Get Mystery Box with random crypto!

El OlaM ▣

የቴሌግራም ቻናል አርማ elolam_the_everlasting_god — El OlaM ▣ E
የቴሌግራም ቻናል አርማ elolam_the_everlasting_god — El OlaM ▣
የሰርጥ አድራሻ: @elolam_the_everlasting_god
ምድቦች: ንድፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.10K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ገፅ የምታገኟቸው፤
#የሚያንፁ መንፈሳዊ ፅሁፎች✉️፤
#የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በምስል🖼፤
#መንፈሳዊ መፅሀፎችን📚፤

#ማራናታ🙌

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-07-02 10:32:33 @Elolam_the_Everlasting_God
1.4K viewsSam Sisay, edited  07:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 10:27:10
What does is mean to be saved? | Voddie Baucham | G3 Interviews
@Elolam_the_Everlasting_God
1.3K viewsSam Sisay, edited  07:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 20:37:35
1.2K viewsSam Sisay, 17:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 09:04:18 ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያህል ያውቃሉ?
❖ የመጀመሪያው መጽሐፍ ቅዱስ የተፃፈው በእብራይስጥ፣ በአረማይክ እና በኮይኔ ግሪክ ቋንቋዎች ነው።

❖ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ
• 66 መጽሐፍት
• 1,189 ምዕራፎች
• 31,173 አንቀፆች
• 810,697 ቃላት
• 3,566,480 ፊደላት ይገኛሉ።

❖ በጣም ረጅሙ መጽሐፍ- መዝሙረ ዳዊት ሲሆን
• በጣም አጭሩ መጽሐፍ- ሶስተኛ ዮሐንስ
• በጣም ረጅሙ ምዕራፍ- መዝሙረ ዳዊት 119
• አጭሩ ምዕራፍ መዝሙረ ዳዊት 117 ነው።

❖ የመጽሐፍ ቅዱስ አማካይ ስፍራ መዝሙረ ዳዊት 118:8 ነው።

❖በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የብዙ ሰዎች መጠሪያ የሆነው ስም ዘካሪያስ ነው።

❖ ብዙ ጊዜ ተደጋግሞ የተጠቀሰው ስም "ዳዊት" ሲሆን 1008 ጊዜ ተጠቅሷል። በመቀጠልም ኢየሱስ 973 ጊዜ፤ ሙሴ 829 ጊዜ ተጠቅሰዋል።

❖ ሙሉው መጽሐፍ ቅዱስ እና የትንቢተ ኢሳይያስ መጽሐፍ አስደናቂ መመሳሰል አላቸው።
ይኸውም፦
• መጽሐፍ ቅዱስ 66 መጽሐፍ ሲኖሩት ትንቢተ ኢሳይያስ 66 ምዕራፎች አሉት።
• የመጀመሪያው 39 የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት የሚተርኩት ስለ እስራኤል ህዝብ ነው። እንደዚሁም የመጀመሪያው የትንቢተ ኢሳይያስ 39 ምዕራፎች የሚተርኩት ስለ እስራኤል ህዝቦች ነው።
• የመጨረሻው 27 የመጽሐፍት ቅዱስ መጻህፍት የሚያስተምሩት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን፤ እንደዚሁም የመጨረሻዎቹ 27 የትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፎች የሚተርኩት ስለ ክርስቶስ መምጣት ነው።

❖ መጽሐፍ ቅዱስ ተፅፎ ያለቀው በ1600 ዓመታት የጊዜ ልዩነት ውስጥ ሲሆን ይህም ከ1500 ዓመተ ዓለም እስከ 100 ዓመተ ምህረት ድረስ ያለውን ዘመን ያጠቃልላል።

❖ መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው የጻፉት መጽሐፍ ነው።( 2ጴጥ 1:21)

❖ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ 49 የምግብ ዓይነቶች ተጠቅሰዋል፤ በተለይ "ጨው" 30 ጊዜ ተጠቅሷል።

