሌላ ሰው የለም፡፡ ካንተ ቀድሞም በትክክል አንተን የሆነ ሰው አልተፈጠረም ለወደፊትም አይፈጠርም፡፡ እግዚአብሔር ቀድሞ ያልሠራው ደግሞም የማይሠራው ምርጥ ዕቃው ነህና ራስህን ከሌላ ጋር አታወዳድር፡፡

ለአንተ ብቻ የሠጠው ጸጋ አለና ሌሎችን መመልከት ትተህ ውስጥህ ያለውን ውድ ማንነት ቆፍረህ አውጣ፡፡ ያንተ ሕይወት ቁልፍ የተቀበረው አንተው ውስጥ ነው፡፡ ሌሎችን ረስተህ ወደ ራስህ ጠልቀህ ግባ፡፡ መብለጥ ከፈለግህም አሁን ያለውን ራስህን ብለጠውና ሌላ ትልቅ አንተን ሁን፡፡

በቅናት እንዳትቃጠል ሌሎችን ሰዎችንም ውደዳቸው፡፡ ከወደድሃቸው ‘ፍቅር አይቀናም’ና የእነርሱ ስኬት የደስታህ ምንጭ ይሆናል፡፡ የቅናት ስሜት ሲሰማህም ‘ቀናተኛ ልቤን ፈውስልኝ’ ብለህ ለምነው፡፡

‘በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን’ ሮሜ 13፡13

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
አለታ ወንዶ ኢትዮጵያ
ጥር 5 2013 ዓ.ም.

መነሻ ሃሳብ:- የአንድ በቅናት ጦስ ሊያበሩ ሲችሉ ብዙ ዋጋ የከፈሉ ቤተሰቦች ታሪክ

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ!

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
115 views ፍቅርተ ስላሴ ስንት ሰዓት ነው ሰዓቱ ስንት ነው አሁንስ ስንት ሰዓት ነው ???, edited  20:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 10:04:40 ​​​​እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ጾመ ፍልሰታ ፍቺ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ! በየትም ዓለም የምትኖሩ የክርስትና እምነት ተከታዮች ሰላምታችን ይድረሳችሁ፡፡

የእመቤታችን ትንሣኤና ዕርገት

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምድር የኖረችው ስልሳ አራት ዓመት ነው፡፡ እነዚህ ዓመታት ሲተነተኑ ሦስት ዓመት በወላጆቿ ሐናና ኢያቄም ቤት፣ ዐሥራ ሁለት ዓመት በቤተ መቅደስ፣ ሠላሣ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አሥራ አምስት ዓመት ከሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ጋር ነው፡፡

ያረፈችውም ጥር 21 ቀን በ50 ዓ.ም ነው፡፡ ባረፈችበት ወቅት ቅዱሳን ሐዋርያት ክቡር ሥጋዋን ለማሳረፍ ወደ ጌቴ ሴማኒ ሲሔዱ አይሁድ "ቀድሞ ልጇ በሦስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ ተነሣ፤ በአርባኛውም ቀን ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ተመልሶም ይህን ዓለምን ለማሳለፍ ይመጣል እያሉ በማስተማር ሕዝባችንን ወስደውብናል፡፡ አሁን ደግሞ ዝም ብለን ብንተዋት እርሷም እንደ ልጇ ተነሳች እያሉ በማስተማር ሊያውኩን አይደለምን? ኑ! ተሰብስበን በእሳት እናቃጥላት" ብለው ክፉ ምክር ተማከሩ፡፡

ከመካከላቸውም ብርቱ ሰው የሆነው #ታውፋንያ የተባለ ቅድስት ሥጋዋን ከሐዋርያት ነጥቆ ለማስቀረት ክቡር ሥጋዋ ያለበትን የአልጋ ሸንኮር ሲይዝ በመልአከ እግዚአብሔር እጁ ተቆርጣ ከአልጋው ላይ ተንጠልጥላ ቀረች፤ ከዚህ የጥፋቱ ሥራው ተምሮ እመቤታችንን በመለመኑ እመቤታችን የተቆረጠች እጁን መልሳለታለች፡፡

