Get Mystery Box with random crypto!

Ekutiinaa😍😘😍😘😉

የቴሌግራም ቻናል አርማ ekutiinaa — Ekutiinaa😍😘😍😘😉 E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ekutiinaa — Ekutiinaa😍😘😍😘😉
የሰርጥ አድራሻ: @ekutiinaa
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 741
የሰርጥ መግለጫ

*አይነ ስውሩ አለምን ማየት ይመኛል*
*መስማት የተሳነው ድምፅን መስማት ይመኛል*
እና ወዳጄ አላህ ለሠጠህ ነገር ምስጋናን አድርስ

አልሀምዱሊላህ

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-23 08:47:25
አሁን ደስተኛ ነኝ! ዛሬ ቀኑ ደስ ይላል!

@Ekutiinaa || @Ekutiinaa
229 views✿Smart girl , 05:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 23:18:01
ወንድ ልጅ እናቱ ስትወልደው
የተሰማት ህመሞች ቢሰማው ኖሮ
ምንም ያህል ምክኒያቶች ቢገዝፉም
አንድም ቀን ሴትን ልጅ አያሳዝንም ነበር ::

https://t.me/Ekutiinaa
223 views✿Smart girl , 20:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 22:00:12 ፃፍ!
ምናልባት ያንተ መፃፍ የተሰበረን ልብ ይጠግን ይሆናል
ምናልባትም ተስፋ አጥቶ የጠወለገ ልብ ላይ ተስፋን ይጭር ይሆናል
ፅናት ያለውን ሰው ያበስር ይሆናል

ፃፍ
ልቦች ህያው ይሆኑ ዘንድ
በሌሎች መመራት የማይቋረጥ ምንዳ ትቸር ዘንድ
የፀኑትን ልታበስር እውቀትህም ሊፋፋልህ

ፃፍ አስታውስ ማስታወስ ለምዕመናን ይጠቅማልና


=================================
ጌታዬ ሆይ
ስለአንተ የሚያወሩ አንደበቶችን፣
አንተን ለማወቅ የሚያነቡ አይኖችን፣
የነብዩን ሱንና የሚፅፉ እጆችን በአሸናፊነትህ ከእሳት ቅጣት ጠብቃቸው። ለኛም እዘንልን
================================
ረቢ ይቅር በለን፤ ማረን፤ የተሟላ ደህንነትንም ለግሰን።
[ ...........]

┏━ ━━━━ ━┓
@Ekutiinaa
┗━ ━━━━ ━
223 views✿Smart girl , 19:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 19:30:40
እንዳልመለስበት አድርገህ ድክመት እና ጥፋቶቼን ስለምታሳየኝ ወድሃለው....... ሰዎችን መፈተን ባይዋጣልኝም ሆን ብዬ ማጥፋት ወዳለው..... ለምን ካልከኝ...... የልብ ወዳጄ ጥፋቴን አይቶ ዝም የሚለኝ አይደለም..... ለኔ የቀረበ ለራሴው ጉዳይ እኔን የሚጣላኝ እንደሆነ አምናለው......

ዝምታ አንድም ለጥልቅ ህመም..... አንድም ለቸልታ..... አንድም ደግሞ ከራስ ለመማከር....... የትኛውን ዝምታ ዝም እንዳልኩህ ለማወቅ እኔ ጋር አትምጣ....... ከራስ ጋር ለመማከር የሚሆነውን ዝምታ መርጠህ ዝም በል........

ዝም ያልኩህ ጊዜ የሆነ ነገርህን አጥቼዋለው...... የሆነ ነገሬን ነጥቄሃለው....... አስከመች?..... እንጃ...... ምናልባት ዝምታው እስኪሰበር!......
.
.
@Ekutiinaa
@Ekutiinaa
218 views✿Smart girl , 16:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 13:25:43 "አንተ ነህ?"

