Get Mystery Box with random crypto!

Elias Official

የቴሌግራም ቻናል አርማ eliasoffical — Elias Official E
የቴሌግራም ቻናል አርማ eliasoffical — Elias Official
የሰርጥ አድራሻ: @eliasoffical
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.66K
የሰርጥ መግለጫ

አዎቂነት መታጨት እና መፈለግ ነው...አስተውል ዛሬ የምታስባት ሀሳብ የነገ ህይወትህ ላይ ያንበሳውን ድርሻ ትይዛለችና

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-17 16:28:22

261 viewsEtNet, 13:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 12:42:41

363 viewsEtNet, 09:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 21:01:56 ‹‹... የሰው ልጅ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ መጠኑና ስፋቱ ቢለያይም፣ ራሱ በሠራው አሊያም ሌሎች ባጠሩለት እስር ቤት ይኖራል፡፡ እንደ ራሱ ሃሳብና አመለካከት ግን ትልቅ እስር ቤት የሚኾንበት አንዳች ነገር የለም፡፡ ......

በዚህች ምድር እጅግ ብዙ ሰው በአእምሮው እስር ቤት ውስጥ በአሉታዊ አስተሳሰብ ታስሮ፣ በከንቱና እንቶ ፈንቶ ፍርሀት ተይዞ ማንም እንዳይረዳው ኾኖ የእስር ቤት ቊልፉን ራሱ ደብቆ ይኖራል፡፡ ››

ምንጭ:- ሜሎሪና
788 viewsEtNet, 18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 00:27:14 እመቤቴ የጌታዬ እናት ሆይ የአንቺን ‛ይሁንልኝ’ የሚል ቃል ተከትሎ እግዚአብሔር ሰው ሆነ ። ሰው ሆኜ ተፈጥሬ ሰው መሆን ያቃተኝን እኔንስ ሰው የምታደርጊኝ መቼ ይሆን ? አምላክ ሰው እንዲሆን ይሁን ያልሺዋ ቅድስት ሆይ ስለ እኔ ሰው መሆን ‛ይሁን’ የምትዪው መች ይሆን ? ‛ በርታ ሰውም ሁን ’ የሚለውን ቃል መጠበቅ አቅቶኝ ኃጢአት ሠልጥኖብኝ ' ሰው ክቡር ሆኖ ሳለ አላወቀም እንደሚጠፋ እንስሳት መሰለ' የሚያሰኝ ሕይወት ለምኖረው ለእኔ ፣ እንደ ቃሉ መሆን ላቃተኝ ለኔ ወደ መሐሪው ልጅሽ ’ ይህ ኃጢአተኛው ባሪያህ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ ’ ብለሽ እኔንም እንደ ቃሉ የምታደርጊኝ መች ይሆን ?
757 viewsEtNet, 21:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 21:07:23 አንብቧት ከጠቀማችሁ ሼር አድርጉት

