Get Mystery Box with random crypto!

ያንቺ ሀገር ወዲያ የኔ ወዲ ማዶ ሀገረ ተቃጠለ ሰው ሆኖ ማገዶ ሰሜኑ ነደደ ምስራቅ ጨለመበት ምዕ | ሰም እና ወርቅ

ያንቺ ሀገር ወዲያ የኔ ወዲ ማዶ
ሀገረ ተቃጠለ ሰው ሆኖ ማገዶ
ሰሜኑ ነደደ
ምስራቅ ጨለመበት
ምዕራቡ ተርቦ
ደቡብ ሞት ነግሶበት
ከየት ይመጣል ሀገር ከየት ይመጣል ወዜ
መጠጣት ተስኖኝ ከውሀ ከወንዜ
የኔ ሀገር የለም
ያንቺም ሀገር ጠፋ
ጎበዙ ዝም ሲል አውርቶ ከርፋፋ
ግና እኔ!
ወዝ ርቋት ሳትደርቅ
በምላሴ ስሟ በብዕር ገጥሚያት
በልቤ ሸራ ላይ በስዕሌ አኑሪያት
ታሪኳ ተራቁቶ እሷነት ቢርቃት
አለች ከኔ ጋራ
ከልቤ ድርሻ አላት።
.
#ኢልያስ #ሀበሻ
.
t.me/Eliyaskedir
t.me/Eliyaskedir