Get Mystery Box with random crypto!

#MoE በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ | Educate Ethiopia

#MoE

በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ እና በመንግስት ተቋማት ገብታችሁ መማር የምትፈልጉ ተማሪዎች የተቋም ምርጫችሁን  በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ የካቲት 02/2015 ዓ.ም ድረስ እንድታስተካክሉ የትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።

በልዩ ሁኔታ በአዳማ እና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዪኒቨርሲቲዎች መማር የምትፈልጉ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና #የማይሰጥ መሆኑን አውቃችሁ መርጣችሁ መመደብ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ የምትሹ ተማሪዎች (ተመሳሳይ ጾታ ያላችሁ መንትያዎች፣ እመጫቶች፣ ነፍሰጡር የሆናችሁ፣ በመንግስት ሆስፒታሎች ህክምና ቦርድ የተረጋገጠ ልዩ ክትትል የሚሻ ህመም ያለባችሁ ተማሪዎች፣ ...) ማመልከቻችሁን እና ደጋፊ ሰነዶቻችሁን በቀጣዩ ሊንክ ብቻ መላክ አለባችሁ፦ https://student.ethernet.edu.et

Source: Tikvah