Get Mystery Box with random crypto!

እመቤቴ የጌታዬ እናት ሆይ የአንቺን ‛ይሁንልኝ’ የሚል ቃል ተከትሎ እግዚአብሔር ሰው ሆነ ። ሰው | Elias Official

እመቤቴ የጌታዬ እናት ሆይ የአንቺን ‛ይሁንልኝ’ የሚል ቃል ተከትሎ እግዚአብሔር ሰው ሆነ ። ሰው ሆኜ ተፈጥሬ ሰው መሆን ያቃተኝን እኔንስ ሰው የምታደርጊኝ መቼ ይሆን ? አምላክ ሰው እንዲሆን ይሁን ያልሺዋ ቅድስት ሆይ ስለ እኔ ሰው መሆን ‛ይሁን’ የምትዪው መች ይሆን ? ‛ በርታ ሰውም ሁን ’ የሚለውን ቃል መጠበቅ አቅቶኝ ኃጢአት ሠልጥኖብኝ ' ሰው ክቡር ሆኖ ሳለ አላወቀም እንደሚጠፋ እንስሳት መሰለ' የሚያሰኝ ሕይወት ለምኖረው ለእኔ ፣ እንደ ቃሉ መሆን ላቃተኝ ለኔ ወደ መሐሪው ልጅሽ ’ ይህ ኃጢአተኛው ባሪያህ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ ’ ብለሽ እኔንም እንደ ቃሉ የምታደርጊኝ መች ይሆን ?