ይድረስልኝ ፍቅር ይዞኛል ለምትሉ ሁሉ
..........................................................
አንተ ፍቅር ይዞኛል የምትለው፤ አዎ አንተ አንችም እንደዛው በፍቅሯ አብጃለው፣ ስነሳም ስተኛም ስለእርሷ ነው የማስበው የምትለው! በዓይኗ ሰረቅ አድርጋ ድንገት ስታየኝ ልቤ ቀጥ ይልብኛል የምትለው፤ እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ? አያድርገውና በመጀመሪያ ያየሃት ቀን ያፈዘዘህ ዓይኗ ቢፈስ፣ ቀልብህን ስቦ ያስደነገጠክ መልኳ ቢጠቁር እና ቢጠፋ፣ እስከ ወገቧ የረዘመው ፀጉሯ ቢቆረጥ፣ አቅርበሃት ጓደኛህ ካደረካት በኋላ የወደድክላት ፀባዩዋ እና ሥርዓቷ ተለውጦ ክፉ እና ደረቅ ብትሆንብህ፣ አንጀትህን ያርሰው የነበረው አረማመዷና ቅልጥፍናዋ በበሽታ ተቀምቶ አልጋ ላይ ሆና ብታቃስት አሁንም ከእርሷ ጋር ትሆናለህ? እንደ ድሮ ከእርሷ ጋር ለመሆን ትሽቀዳደማለህ? ሁሌ እንደምታፈቅራትና እንደምትሳሳላት መንገርህን ትቀጥላለህ? ለእርሷ የምታሳየው ትህትናና ክብር ይቀንስብሃል? አንቺስ ብትሆኚ? መጀመሪያ ያየሽው ዕለት ደስ ያለሽ መልኩና ቁመናው እንዳልነበረ ቢሆን፣ ሁሌ አንቺን ለማስደሰት ብሎ አንቺን በመጋበዝ እና በማዝናናት ያጠፋው የነበረው ገንዘብና ሀብት ጠፍቶ ፍጹም ደሃ ቢሆን፣ መጀመሪያ የተዋወቃችሁ ሰሞን ሲያሳይሽ የነበረው ፍጹም ትህትና እና አክብሮት ተለውጦ በትዕቢት አንቺን መማታት ቢጀምር፣ ጤንነቱን አጥቶ በበሽታ ቢንከራተት፣ በመጀመሪያ ወደ እርሱ ስቦ ያመጣሽ ነገሮቹ ሁሉ ቢጠፉ አሁንም ከእርሱ ጋር ትሆኚያለሽ? አሁንም እርሱ ጋር ስልክ መደወልሽን ትቀጥያለሽ? እህቴ ሆይ እስቲ ንገሪኝ፤ ፍቅርሽ ከአፍሽ ነው ወይስ ከልብሽ? ወንድሜ ሆይ ልጠይቅህ፤ ፍቅርህ በመናገር ነው ወይስ በተግባር?

መልሳችሁ " ይህ ቢፈጠር አብሬ አልቀጥልም" ከሆነ ከመጀመሪያውም ፍቅር እንዳልያዛችሁ ላርዳችሁ እወዳለሁ፡፡ ስትተያዩ እወድሃለሁ፣ እወድሻለሁ ከምትባባሉ ባየሁሽ/ ባየሁህ ቁጥር በውስጤ ያሉት ንጥረ ነገሮች (hormones) ይንተከተካሉ ብትባባሉ የተሻለ ነው፡፡ ምክንያቱም የፍቅር ትርጉም ይህ አይደለምና፡፡

ፍቅርማ ምን እንደሆነ ራሱ ፍቅር የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገባ አስተምሮናል፡፡ እርሱ ከምድር አፈር ካበጃጀን በኋላ የሕይወትንም እስትንፋስ እፍ ካለብን በኋላ ፍጥረት ሁሉ መልካም እንደሆነ ተመልክቷል፡፡ ያኔ አምሮብን፣ ተከብረን ሳለ ወዶናል፡፡ እፀ በለስን በልተን ያበራ የነበረው የጸጋ ልብሳችን ተገፎ ራቁታችንን ስንሆን፣ ደዌ የማያውቀው ሥጋችን በከንቱ ፍትወታት ሲታመምም በፍጹም ፍቅሩ አፍቅሮናል፡፡ ይተወንም ዘንድ ስላልቻለ ፍቅርን ፍቅር ከዙፋኑ ስቦ ስለእኛ እስከ ሞት አደረሰው፡፡ ታመን በኃጢአት አልጋ ተኝተን ሳለ ከጎናችን ሳይለይ ያሳታመመን አምላካችን ነው፡፡ እስከመጨረሻው ድረስ በኃጢአት የከረፋነውን ሳይጸየፈን ተጠግቶን ቁስላችንን በቁስሉ ያከመን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ሊያክመን መጥቶ እንኳን እኛ አልተቀበልነውም፡፡ ቁስላችንን ሳይጸየፍ የቀረበንን ፈጣሪያችንን መታነው፡፡ ኑ ላድናችሁ ሲለን በመስቀል ላይ ሰቀልነው፡፡ ሐኪሙን የሚሳደብና የሚማታ በሽተኛ እንደምን ያለ ነው? የበሽተኛውን ስድብ እና ድብደባ ታግሶስ በትጋት የሚያክም ሐኪም እንደምን ያለ ነው? ለዚህስ አንክሮ ይገባል!!

