Get Mystery Box with random crypto!

ቅዱስ እስጢፋኖስ | 𝚂𝚝 𝚂𝚝𝚎𝚙𝚑𝚎𝚗

የቴሌግራም ቻናል አርማ elihu_tube —   ቅዱስ እስጢፋኖስ | 𝚂𝚝 𝚂𝚝𝚎𝚙𝚑𝚎𝚗
የቴሌግራም ቻናል አርማ elihu_tube —   ቅዱስ እስጢፋኖስ | 𝚂𝚝 𝚂𝚝𝚎𝚙𝚑𝚎𝚗
የሰርጥ አድራሻ: @elihu_tube
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.13K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ በቀዳሜ ሰማዕት ሊቀ ዲያቆናት በቅዱስ እስጢፋኖስ ስም የተከፈተ ምህላፍ / ቻነል ልዩ ልዩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅድስት ቤተ ክርሰቲያን ትምህሮቶች እና ሥርዓቶች የሚተላለፉበት ነው ።

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-25 20:29:32
#Share #Share #Share

@Elihu_Tube
@Elihu_Tube

https://www.tiktok.com/@Elihu_Tube

Follow Us on Tik-Tok
2.9K viewsedited  17:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 07:30:00 ሐምሌ 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

1.አባ ኅልያን ገዳማዊ
2.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሰማዕት (ዘሐምስቱ አሕጉር)
3.ቅዱስ ታውድሮስ ሰማዕት
4.ሰማዕታት ሉክዮስና ድግናንዮስ (በንስሃ ለክብር የበቁ የጦር አለቆች)

ወርሐዊ በዓላት

1.አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ኁሉ አባት)
2.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ (ኢትዮዽያዊ)
3."318ቱ" ቅዱሳን ሊቃውንት (ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ)
4.የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን
5.አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ (ኢትዮዽያዊ)
6.ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ (ዓለመ ብፁዐንን ያየ አባት)

አምላከ ቅዱሳን ለኛ ለባሮቹ የቅዱሳኑን እና የሰማዕታቱን ጽናት የወንጌላዊያኑንም ፍቅር ያድለን በረከታቸዉን ከማይጎድል እጁ አብዝቶ ይስጠን፡፡

@Elihu_Tube
@Elihu_Tube
3.9K views04:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 23:56:45
እንኳን ለቅድስት ስላሴ አመታዊ በዓለ ንግስ በሰላም አደረሳቹ!

- #FOR_PROFILE_PICTURE
-

@Elihu_Tube
@Elihu_Tube
809 views20:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 06:57:33 ለምን መስቀሉ ተዘቀዘቀ ?

የቤተክርስቲያን ጉዞ ሁልጊዜ በመስቀል ላይ ነው፡፡ ይህ የመስቀል ጉዞ ደግሞ መሥዋዕትነትን /መከራ መቀበልን/ ይጠይቃል፡፡ ከዚህም የተነሣ በሰይፍ የተመተሩ፤ በመጋዝ የተተረተሩ፣ በእሳት የተቃጠሉ ለአናብስት የተጣሉ በአጠቃላይ በብዙ ስቃይ የተፈተኑ ቅዱሳን ሐዋርያት አሉ፡፡ ከእነዚህ ሐዋርያት ደግሞ በዋናነት የሚጠቀሱት እነዚህ ሁለት ሐዋርያት ናቸው፡፡ «ሥጋን የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚችለውን ፍሩ፡፡» የሚለውን የጌታችንን ቃል መመሪያ አድርገው ለቤተክርስቲያን ሁሉን አድርገው፤ ሁሉን ሆነው የሰማዕትነትን ጽዋ ተቀብለዋል፡፡

ቅዱስ ጴጥሮስ ስለ ክርስትና ሃይማኖት የአይሁድ መሪዎችንና ሊቃነ ካህናቱን ይሞግት፤ ከእነርሱም ፊት ምስክርነት ይሰጥ ነበር፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ የአይሁድን ሊቃነ ካህናት «ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል» እያለ በሸንጎ ይሟገት ነበር፡፡ /የሐዋ.5.29/ በዚህም ብዙውን ጊዜ ይገረፍ ይታሰር ነበር፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ደግሞ ሐዋርያው ቅዱስ ጳዉሎስም የተለያዩ የመከራ ጽዋን ተቀብሏል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳዉሎስ እርሱና ሌሎች ሐዋርያት ስለክርስቶስ መከራ መቀበላቸውን ሲገልጽ «በሁሉ መከራ ስንቀበል አንጨነቅም፣ እንናቃለን አንዋረድም፤ እንሰደዳለን አንጣልም፤ እንጨነቃለን አንጠፋም፡፡» በማለት ነው፡፡ /2ቆሮ 4.8-11/ ከዚህም በተጨማሪ «በብዙ መጽናት፣ በመከራ፣ በችግር፣ በጭንቀት፣ በመገረፍ፣ በወኅኒ፣ በሁከት፣ በድካም፣ እንቅልፍ በማጣትም» በማለት የሰማዕትነት ሕይወቱን ገልጿል፡፡ /2ቆሮ.6.4-5፣ 1ቆሮ. 11.22-28/

በአጠቃላይ ቅዱስ ጳውሎስ የደረሰበትን መከራ ሁሉ በዚህ መልኩ ገልጿል፡፡ እነዚህ ሁለት ሐዋርያት በዚህ መልኩ ስለ ወንጌልና ስለክርስቶስ መከራ ከተቀበሉ በኋላ ከዚህ ምድር ያለፉት በሰማዕትነት ነው፡፡ ሁለቱም በሰማዕትነት ያለፉት በዘመነ ኔሮን ሐምሌ 5 ቀን 67 ዓ.ም ነው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ በሰማዕትነት ያረፈው የቁልቁሊት ተሰቅሎ ሲሆን ቅዱስ ጳዉሎስ ደግሞ አንገቱን ተሠይፎ ነው፡፡ ይህንም ለመገልፅ ሲባል የቁልቁሊት የቆመ መስቀል ቅዱስ ጴጥሮስ ይዞ ይሳላል። የእነዚህ ሁለት ታላላቅ የጌታችን ሐዋርያት ረድኤት በረከት አማላጅነት ሁላችንንም አይለየን፤ አሜን፡፡

@Elihu_Tube
@Elihu_Tube
1.1K viewsedited  03:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 10:04:22
በረከታቸዉ ይደርብን

#Share #Share #Share

@Elihu_Tube
@Elihu_Tube

https://www.tiktok.com/@Elihu_Tube

Follow Us on Tik-Tok
1.4K viewsedited  07:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 20:46:29
ለብርሐናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ ዓመታዊ የእረፍት በዓላቸው እንዲሁም ለፃድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በዓለ መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን

- #FOR_PROFILE_PICTURE -

@Elihu_Tube
@Elihu_Tube
1.3K viewsedited  17:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 19:02:55 ጥያቄ 5 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ለመጥራት ከምትጠቀምባቸዉ ስሞች ቢያንስ አንዱን ጥቀስ/ጥቀሽ ? መልሳችሁን Comment ላይ
1.3K views16:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 18:58:29
- #FOR_PROFILE_PICTURE -

@Elihu_Tube
@Elihu_Tube
1.3K views15:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