ውዴ አንተ ነህ? ያ እንኳን ሳላውቀው በፍቅሩ ክንፍ ያልኩለት.....ውድ ባለቤቱ የልጆቹ እናት የቤቱ ብርሀን የቀኑ ድምቀት የደስታክ ምንጭ የጭንቀቱ ማስረሻ ልሆንለት የተዘጋጀሁለት አዎ ሀቢቢ አንተ ያ ነህ? አዎ አንተ መሆን አለብህ ያ እኔ ምናፍቀው የህይወትን ውጣ ውረድን ከሱ ጋር ማየት የምሙኘው ህመሙን መታመም ደስታውን ለመደሰት የተዘጋጀሁት እኮ ያ እንኳን ምን አለ በህልሜ አንዴ እንኳን በያው ብዬ የምናፍቀው........ጌታዬን አገናኘኝ ብዬ በግንባሬ ተደፍቼ የእንባ ዘለላዎች እያወረድኩ የማለቅስለት የነውሬ መሰተሪያ የሀምትሆንልኝ የቤቴን ገመና የምልትደብቅልኝ..... እሺ ሌላው ይቅር ያ እንኳን አላህዬ ሀቁን ተወጪው የጀነት መግቢያ መንገድሽ ነው ብሎ ያዘዘኝ ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ለሰሀቦቻቸው ፍጡር ለፍጡር መስገድ ቢችል ሴት ልጅ ለባሏ ሱጁድ እንድታደርግ አዛታለሁ ያሉን....የኔ ሀቢቢ አንተ ማለት የጀነት ሙሽራዬ የልጆቼ አባት የልቤ ንጉስ የቤቴ ድምቀት...... ወተህ እስክትገባ ናፍቆትህ የሚያንከራትተኝ ..... ደክሞህ ስትገባ ጎንህን ማሳረፊያ ላዘጋጅልህ ደፋ ቀና ምልልህ.....እኮ ውዴ ወደ ቤት ስትገባ ውብ ሁኜ ልጠብቅህ ሽቶው እንኳን ሳይቀር እላዬ ላይ ምነሰንስልህ.....እኮ የቤቱ ድምቀት የጨለማው ብርሀን የሆነውን ፈገግታህን ለማየት የምጓጓልህ አዎ አንተ ማለት ያ ነህ ሁሌም የምምኝህ አዎ ማሂ አንተ ነህ ውዱ ባሌ
225 views✿Smart girl , 10:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 09:00:17
አለማፍቀር እኮ የምድርን የተዘበራረቀ ደስታ የሚሰጥ ስሜትን...... የሰው ልጅ ሊደርስበት የሚችለውን የጥንካሬ ጥግ...... እራስን ውብ አድርጎ በራስ ላይ ሌላን አንግሶ የራስ ያለመሆንን ጥግ ........... በፍቃደኝነት ጎንበስ ብሎ መገዛትን.... መልካም የሚባሉ የህይወት ገፆችን መመልከቻ ቁልፍ ማጣት ነው!...…...

አለማፍቀር የማጣት ፍርሀትን........ ያለምክንያት መናፈቅን....... ያለትግል መረታትን..... ከራስ ላይ መገለልን እንዳናይ የሚያግድ ግድግዳ ነው........

አለማፍቀር አለም ላይ ያሉ ውብ..... አስደሳች..... እጅግ አስከፊ የሚባሉ ስሜቶችን አለማጣጣም እና አለማወቅ ነው.......