ከዚህ በኋላ መልአከ እግዚአብሔር የእመቤታችንን የተቀደሰ ሥጋዋን ጌታችን ይወደው የነበረ ተብሎ የተነገረለት ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስን ይዞ በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር አስቀመጠው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም የሆነውን ሁሉ ለወንድሞቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ነገራቸው፡፡ እነሱም የእመቤታችን ሥጋ በክብር ለማሳረፍ ካላቸው ጉጉት የተነሣ ከነሐሴ 1 ቀን ጀምሮ ሱባኤ ገቡ፡፡

ከሁለተኛ ሱባኤ ቆይታቸው በኋላ በአሥራ አራተኛ ቀናቸው ጌታችን የእመቤታችንን ትኩስ ሥጋ ሰጣቸው፡፡ ሐዋርያትም በዝማሬና በታላቅ ምስጋና በጌቴ ሴማኔ ቀበሯት፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ‹‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት› › ተብሎ ትንቢት የተናገረውን ሲተረጉሙት ‹‹ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ሆይ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት የምታሳርፈው የመቅደስህ ታቦት የሆነችውን ድንግል ማርያምን ይዘህ ተነሥ›› ብለው ያመሰጥሩታል፡፡ /መዝ. 131፥8/፡፡

የእመቤታችንን ቅድስት ሥጋዋን ሐዋርያት ሲቀብሯት በሀገረ ስብከቱ ሕንድ የነበረው ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ ሲመለስ እመቤታችን ስታርግ ያገኛታል ለምልክት እንዲሆነው ሰበኗን (የመግነዟን ጨርቅ) ተቀብሏት ይለያያሉ፡፡ ለወንድሞቹ ሐዋርያት ያየውን ይነግራቸዋል፡፡

ለበረከት የሰጠችውንም ሰበን ያካፍላቸዋል፤ ሐዋርያት ‹ ‹ዕርገቷን እንዴት እሱ ብቻ ተመልክቶ ለምን እኛ ይቀርብናል› › ብለው በዓመቱ ነሐሴ አንድ ቀን ሱባኤ ገቡ፡፡ ነሐሴ 16 ቀን የልባቸው መሻት ተፈጸመላቸው፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እመቤታችንን መንበር፣ ቅዱስ ጴጥሮስን ንፍቀ (ረዳት) ቄስ፣ ቀዳሚ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስን ገባሬ ሰናይ (ዋና ዲያቆን) አድርጎ ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው፡፡

በትኅትና የያዙት ሱባኤም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ዕርገቷን ለማየት አበቃቸው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ይህን መሠረት አድርጋ ከነሐሴ 1-16 ጾመ ፍልሰታ በማለት ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ አድርገን እንድንጠቀምበት ሥርዐት ሠራችልን፡፡

በነቢያና በሐዋርያት መሠረት ላይ የታነጽን ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች በየዓመቱ ይህን ጾም በሱባኤ በማሳለፍ ከእመቤታችን ጸጋና በረከት ተሳታፊዎች እንሆናለን፤ ሆነናልም፡፡ የዓመት ሰዎች ይበለን፡፡

ከእመቤታችን ረድኤት በረከት ተቋዳሾች ያድርገን፡፡
                    


153 views ፍቅርተ ስላሴ ስንት ሰዓት ነው ሰዓቱ ስንት ነው አሁንስ ስንት ሰዓት ነው ???, 07:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 22:25:49 ተስፋ መቁረጥና ስንፍና እጅግ ክፉዎች ናቸውና ከእነዚህ እንራቅ፡፡

“ክፋታቸውስ እንደምን ያለ ነው?” ያልከኝ እንደ ኾነም እንዲህ ብዬ እመልስልሃለሁ፡- ተስፋ መቁረጥ የወደቀው ሰው እንደ ገና እንዲነሣ አይፈቅድለትም፤ ስንፍናም የቆመው ሰው እንዲወድቅ ያደርጓል፡፡ ስንፍና ገንዘብ ያደረግናቸውን መልካም ነገሮች ከማሳጣቱም በላይ ሊመጡ ካሉ ክፉ ነገሮች እንዳንጠበቅ ያደርገናል፡፡ ስንፍና ከሰማያትም ቢኾን ይጥለናል፤ ቀቢጸ ተስፋም ወደ ክፋት ዐዘቅት እንድንሰጥም ያደርገናል፡፡ በእውነት በቀቢጸ ተስፋ ካልተያዝን ከጽኑ ክፋት መመለስ ይቻለናል፡፡