ወዳጄ ሆይ ፍቅር በደስታ ጊዜ ኖሮ በኃዘን ጊዜ የሚጸና፣ በጤናው ጊዜ አብቦ በደዌ ጊዜ የሚፈካ፣ በሰላም ጊዜ ተኮትኩቶ በጭንቅ ጊዜ የሚበቅል ረቂቅ የአምላክ ስጦታ ነው፡፡ ታድያ ወዳጄ ሆይ በፍቅርሽ ተይዣለሁ ያልካት ሚስትህን ያማረው መልኳ በድንገት ቢጠፋስ ብለህ የምትጨነቅ ከሆነ እንዴት እወዳታለሁ ልትል ትችላለህ? ጤናዋን አጥታ አልጋ ላይ ብትተኛ ጥለሃት ለመሄድ የምታስብ ከሆነ እንዴት እወድሻለሁ ልትላት ትችላለህ? አንቺስ ብትሆኚ፤ ፀባዩ እንዳለ ተለውጦ ቢንቅሽና ቢያቃልልሽ ትተሽው ለመሄድ የምታስቢ ከሆነ እንዴት ዓይኑን እያየሽ እወድሃለሁ ትይዋለሽ? ቢመታሽም እንኳን እንደ አምላክ ምቱን ታግሰሽ እርሱን ለማከም ካልፈቀድሽ እንዴት አፈቅርሃለሁ ትይዋለሽ?

" ፍቅር ያስታግሳልና"(1ኛ ቆሮ 13÷4) የማትታገሱ ከሆነ እንዴት ፍቅር ይዞኛል ትላላችሁ? አምላክ ያሳየንን ፍቅር ለሌሎች በመስጠት ክርስቶስን ልንመስለው ይገባናል፡፡ እህቴ ሆይ ወዳጅሽ በክፉ ሱስ ተጠምዶ፣ በትዕቢትና በንቀት ልቡ ተነድፎ ገብቶ ቢያንቋሽሽሽ ለእርሱ የምትሰጪው ፍቅር እንዲጎድል አትፍቀጂ፡፡ የፈለገ ተለውጦ የማታውቂው ሰው ቢሆንብሽም ለእርሱ የምትሰጪውን እንክብካቤ በትጋት ፈጽሚ፡፡ ያለንግግር ፍቅርሽን የሚነግሩትን ዓይኖችሽን ከዓይኖቹ አታንሺ፡፡ ወንድሜ ሆይ የሚስትህን የምትወድላት ፀባዩዋን ረስታ ደረቅና የምታውክ ብትሆንብህ እንኳን በስስት የምታያትን የፍቅር መመልከት አትንፈጋት፡፡ አምላክስ በሕመማችን ጊዜ ዓይኑን ከእኛ ድንገት ቢያነሳ ኑሮ ወድቀን እንደምንቀር ሁሉ አንተም ዓይንህን ከሚስትህ ላይ አታንሳ፡፡ ጌታ በፍጹም ፍቅር ወዶናልና እርስ በርሳችሁ በሚያስታግሰው እውነተኛው ፍቅር ተዋደዱ፡፡ በፍቅርም ቃል ተነጋገሩ እንጂ አትቆጡ፡፡

ቸሩ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ የአፍ ብቻ ሳይሆን የልቡና፣ በመናገር ብቻ ሳይሆን በተግባር የምንገልጠው እውነተኛውን ፍቅር ስጠን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን
787 viewsEtNet, 18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 18:29:51 እውነተኛ ሰዎች አብዛኞቹ ብቸኛ ናቸው
648 viewsEtNet, 15:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 16:12:36 «ለመተኛት ወደ አልጋህ ባመራህ በቀረብህ ጊዜ አልጋዬ፡ ምን አልባት በዚህ ሌሊት ለእኔ መቃብሬ ልትኾኚ ይኾን ይኾናል፤ በጊዜአዊው ዕንቅልፍ ፈንታ በዚህ ሌሊት ያኛው እንቅልፍ (ሞት) ይመጣብኝም እንደ ኾነ አላውቀውም በላት ።ስለዚህ ነጻ እግሮች እያሉህ ከመልካም ሥራ በኋላ ሩጥ፤ ከታሠሩ መፈታት በማይችሉበት ማሰሪያ ከመታሠራቸው በፊት፡፡ የእጆችህ ጣቶችም እስካሉህ ድረስ ሞት ከመምጣቱ በፊት በጸሎት ፊትህንና መላ ሰውነትህን በተእምርተ መስቀል አማትብ፡፡ ዐይኖች እስካሉህ ድረስ በአቧራ ከመሽፈናቸው በፊት በእንብዕ(በእንባ) ምላቸው።ሰው ሆይ ከዚህ ዓለም መለየትህን አስብ፣ እንዲህም በል፡- እነሆ የታዘዘ መልአክ ከበር ቆሞአል (ደርሶአል)፣ እኔንም ይከተለኛል። ለምን ሊል ዘሊል እኾናለሁ? መመለሻ የሌለው ዘለዓለማዊ መንገድ አለ፡፡መለኮት ደግነት የተነሣ የሰውን ልብ የሚገዛውና ነፍስን ወደ ሕይወት የሚመራት የመጀመሪያው ትምህርት ተዘክሮተ ሞት ነው።.ተዘክሮተ ሞት በሰይጣን እጅግ በብዙ ይጠላል፡፡ እርሱም ከሰው ተዘክሮን ለመንቀል በሙሉ ኃይሉ መሞከርን አይተዉም፡፡ የሚቻለውስ ቢኾን በምድራዊ ሕይወት አሳብ ተብትቦ ተዘክሮተ ሞትን ከሰው ልብ (አእምሮ) ለማስወገድ ምድራዊ መንግሥታትን ለሰው በሰጠው ነበር፡፡ አታላዩ ሰይጣን ተዘክሮተ ሞት በሰው ሁልጊዜም ካለ፣ አሳቡ ለአሁኑ ሕይወት መታለሎች የተጣበቀ ኾኖ እንደማይቀር አልያም የሰይጣን ማታለሎች ሰውን ሊቀርቡት እንደማይችሉ ያውቃል፡፡"
687 viewsEtNet, 13:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 18:53:00 አንድ ሰው መጥቶ ለአንድ ቅዱስ አባት ጥያቄ አቀረበለት

"ተአምር መሥራት እፈልጋለሁ ፣ እንዴት ላድርግ?"
ቅዱሱ አባት መለሰለት

"አንድን ሰው ወንጌል እንዲያነብ ካስተማርከው ዓይን አበራህ ማለት ነው

ድሆችን እንዲረዳ ካስተማርከው ሽባውን አዳንክ ማለት ነው

ወደ ቤተ ክርስቲያን መሔድ እንዲችል ካደረግህ አንካሳውን ፈውሰሃል

ሙት ማንሣት ከፈለግህ ደግሞ ንስሓ እንዲገባ አድርገው ያኔ የሞተ ሰውን አስነሥተሃል ማለት ነው
በል ሒድና ተአምር ሥራ!"



ለልጆቻችን ክርስቶስ ማን እንደሆነ እኛ ካልነገርናቸው ዓለም ክርስቶስ ያልሆነውን ሁሉ ይነግራቸዋል።



"ፍቅር እንዴት መቆጣት እንዳለበት አያውቅም"
ቅዱስ ማር ይስሐቅ



ኃጢአተኞች በሌላ ኃጢአተኛ ላይ ከእነርሱ ለየት ያለ ኃጢአት ስለ ሠራ ይፈርዱበታል ፣ ወይም ተመሳሳይ ኃጢአት ቢሠራም ይፈርዱበታል።


“የሚጾሙ የሚጸልዩና የሚተጉ ድቃቂ ሳንቲም እስካላስወጣቸው ድረስ በምንም ነገር ላይ የሚገኙ በችግር ላይ የሚሰቃዩትን ግን ዞር ብለው የማያዩ ብዙ ሰዎችን አውቃለሁ" ቅዱስ ባስልዮስ



"እኛ መነኮሳት ነን:: እኛ የሠለጠንነው ሰዎችን ለመግደል ሳይሆን ምኞታችንን ለመግደል ነው" አባ ጴኤሜን

★ ★ ★
አባታችን ሆይ እንዴት ትላለህ?