❖ ከቤት እንሰሳት መካከል ስሟ ያልተጠቀሰ እንሰሳ "ድመት" ብቻ ናት።
ውሻ 14 ጊዜ ተጠቅሷል።

❖ በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ እራሳቸውን በራሳቸው ያጠፉ ሰዎች ሰባት ሲሆኑ
እነርሱም፦ 1. አቤሜሌክ 2. ሳምሶን 3. ሳዖል 4. የሳዖል ወታደር 5. አኪጦፌል 6. ዚምራ 7. ይሁዳ ናቸው።

❖ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ
ስለ ፀሎት 400 ጊዜ
ስለ እምነት 500 ጊዜ
ስለ ገንዘብና ሐብት ደግሞ 2,000 ጊዜ ተፅፏል። መጽሐፍ ቅዱስ ገንዘብን መውደድ የኃጢአት ሁሉ ስር ነው ይለዋል።


❖ መጽሐፍ ቅዱስ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ እንግሊዝኛ የተተረጎመው በ 1388 ዓ.ም ነው።
@Elolam_the_Everlasting_God
1.4K viewsSam Sisay, 06:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 11:42:59
1.5K viewsSam Sisay, 08:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 11:42:59 ስሑትና አሳች ትርጕማን

የ1980ዎቹ የኢኦተቤ/ክ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጕም የመጀመሪያውም እንደገና የታተመውም የሄደበት የአተረጓጐም ስልት የሚደንቅም የሚያስደነግጥም ነው። ትርጕም ከምንጭ ወደ ተቀባይ ይፈስሳል እንጂ ከተቀባይ ተነሥቶ ወደ ምንጭ ቋንቋ አይሄድም። በዚያ ትርጕም ውስጥ እንዲህ የተደረጉ በጣም ብዙ ቢኖሩም አንድ ሦስት ምሳሌዎች ብቻ እንይ።

አንደኛ፥ ቲቶ 1፥5 ሽማግሌ የሚለውን ቄስ ወይም ቀሳውስት ብለው በመለወጥ በግርጌ ማስታወሻ፥ #የግሪኩ #ሽማግሌዎች #ይላል።’ ብለው ጽፈዋል። ከየትኛው ነው የተረጐሙት ማለት ነው? ግሪኩ ይህን ካለ፥ ግሪኩ የግርጌ ማስታወሻ አማርኛው ዋና መሆኑ ነው ማለት ነው? አማርኛ ከግሪኩ መብለጡ ነው ማለት ነው? የግሪኩ ሽማግሌ ያለውን የአማርኛ የቀደሙት ተርጓሚዎችና ሊቃውንትም ሽማግሌ ያሉትን በኋላ የመጣው ተርጓሚ ሊለውጥ ድፍረትን ከወዴት አገኘ? ስሑት ትርጕም።

ሁለተኛ ምሳሌ፥ ይህኛው ወደ ምንጩ ወደ ግሪክም፥ ወደ ጎን ወደ ግዕዝም የሚሄድ ነው። ማቴ. 5፥6 ‘ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ’ የሚለውን፥ በመጀመሪያ ‘በግዕዙ፥ ‘ስለ ጽድቅ የሚራቡና የሚጠሙ’ የሚል የግርጌ ማስታወሻ ተጽፎለታል። በቀጣዩ ደግሞ፥ ‘በግሪኩ፥ ‘ስለ ጽድቅ የሚራቡና የሚጠሙ ይላል’ ተብሎ የግርጌ ማስታወሻ ተቀምጦለታል። እውነት ይላል? የትኛው ግዕዝ እንደሚል አልተገለጠም። ታትሞ የተሰራጨው የግዕዝ አዲስ ኪዳን፥ ‘ብፁዓን እለ ይርኅቡ ወይጸምኡ ለጽድቅ።’ ይላል። ጽድቅን እንጂ ስለ ጽድቅ አይልም። ወደ ግሪኩ ስንመጣም ስለ ጽድቅ ይላል? አይልም። ታዲያ ለምን ተባለ? ምናልባት ስለ ጽድቅ ሲባል ወይም ለመጽደቅ ሲባል ወይም ጽድቅን ለማግኘት ሲባል መራብና መጠማትን ለማስተማር ይመስላል። በማመን ሳይሆን በመከራና በጉስቍልና ለመጽደቅ የሚደረግ ጥረትን ትክክለኛ ለማስመሰል ያልተባለው እንደተባለ የተደረገ ነው የሚመስለው። ስሑት ትርጕም።