እነዚህ ኹለቱ ምን ያህል ኃይል እንዳላቸው ይበልጥ ታውቅ ትረዳ ዘንድ ምሳሌ ጠቅሼ ልንገርህን? መልካም! ዲያብሎስ መጀመሪያ ላይ መልካም ነበር፤ ከስንፍናና ከቀቢጸ ተስፋ የተነሣ ግን እንደ ገና የማይነሣ ኾኖ ወደ ክፋት ወደቀ፡፡ ዲያብሎስ ጥንቱ መልካም እንደ ነበረ ሲናገር መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ያለውን አድምጥ፡- “ሰይጣን እንደ መብረቅ ከሰማይ ሲወድቅ አየሁ” (ሉቃ.10፡18)፡፡ መብረቅ የሚለው አገላለጽ ዲያብሎስ ከመውደቁ በፊት ምን ያህል ብሩህ ሕይወት እንደ ነበረውና በምን ያህል ቅጽበት እንደ ወደቀ የሚያመለክት ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ ተሳዳቢ፣ አሳዳጅና ነውርን የማያውቅ ሰው ነበር (1ኛ ጢሞ.1፡13)፡፡ ነገር ግን ቀናተኛ ስለ ነበርና ተስፋ ስላልቈረጠ ተነሥቶ መላእክትን የሚተካከል ኾነ፡፡ ይሁዳ ሐዋርያ ነበር፤ ነገር ግን በስንፍና ምክንያት ጌታውን አሳልፎ ሰጠ፡፡ ፈያታዊ ዘየማን ደግሞ እንደዚያ እጅግ ክፉ የነበረ ሰው ቢኾንም ቅሉ ተስፋ ስላልቈረጠ ኹሉንም ቀድሞ ገነት ገባ፡፡ ፈሪሳዊው ሰው ራሱን ከፍ ከፍ ያደርግ ስለ ነበር ከምግባር ማማ ላይ ወደቀ፡፡ ቀራጩ ግን ተስፋ ስላልቈረጠ ከፈሪሳዊውም በልጦ ወደ ምግባር ሰገነት ወጣ፡፡
ስለዚህ ይህን ዐውቀን ዘወትር ከስንፍናና ተስፋ ከመቁረጥ እንራቅ!

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
122 views ፍቅርተ ስላሴ ስንት ሰዓት ነው ሰዓቱ ስንት ነው አሁንስ ስንት ሰዓት ነው ???, 19:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 06:47:01 ትሑትና ትዕግሥተኛ ሁን

በምድረ ገጽ ላይ ከነበሩት ሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ ትሑት የነበረውን ነቢዩን ሙሴን ምሰል “ሙሴም በምድር ላይ ካሉት ሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ ትሑት ሰው ነበረ።” ዘኁ 12፥3።

ሁል ጊዜ መሐሪ እና ይቅር ባይ ለመሆን ሞክር ሐዋርያው “ለማንም ስለ ክፉ ፋንታ ክፉን አትመልሱ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ... ተወዳጆች ሆይ ራሳችሁ አትበቀሉ ለቁጣ ፋንታ ስጡ እንጂ ...” ሮሜ 12፥17-19 ብሏልና። እንዲሁም ቁጣን ጊዜያዊ ስሜትን እና ንዴትን እንድናስወግድ “ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ” ሮሜ 12፥21 በማለት ይጠይቀናል።

በእርግጥ መታገስ የሚችል ሰው ዕድለኛ ሲሆን ይህንን የማይችል ግን ደካማ ነው። ለዚህ ነው ሐዋርያውም “እኛም ኃይለኞች የሆንን የደካሞችን ድካም እንድንሸከም ራሳችንንም ደስ እንዳናሰኝ ይገባናል።” ሮሜ 15፥1 ያለው።

