Get Mystery Box with random crypto!

#Update በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው ከ50 በመቶ በታች ያመጡ እና በ | Educate Ethiopia

#Update

በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው ከ50 በመቶ በታች ያመጡ እና በዩቨርሲቲዎች የቅበላ አቅም "ዕጩ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች" ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡበትን ነጥብ ከ10 እስከ 15 ቀናት ውስጥ ይፋ እንደሚያደርግ የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

"ዕጩ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች" ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ ተደርጎ ራሳቸውን የሚያበቃቸውን ትምህርት ተከታትለው በሚቀጥለው ዓመት የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች በመሆን ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ለማድረግ የትምህርት ሚኒስቴር እየሠራ እንደሚገኝ ሚኒስትር ድኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ለፋና ብሮድካስቲንግ ተናግረዋል፡፡

"ዕጩ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች" በዕጩነት ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡበትን ነጥብ በጥቂት ቀናት ለማሳወቅ እየተሠራ ነው ብለዋል።

ሌሎች በራሳቸው ከፍለው በግል ተቋማት የማጠናከሪያ ትምህርት ተከታትለው የሚሰጥ ፈተናን ካለፉ የመጀመሪያ ዓመት የሚሆኑበት ዕድል እንደሚፈጠርላቸውም ሚኒስትር ድኤታው ገልጸዋል፡፡