እንደ ልጅ ካልኖርህ እንዴት "አባት" ትለዋለህ?
ሌላውን ጠልተህ ራስ ወዳድ ከሆንክ እንዴት አባት "አችን" ብለህ በአንድነት ትጠራዋለህ?
ምድራዊ ነገር ብቻ እያሰብህ እንዴት "በሰማያት የምትኖር" ትለዋለህ?
ልብህ ከእርሱ ርቆ በአንደበትህ ብቻ እየጠራኸው "ስምህ ይቀደስ" እንዴት ትለዋለህ?
ሥጋዊና መንፈሳዊውን እየቀላቀልህ "መንግሥትህ ትምጣ" ለምን ትለዋለህ?
መከራን በጸጋ የማትቀበል ከሆነ "ፈቃድህ ይሁን" ለምን ትላለህ?
ለራስህ ሆድ እንጂ ለተራቡት ግድ የማይሰጥህ ከሆነ ለምን "እንጀራችንን ሥጠን" ትላለህ?
በወንድምህ ላይ ቂም ይዘህ "እኛም የበደሉልን ይቅር እንደምንል" እንዴት ትላለህ?
የኃጢአትን አጋጣሚዎች ሳትሸሽ "ወደ ፈተና አታግባን" እንዴት ትላለህ?
ክፉን ለመቃወም አንዳች ሳታደርግ "ከክፉ አድነን" እንዴት ትላለህ?
ጸሎቱን ከልብህ ሳትሰማውስ እንዴት አሜን ትላለህ?

ምንጭ: Orthodox Notes (ON)
ትርጉም: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጎተንበርግ
663 viewsEtNet, 15:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 20:00:27 #ምርጥ #ባህሪ

ጥቂት አዉራ፡፡ ስታወራ ቀስ ብትል መልካም ነዉ፡፡

አንድ ቦታ ላይ ብዙ አትታይ፡፡ ስራህ ላይ አተኩር፡፡

ምርጥ የሰዉነት አቋም ይኑርህ፡፡

ተግባቢና የተረጋጋ ሰዉ ሁን፡፡

ማንም ትክክል ነህ እንዲልህ አትጠብቅ፡፡ ማንም ደጋፊህ እንዲሆን አትጎትጉት፡፡

ስላለህ ነገር ደጋግመህ እየተናገርክ የመጎረር ስሜትን ከመፍጠር ተቆጠብ፡፡

ፀዳ በል፡፡ በደንብ ልበስ ፣ ፏ በል!

ምርጥ አዳማጭና መፍትሄ አምጪ ሁን፡፡

አደርገዋለሁ ያልከዉን ነገር አድርገዉ፡፡

በጣም ደስ ሲልህ ወይም በጣም ስታዝን ዉሳኔ አትወስን፡፡

ሴቶችን በአስተሳሰባቸዉ ብቻ መዝናቸዉ፡፡

የግል ጉዳይህን ላገኘኸዉ ሰዉ ሁሉ አትናገር፡፡

ሰዉ ስላንተ የፈለገዉን ቢያስብ ከማንነትህ ጋር አታገናኘዉ፡፡

ሃላፊነት መዉሰድን አትፍራ፡፡

ማንንም ለመጉዳት ብለህ ጉድጓድ ከመቆፈርም ይሁን ከማስቆፈር ራስህን አሽሽ፡፡

የጎዱህንና ‘ምንም የለዉም!’ ብለዉ የራቁህን ሰዎች ስኬታማ በመሆን አሳያቸዉ፡፡

ሃሳብህን ለማሳመን የሰዎችን ማንነት አትጉዳ፡፡ ትክክክል ብትሆን እንኳን ካመኑ ይመኑህ ካላመኑህ ጊዜዉ ያሳምናቸዋል፡፡

ለአንቺም በተመሳሳይ እህቴ፡፡
653 viewsEtNet, 17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 12:12:16
788 viewsEtNet, 09:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