ሌሎች አንተ እንዳሰብካቸው ፍጹም የሚስማሙ እንዲሆኑ አትፈልግ። ነገር ግን መሆን እንዳለባቸው ሳይሆን እንደሆኑት አድርገህ ተቀበላቸው ሁላችንም ተፈጥሮን እንደራሷ አድርገን ተቀብለናል። ወቅቶችን ዝናባማ፤ ማዕበላማም ይሁን ሞቃታማ ተፈጥሮ ራሱን እንዲለውጥ ሳንጠይቅ ተቀብለነዋል። ከሰዎችም ጋርም ልክ እንዲሁ እናድርግ።

ሰዎች ሁሉ ጻድቅና መልካም አይደሉም። ብዙዎቹ ድክመቶች ወይም የተወሰኑት ባሕርያቸውን ተቆጣጣሪ የሆነ አመሎች አሉባቸው። ሰዎች የተለያዩ ዓይነቶች ናቸው። ከእነዚህ አንዳንዶች ሁከተኞች ናቸው። ስለዚህ በጠባያቸው ተጽዕኖ እንደማይደረግበት ተመልካች እንሁን። ባሕሪያቸውንም በጥበብ እንቀበላቸው።
193 views ፍቅርተ ስላሴ ስንት ሰዓት ነው ሰዓቱ ስንት ነው አሁንስ ስንት ሰዓት ነው ???, 03:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 19:37:04 ለኵነኔ የማያበቃ የኃጢአት ትንሽ ባይኖረውም: መሠረትነታቸውን ለመናገር ያህል አበው ሦስቱ አርእስተ ኃጣውኡ (የኃጢአት ታላላቆች) ሲሉ የሚጠሯቸው አበይት የሰይጣን ፈተናዎች አሉ:: ስስት፣ ትዕቢትና ምቾት (ፍቅረ ንዋይ) ይባላሉ:: ዓይነተ ብዙ የዲያቢሎስ ውጊያዎችን ሰብስበን ብንደምር ብንቀንስ ከነዚህ ከሦስቱ አይወጡም:: በዚህ የተነሣ በነዚህ ፈተናዎች ድል የተነሣ: የተቀሩትን ማሸነፍ እንደማይቻለው ይነገራል:: ስግብግብነት ያስቸገረው፣ ትሕትና የጎደለው፣ ድሎት ደስ የሚለው ሌሎች ጥፋቶችን ማጥፋት አይሆንለትም ነው ብሂሉ:: ለምሳሌ ዝሙትና ቅንጦት ይዋደዳሉ፤ የስንፍና እጮኛ ሆድ ናት፤ ዕብሪትና ንስሐ ተግባብተው አያውቁም:: ... አንቺ ማስተዋል የሚሉሽ ሆይ፥ አንዴ ነይማ: እዚህ ትፈለጊያለሽ!
274 views ፍቅርተ ስላሴ ስንት ሰዓት ነው ሰዓቱ ስንት ነው አሁንስ ስንት ሰዓት ነው ???, 16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 21:57:17 #እኛ_እያለን_ቤተክርስቲያን_አትቸገርም!"

#ሥዕለት_ሰሚው_ሽማጎ_ቅዱስ_ጊዮርጊስ
•••
ውድ ኦርቶዶክሳውያን ቤተሰቦቼ ሰላም ለእናንተ ይሁን ? እንዴት ሰነበታችሁ? እባካችሁን ከላይ ያሉትን ቪዲዮዎች በደንብ አዳምጧቸው። የሽማጎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ሊዘጋ ነው። አገልግሎት ሊቋረጥ ነው። ቤተክርስቲያን ልትዘጋ ነው።
#እኛ_እያለን_ቤተክርስቲያን_አትቸገርም!" በሚል ንቁ ተሳትፎ እርዳታችንን ማድረግ ይጠበቅብናል!

