Get Mystery Box with random crypto!

“ከዛሬ ጀምሮ የክልል ልዩ ኃይል የሚባል አደረጃጀት የለም”  - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ http | እለታዊ ዜና

“ከዛሬ ጀምሮ የክልል ልዩ ኃይል የሚባል አደረጃጀት የለም”  - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
https://amharic.voanews.com/a/7051902.html

“ከዛሬ ጀምሮ የክልል ልዩ ኃይል የሚባል አደረጃጀት የለም” ሲሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ዛሬ ተናግረዋል።


የመከላከያ ጀነራሎች፣ ፌዴራል ፖሊስ እና የክልል የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት የክልል ኃይሎችን በፌዴራል ኅይሎች ውስጥ መልሶ ማደራጀት በተመለከተ ገምግማ መካሄዱን ብሔራዊው የቴሌቭዥን ጣቢያ ኢቢሲ ዛሬ ዘግቧል።


“የክልል ልዩ ሃይሎች እንደገና በመደራጀታቸው ህብረ ብሄራዊ ጠንካራ የጸጥታ ተቋም ይገነባል” ሲሉ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ መናገራቸውን ጣቢያው ዘግቧል።


“ኢትዮጵያ ከነበረችበት የጸጥታ ችግር በፍጥነት መውጣቷን፣ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነትም በመልካም ሁኔታ እየተከናወነ” መሆኑን መናገራቸውንም ሪፖርቱ አክሏል።


የክልል ኃይሎችን አደረጃጀት ለመቀየር ካስገደዱት ጉዳዮች መካከል “የክልል ልዩ ኃይሎች አደረጃጀት ህጋዊ አለመሆን፣ በክልሎች መካከል እንደ ስጋት መተያየት እንዲሁም ችግሮችን በሃይል ለመፍታት የሚደረገው እንቅስቃሴ” መሆናቸውን ፊልድ ማርሻሉ ተናግረዋል።


በሁሉም ክልሎች መልሶ የማደራጀት ሥራው “ተጠናክሮ መቀጠሉን" የገለጹት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም “ከዛሬ ጀምሮ የክልል ልዩ ኃይል የሚባል አደረጃጀትና መዋቅር የለም" ብለዋል።