ምክንያት አልባነት የፍቅር መሰረት ነው......
ያለምክንያት ማፍቀር........ ያለምክንያት መፈለግ..... ያለምክንያት መናፈቅ..........ያለምክንያት የራስ አለመሆን....... ያለምክንያት ..........
ምክንያቱም ለሁሉም ፍቅር በቂው ምክንያት ነው፡፡

ሳላወራህ መቆየት መፍራቴን........ ሳላይህ መሰንበትን መጥላቴን....... ድምፅህን የመስማት ጉጉቴን እኮ እወደዋለሁ....... ፍቅር ነዋ!......
.
.
@Ekutiinaa
@Ekutiinaa
243 views✿Smart girl , 06:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 12:06:01
<<ድንግል የሆነች ፣ ግን ደግሞ እንደባለትዳር ሴት ብልህ የሆነች ፣ ወይም አግብታ የነበረ ግን እንደ ልጃገረድ የዋህና ተጫዋች የሆነች ፣ አጠገቧ ሲሆኑ ጣፋጭ ፣ ሲርቋት የምትናፍቅ ፣ ቀደም ብላ በድሎት ትኖር የነበረና በኋላ ድህነት የቀመሰች - በዚህም የተነሳ የሃብታምም ሆነ የደሃ ባህሪ ያላት ፥ ሃብታም ስንሆን የምድራዊውን ነዋሪዎች ገፅታ መላበስ የምትችል ስንደኸይ ደግሞ የጀነት ሰዎች ሥነምግባር የሚኖራት>>

ኻሊድ ኢብኑ ሶፍዋን የትዳር አጋሩ ብትሆን የሚመኛትን ሴት ባህሪ ሲመርጥ...


https://t.me/Islamictub
256 views✿Smart girl , 09:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 20:43:11
ሽቅርቅር እናት የለችኝም !...... የእጆቿ ከለር ከሰውነት ከለርዋ ጋር በጭራሽ አይገጥምም! .....ፊትዋ ለኔ የንጋት ጮራ ለመሰለ ፊት ተገብሯል ...... ሳቋ ድምፅ ኖሮት አያስተጋባም .....ስጋትና ጭንቀቷ በትንሽዬ ፈገግታዋ ስትታጀብ ነው ምድር የምትሞቀው ........

የምትለብሰው ሽቶ የተርከፈከፈበት፣ ፋሽኑ ያላለፈበት፣ ተመርጦ የተዘጋጀ ባይሆንም እናትነቷ የለበሰችውን ሁሉ ውብ ያደርገዋል ........ ድህነት አንገት ቢያስደፋት ተስፋና ሀላፊነት አትወድቂም ብለው ደግፈው አቁመዋታል .......... ስስት እና ፍቅር አይኗ ላይ የማይጠፉ ከልጅነት እስከ እውቀት የምመለከታቸው እውነቶች ናቸው........

ማካፈል ሳይሆን ያላችሁን ነገር እናንተ ጋር ሳታስቀሩ ልትሰጡት የማትሰስቱለት አካል ይኖር ይሆን? ግን ደግሞ ያለውን ሁሉ ለራሱ ሳያስቀር እና ሳይሰስት እየሰጠ የተቸገራችሁበት?

እናቴ ብቻ ናት!......... ሌላው ካለው ሲያካፍለኝ ያላትን ሳትሰስት የምትለግሰኝ ፍቅሯን ፣ እርህራሄዋን ...... ምን እዘረዝራለው? ሁሉንም ብዬ አጠቃልዬ የለ? በምን እክሳታለው ብዬ ሳስብ ምን ስለሆንሽ እያለ ውስጤ ባዶ ያደርገኛል... ውለታዋን ስለመክፈል ሳስብ ሰው ያለመሆኔ ስሜት ይሰማኛል.........

ታሳዝነኛለች ...... አለም ላይ ብቸኛዋ አሳዛኝ ፍጥረት ትመስለኛለች ...... ምድር ላይ ያልሳቀቻት ሳቅ ጀሊሉ በጀነት በብዙ ከነ ሁሉም ስጦታው እንዲያድላት ምኞቴ ነው! ........

ሁሉንም እናቶች አላህ ይጠብቅልን !
.
.
@Ekutiinaa
@Ekutiinaa
284 views✿Smart girl , 17:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 16:48:59
260 views✿Smart girl , 13:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