ሙሉ ችግራቸውን ከ



እና


ከዚህ Link ላይ ገብታችሁ ማየት ማዳመጥ ትችላላችሁ። የደብሩ አስተዳዳሪ እና አገልጋይ ከሆኑት ከቀሲስ መሐሪ ይመር ጋር ቆይታ አድርገናል። የተጋረጠባቸውን ችግር ከአንደበታቸው ሰምታችሁ የበኩላችሁን አድርጉ። #ለኮንሰርት #ለሙዚቃ ድግስ #ለባዛር #ለኤክስፖ #ለሲኒማ #ለቲያትር ..... ብር ክፍላችሁ አታውቁምን? ታዲያ ለሰማዕቱ ቤት ማድረግ እንዴት አንችልም? ይህንን መልዕክት ከለጠፍኩበት ቀን እስካሁን ድረስ ብዙ የእርዳታ ጎርፍ መፍሰስ ነበረበት። #ከአንድ ብር ጀምሮ ይቻላል። የግድ #መቶ ብር ያለ የለም። የተቻላችሁን ብቻ ነው። ሃሳብም እርዳታ ነው። በዋናነት ግን #ለብዙኃኑ እንዲደርስ Share አድርጉት። ዋጋችሁን ከሰው ሳይሆን ከእግዚአብሔር ዘንድ ትቀበላላችሁ። #ዳዊት የእግዚአብሔር ታቦት በድንኳን ሆኖ ከቤቴ አልተኛም ብሏል። በዚህም ጸጋ በዲበ ጸጋ አግኝቷል። ለጠቢብ የተናገርኩት ሁሉ በቂ ነው። ፍንጭ ከሰጠኋችሁ በቂ ነው። ማመን እና ማወቅ ያለባችሁ ነገር ቢኖር #መልዕክቱ የእኔ አይደለም። አስተባባሪውም እኔ አይደለሁም። ራሱ ሰማዕቱ #ቅዱስ ጊዮርጊስ ነው። መልዕክቱም አስተባባሪውም ራሱ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነው።
•••

#እኛ_እያለን_ቤተክርስቲያን_አትቸገርም!"
169 viewsÑåŧŧ¥ Ć Ñ¥, 18:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 14:02:14 መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ።” ምሳ. 31፡29

ክርስቶስን ያከበሩ፤ መንገዱን የተከተሉ ብዙ ሴቶች አሉ፤ እውነትን የመሰከሩ፤ ስለ ቃሉ የኖሩ ብዙ ሴቶች አሉ፤ መስዋዕትነትን የከፈሉ በሰማዕትነት ያለፉ ብዙ ሴቶች አሉ፤ ታላላቅ የምድር ነገስታትን፤ ታላላቅ ነቢያትን የወለዱ ብዙ ሴቶች አሉ፤ ከነዚህ ሁሉ ግን አንቺ ትበልጫለሽ።

ቅድስት ድንግል ሆይ አንቺ እኮ ሰማይ ዙፋኑ ምድር መረገጫው የሆነ፤ ድንቅ መካር ኃያል አምላክ የሰላም አለቃ፤ ሁሉ በእርሱ የሆነ ከሆነውም አንዳችም እንኳን ያለርሱ ያልሆነ፤ ዓለምን ሁሉ ከሞት ወደ ሕይወት የመለሰ፤ መንበሩን የሚሸከሙ ኪሩቤልና ሱራፌል የሚንቀጠቀጡለት፤ የሁሉ ፈጣሪ፤ የሁሉ አምላክ የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ እናት ነሽ። በፊትም አሁንም ወደፊትም ካንቺ በቀር ፈጣሪዋን ልጄ ብላ የምትጠራ ሴት አልነበረችም፣ የለችም፣ አትኖርምም፤ ክርስቶስም እናቴ ብሎ የሚጠራት ብቸኛዋ ሴት አንቺ ነሽ በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ።

እናት ስትሆኝ ድንግል፤ ድንግል ስትሆኝ እናት በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ። ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ብሎ የሚጠራሽ ብቸኛዋ ሴት በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ። እግዚአብሔር መርጦና ጠብቆ ያስቀረሽ ዘር በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ። ለዓለም ሁሉ ድህነት ምልክት የሆንሽ በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ።

እናቴ ሆይ እንግዲህ እኔ ምን ልናገር? ሺህ ቃላትን ብደረድር ያንቺን ክብር ልገልፀውስ እንደምን እችላለው? አዎ አሁንም እላለሁ “መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ።” ምሳ. 31፡29

