Get Mystery Box with random crypto!

ትልቅ ደረጃ መድረስ ከፈለጋችሁ! በእድሜ ቆጠራ ብቻ፣ በገንዘብ ብዛት ብቻ፣ በአእምሮ እውቀትም | የኤማሁስ መንገደኞች........ channel )

ትልቅ ደረጃ መድረስ ከፈለጋችሁ!

በእድሜ ቆጠራ ብቻ፣ በገንዘብ ብዛት ብቻ፣ በአእምሮ እውቀትም ብቻ . . . ትልቅ ደረጃ መድረስ አይቻልም፡፡

እነዚህንና ሌሎችም ነገሮች ኖሯቸው በሕብረተሰቡ መካከል ትልቅ ደረጃ የደረሱ ሰዎች የመኖራቸውን ያህል፣ እነዚህ ነገሮች እያሏቸው ለአናሳ ነገር ሰክነውና አናሳ ሕይወት ኖረው የሚያልፉ ጥቂቶች አይደሉም፡፡

ትልቅ ደረጃ መድረስ ከፈለጋችሁ፡-


1. ከትንሽነት አመለካከት መውጣት አስፈላጊ ነው፡፡ አመለካከታችን ዛሬ ካለንበት ደረጃችን ወደላቀ ከፍታ የሚያወጣንን ራእይና አላማ ካላካተተ ይህ የአመለካከታችን ትንሽነት የማንነት አናሳነት መፍጠሩ አይቀርም፡፡

2. ከትንንሽ ንግግሮች መላቀቅ የግድ ነው፡፡ የምናወራቸው ነገሮች በእለቱ ከሚናፈሰውና የሰውን ነገር ከመብላት አልፎ ካልሄደ የንግግራችን አናሳነት የማንነት ትንሽነት መፍጠሩ አይቀርም፡፡

3. ከትንንሽ ገጠመኞች በላይ መኖር ወሳኝ ነው፡፡ በየቀኑ የሚገጥሙንን ጥቃቅን አስቸጋሪ ገጠመኞች አልፈን በመሄድ ትኩረታችንን ዋናውና ዘላቂው የሕይወታችን አላማ ላይ ካላደረግን ሁኔታው የማንነት አናሳነት መፍጠሩ አይቀርም፡፡፡፡

4. ከትንንሽ ዘሮች ዘልቆ መሄድ ጠቃሚ ነው፡፡ ትንሽ ዘር፣ ትንሽ ፍሬ … ትንሽ ሙከራ፣ ትንሽ ስኬት … ትንሽ መስዋእትነት ትንሽ ዋጋ … ትንሽ እቅድ፣ ትንሽ ውጤት ስሌቱ ይኸው ነው፡፡ ከዚህ አዙሪት ወጥተን በትልቁ መዝራት ካልጀመረን ሁታው የማንነት አናሳነት መፍጠሩ አይቀርም፡፡

https://t.me/Emmausmengdgnch
https://t.me/Emmausmengdgnch
https://t.me/Emmausmengdgnch