ሦስተኛ፥ ሮሜ 8፥34 ‘ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።’ የሚለውን፥ ‘ደግሞ ስለ እኛ የሚፈርደው ኢየሱስ ነው።’ ካሰኙት በኋላ በግርጌ ማስታወሻ፥ #ግሪኩ #የሚማልደው #ይላል።’ ብለዋል። ማለቱን አምነው ግን ለውጠውታል። ከሌላ ቋንቋ ጋር ተስተያይቶ፥ ለምሳሌ፥ እንግሊዝኛው ወይም ጉራግኛው እንዲህ ይላል ቢሉ አንድ ነገር ነው። ዋናው የተጻፈበት፥ ኦርጅናሌው፥ ‘ግሪኩ እንዲህ ይላል’ ብሎ ያ የምንጩ ቋንቋ ያላለውን መተርጐም ስነ ጽሑፋዊ ወንጀል ነው። መንፈሳዊ ዕብለቱን ትተን።

አዲስ ኪዳን የተጻፈው እኮ ሲጀመርም በግሪክ ነው። በግሪክ እንደዚያ ካለ፥ በምን ምክንያትና ሥልጣን ነው እኛ፥ ‘የግሪኩ የሚማልድ ይላል፤ እኔ ግን ይፈርዳል ብዬዋለሁ።’ ወይም፥ ‘የግሪኩ ሽማግሌ ይላል እኔ ግን ሊቅ፥ ሊቃናት፥ ቄስ፥ ቀሳውስት፥ ቀሲስ ብዬዋለሁ።’ ወይም፥ ‘የግሪኩ ጽድቅን ብሏል፤ እኔ ግን ስለ ጽድቅ ብያለሁ።’ የምንለው? ይህ አላዋቂነት ብቻ ሳይሆን፥ ድፍረትም ብቻ ሳይሆን፥ የትርጕም ሕግን መተላለፍ ብቻም ሳይሆን፥ አላዋቂዎችን የማሳት የአሳችነት አካሄድ ነው። የኑፋቄ የመጀመሪያው እርምጃ ነው፤ ትልቅ እርምጃ!

መጽሐፍ ቅዱሳችንን በአክብሮት እንማረው፤ ትርጕሙም፥ አተረጓጎሙም፥ ትርጓሜውም ጤነኛ ሆኖ እንጠብቀው።

ዘላለም ነኝ።
1.3K viewsSam Sisay, 08:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 10:20:43
1.1K viewsSam Sisay, 07:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 17:08:02
2ኛ ቆሮ 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶ ይህንም እላለሁ፦ በጥቂት የሚዘራ በጥቂት ደግሞ ያጭዳል፥ በበረከትም የሚዘራ በበረከት ደግሞ ያጭዳል።
⁷ እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ፥ በኀዘን ወይም በግድ አይደለም።
⁸-⁹ በተነ፥ ለምስኪኖች ሰጠ፥ ጽድቁ ለዘላለም ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ እግዚአብሔር፥ ሁልጊዜ በነገር ሁሉ ብቃትን ሁሉ አግኝታችሁ ለበጎ ሥራ ሁሉ ትበዙ ዘንድ፥ ጸጋን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል።
¹⁰ ለዘሪ ዘርን ለመብላትም እንጀራን በብዙ የሚሰጥ እርሱም የምትዘሩትን ዘር ይሰጣችኋል ያበረክትላችሁማል፥ የጽድቃችሁንም ፍሬ ያሳድጋል፤
https://t.me/Elolam_the_Everlasting_God
https://t.me/Elolam_the_Everlasting_God
1.2K viewsAn Du, 14:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