የቅድስት ድንግል ማርያም በረከቷ በሁላችን ላይ ይደር፤ ምልጃ ቃል ኪዳኗ ይጠብቀን። አሜን!!!
213 views ፍቅርተ ስላሴ ስንት ሰዓት ነው ሰዓቱ ስንት ነው አሁንስ ስንት ሰዓት ነው ???, 11:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 06:44:03 አንድ ሰው "ይሄ ባህሪዬ ነው ምንም ማድረግ አልችልም የሚለውን ንግግር ትክክል ላልሆነ ስራ ማስተባበያነት ሆኖ ሲቀርብ ምን ያህል ጊዜ ሰምቶት ይሆን?ይሄ ምንንያሳያል?ይሄን የተናገረው ሰው በጉዳዩ ላይ ምንም ኃላፊነት እንደሌለውና ባህሪው መቀየር እንደማይችል ያመላክታል።

እስከ ሕይወቱ ፍፃሜ ድረስ ይሄን የተሳሳተ ነገር እያደረገ መቀጠል እንዳለበትና እንደዚህ ሆኖ እንደ ተፈጠረ ያምናል ወይም አባቱ ወይም አያቱ እንደ እንደዚህ እንደነበሩ እነሱ እንደዚህ ባይሆኑም ከሶስት ወይም አራት መቶ ዓመታት በፊት በቤተሰባቸው የዘር ሀረግ ውስጥ አንዳቸው የዚህ ችግር ተጠቂ እንደነበሩና እሱም እራሱ እንደዛው ሆኖ መቅረት እንዳለበት ያስባል።

አንደዚህ አይነቱ እምነት ለሁሉም መሻሻሎች ወደ መልካምነት ለሚደረጉ ጉዞዎችና ለሁሉም የባህሪ ዕድገቶችና የሕይወትን ታላቅነት ለማስፋፋት እንቅፋት ስለሆነ ብቻ መነቀል መጥፋትና መወገድ ይኖርበታል።

ባህሪ ወጥ አይደለም እርግጥ በተፈጥሮ ውስጥ ካሉ በጣም ተለዋዋጭ ከሆኑት ነገሮች መካከል አንደኛው ነው።ሆን ተብሎ በፈቃደኝነት በተደረገ ነገር ካልተለወጠ ያለማቋረጥ በተደጋጋሚ በሁኔታዎች በሚደርስበት ጫና በመለወጥ ይስተካከላል።ባህሪ አንድ ሰው አንድን ነገር "ምንም ማድረግ አልችልም" በሚል የእምቢተኝነት እምነት ያለማቋረጥ በመተግበር እንዲፀና ካላደረገው በቀር ቋሚ ሊሆን አይችልም።

አንድ ሰው ይሄን እምነቱን ሊያስወግድ መለወጥ እንደሚችል ያውቃል።ከዚህ በተጨማሪም ዕውቀትና ፈቃድ ባህሪን እስከ ተፈለገው ድረስ መገንባት እንደሚችሉና አንድ ሰው ቅን ከሆነ በፍጥነት ባህሪውን መለወጥ እንደሚችል ጠንቅቆ ያውቃል።

ባህሪ አንድን ነገር ደጋግሞ በመስራት የሚፈጠር ዐመል እንጂ ሌላ ምንድነው?አንድን ነገር ደጋግመህ መስራትህን አቁም ወዲያውኑ ያ ባህሪ ይለወጣል።

ምንም እንኳ አብሮ የነበረን ሀሳብ ወይም ድርጊት መለወጥ መጀመሪያ ላይ በጣም ከባድ ቢሆንም ነገር ግን ጥረት በተደረገ ቁጥር አስቸጋሪነቱ እየቀነሰ ይመጣና መጨረሻ ላይ ይጠፋል።

ከዚያም አዲስና መልካም አመል ይፈጠርና ባህሪም ከመጥፎነት ወደ ጥሩነት በመለወጥ የተከበረ ይሆናል።አዕምሮም ከስቃይ ነፃ በማውጣት ወደ ደስታ ከፍ ይላል።

ማንም ሰው ህዘንን ለሚፈጥርበትና ራሱ አላስፈላጊ እንደሆነ ለሚቆጥረው ባህሪ ተገዥ መሆን አያስፈልገውም።መተውና ከባርነት ነፃ መውጣት ይችላል።ራሱን ማድረግና ነፃ ማውጣት ይችላል?

@Enkeyopaghion
@Enkeyopaghion
203 views ፍቅርተ ስላሴ ስንት ሰዓት ነው ሰዓቱ ስንት ነው አሁንስ ስንት ሰዓት ነው ???, 03:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 20:13:21 ድነኀል ወይስ አልዳንክም?

