Get Mystery Box with random crypto!

ለቅድመ-ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞቻችን በሙሉ ተቋማችን የኢድ-አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ የቅ | Ethiopian Electric Utility

ለቅድመ-ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞቻችን በሙሉ

ተቋማችን የኢድ-አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ የቅድመ-ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞቻችን በበዓሉ ዕለት በመላው አገሪቱ በሚገኙ በተመረጡ የደንበኞች አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ካርድ መሙላት እንዲችሉ ሁኔታዎችን አመቻችቷል፡፡ በዚህ መሰረት

#ከ2_እስከ_6 ሰዓት ድረስ አገልግሎት የሚሰጡ

በአዲስ አበባ ከተማ፡- ጉርድ ሾላ፣ ካዛንችስ፣ ቱሊ ዲምቱ፣ አያት፣ ለቡ ቁ.10 እና ቤቴል ቁ.4 ማዕከላት፣
በኦሮሚያ ሪጅን፡- አዳማ፣ ጅማ፣ ሻሸመኔ እና ፊንፊኔ ዙሪያ ዲስትሪክት ስር ያሉ የተመረጡ ማዕከላት፣
በአማራ ሪጅን፡- ባህርዳር፣ ደብረማርቆስ፣ ጎንደር፣ ደብረብርሃን፣ ወልደያ ዲሰትሪክት ስር ያሉ የተመረጡ ማዕከላት፣
በሲዳማ ሪጅን፡- አዋሳ ቁ. 2 ማዕከል፣
በድሬዳዋ ሪጅን፡- ድሬዳዋ ቁ.2 ማዕከል፣
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ሪጅን፡- አሶሳ ማዕከል፣
በደቡብ ሪጅን፡- አርባምንጭ፤ ወላይታና ሆሳዕና ዲሰትሪክቶች ስር አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ ሁሉም ማዕከላት፣
በደቡብ ምዕራብ ሪጅን፡- በሪጅኑ ስር የሚገኙ ሁሉም ማዕከላት፣

#ከ2_እስከ_11 ሰዓት አገልግሎት የሚሰጡ

በሐረር ሪጅን፣ የሀረር ቀ.1 ማዕከል፣
በሶማሌ ሪጅን፡- በጂግጂጋ ከተማ በሚገኙ ቁ.1 እና 2 ማዕከላት እንዲሁም
በአፋር ሪጅን፡- በአዋሽ 7 ኪሎ፣ ሎጊያ፣ ሰመራ፣ ዱብቲና አሳይታ ማዕከላት፣
የካርድ መሙላት አገልግሎት የሚሰጡ መሆናቸው አውቃችሁ አገልግሎቱን ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት