2022-10-26 16:03:03
ጤና ይስጠልኝ ውድ የእፎይ ቤተሰቦች
ዛሬ ስለ ትርፍ አንጀትና ተያያዥ ጉዳዮች እናያለን
==================================
ትርፍ አንጀት ህመም ምክንያትና ምልክት
ትርፍ አንጀት የትልቁ አንጀት መጀመሪያ ላይ የሚገኝ ሲሆን በቀኝ የሆዳችን የታችኛው ክፍል ይገኛል፤ ቁመቱም እስከ 9 ሴንቲ ሜትር ሊደርስ ይችላል፤ ወፍራም ግድግዳም አለው፡፡
ትርፍ አንጀት ምንም አይነት ጥቅም እንደሌለው ለረዥም ጊዜ ሲታመንበት የኖረ ሲሆን እ.ኤ.አ በ2007 በተመራማሪዎች በተደረገ ጥናት ግን ጥቅም እንዳለው ተደርሶበታል፡፡
የትርፍ አንጀት በሽታ የሚከሰተው ከትልቁ አንጀት ጋር የተጣበቀው ጣት የመሰለው ተቀጥላ ወይም ትርፍ አንጀት ሲቆስል ነው፡፡
የትርፍ አንጀት በሽታ ምክንያቶች በባለሞያተኞች ጥናት መሰረት ለትርፍ አንጀት በሽታ ምክንያት ናቸው ተብለው የሚጠቀሱ ሁለት ምክንያቶች አሉ፡-
በአንዳች በሽታ ልክፍት ምክንያት በሆድ ውስጥ የሚፈጠር ማመርቀዝ (Infection)፡- በሆድ ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶች የሚጋጥም ልክፍት ወደ ማመርቀዝ ደረጃ ሲደርስ፣ ያ ሁኔታ በመስፋፋት ወደ ትርፍ አንጀት በመዝለቅ የሚያጋጥም እና
ቁራጭ ሰገራ በትርፍ አንጀት ውስጥ ተቀርቅሮ መቅረት (Obstruction)፡- ደረቅና ጠንካራ የሆነ ቁራጭ ሰገራ በትርፍ አንጀት ውስጥ በሚቀረቀርበት ወቅት በሰገራው ውስጥ የሚገኙ ባክቴሪያዎች የትርፍ አንጀቱን በመመረዝ እንዲታመም ስለሚያደርጉ ነው የሚል ነው፡፡
የትርፍ አንጀት ህመም ምልክቶች
የማያቋርጥና እየጨመረ የሚሄድ የሆድ ሕመም ሕመሙ በመጀመሪያ እምብርት አካባቢ ይጀምርና ወዲያውኑ ወደ ታችኛው ቀኝ የሆድ ክፍል ይዞራል።
መጠነኛ ትኩሳት፣ የሆድ ድርቀት፣ ተውከት ይኖራል፤ የምግብ ፍላጎትም ይቀንሳል፡፡
1.3K viewsHallè Teferi, 13:03