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ በአንድ መጽሐፋቸዉ እንዲህ ይላሉ። አንድ ወጣት ልጅ እንዲህ ብሎ ጠይቆኛል “አንድ ሰው ድነኀል ወይስ አልዳንኽም?” ብሎ ቢጠይቀኝ መልሴ ምንድ ነው?

መጀመሪያ ይሄ ሰዉ እዉነተኛ ኦርቶዶክስ እንዳልሆነ ማወቅ አለብህ። በእርግጠኝነት ይሄ ሰዉ ፕሮቴስታንት ነዉ ወይንም ቢያንስ በፕሮቴስታንታዊ ባህል ውስጥ ነዉ የሚኖረዉ፣ ባህሉም የፕሮቴስታንት ነው። ከዚህ በፊት የተቀበልካቸዉን ምስጢራትንና ጥምቀትን እንደ ምንም ቆጥሮ፣ በሃይማኖትህ ላይ ጥርጥር ለመሙላት በመሞከር፣ ባለፈዉ የሕይወት ዘመንህ ሁሉ አሕዛብ እንደነበርክ አድርጎ እንደ ገና እመንና ዳን ሊልህ ነው። ይሄ ሰዉ በፍጹም ኦርቶዶክስ ሊሆን አይችልም አነጋገሩም ይገልጠዋል።

ለማንኛዉም እንዲህ ብለህ ልትመልስለት ትችላለህ “በጥምቀት ከአዳም የውርስ ኀጢአት ድኜያለሁ፤ ይሄ ድኅነት የሚገኛዉ በደመ ክርስቶስ የቤዛነትንና የድኅነት ኀይል ነው። ነገር ግን የመጨረሻዉ ድኅነት በስጋ ስንለይ የሚገኝ ነው። አሁንም በውጊያ ላይ ነን “መጋዳላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፣ ከአለቆችና ከስልጣናት ጋር ከዚህ ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳዊያን ሰራዊት ጋር እንጂ።” (ኤፌ. 6፥12)። ይሄንን ውጊያ ድል ስናደርግና ስናሸንፍ ድኅነትን እናገኛለን…”

በስጋ እስካለን ድረስ “ድል ነስተናል፤ ድኅነትን አግኝተናል” ልንል አንችልም። ስለዚህ ቅድስት ቤተክርስቲያን የቅዱሳንን ልደት አታከብርም ወይም የተጠመቁበትን ዕለት፤ ይልቁንም ከዚህ ዓለም የተለዩበትን ወይንም መስዋዕት የሆኑበትን ቀን ታከብራለች እንጂ። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላልና “ዋነኞቻችሁን አስቡ፣ የኑሮአቸዉንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸዉ ምሰሉአቸዉ።” (ዕብ. 13፥7)። ስለዚህ በቅዳሴ ላይ የቅዱሳንን መታሰቢያ እናደርጋለን፤ በእምነት ፍጹማን የሆኑትንና ሕይወታቸውን በእምነት የፈጸሙትን፣ በአጸደ ነፍስ ያሉ ቅዱሳንን ሁሉ እናስባለን።

ይሄም የታላቁ አባ መቃርስን ከዚህ ዓለም መለየት እንዳስታውስ ያደርገኛል። ነፍሱ ከስጋው ተለይታ ስትሄድ “መቃርስ አንተ ድነኸል” እያሉ አጋንንት ነፍሱን አሳደዷት፤ ነገር ግን ገነት እስከሚገባ ድረስ “በጌታ ጸጋ ድኜያለኹ” አላላቸዉም ነበር…!

አባታችን ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ከዛሬ ሃምሳ ዓመት በፊት ነገረ ድኅነትን አስመልክቶ ለፕሮቴስታንቶች መልስ ከሰጡበት “Salvation in the Orthodox Concept” ከተሰኘው መጽሐፍ ላይ የተወሰደ ነዉ።

@Enkeyopaghion
@Enkeyopaghion
621 views ፍቅርተ ስላሴ ስንት ሰዓት ነው ሰዓቱ ስንት ነው አሁንስ ስንት ሰዓት ነው ???, 17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