Get Mystery Box with random crypto!

የእንግሊዝኛ ቋንቋን ያለምንም የበይነ መረብ ክፍያ ለመማር የሚያስችል መማሪያ ይፋ ሆነ ------ | Educate Ethiopia

የእንግሊዝኛ ቋንቋን ያለምንም የበይነ መረብ ክፍያ ለመማር የሚያስችል መማሪያ ይፋ ሆነ
-------------------------------
የእንግሊዝኛ ቋንቋን ያለምንም የበይነ መረብ ክፍያ ለመማር የሚያስችል መማሪያ የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የኢትዮ-ቴሌ ኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬ ህይወት ታምሩ በተገኙበት ይፋ ሆኗል::

መማሪያው በትምህርት ሚኒስቴር የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የተዘጋጀ ሲሆን ከተማሪዎችና መምህራን በተጨማሪ ሁሉም የማህበረሰብ አካል ሊጠቀምበት እንደሚችል ተጠቁሟል::

የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ መተግበሪያው በትምህርት ቤቶች የሚሰጠውን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት የበለጠ በማጠናከር በመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ የተማሪዎችን የመረዳት አቅም ለመገንባት ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል።

ፕሮፌሰሩ ከዚሁ ጋር አያይዘው እንደገለጹት የሀገራችን የትምህርት ስርአት ከሰባተኛ ክፍል ጀምሮ የመማሪያና ማስተማሪያ ቋንቋ በአብዛኛው እንግሊዝኛ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በአግባቡ ለመረዳት የሚገጥማቸውን ችግር ለመቅረፍ እየተሰራ ነው ብለዋል::

ከተለያዩ ሀገራት በጎ ፈቃደኛ የእንግሊዘኛ መምህራንን እና የዲስፖራ አባላትን ወደ ሀገር ቤት በማስመጣት በት/ቤቶች ውስጥ ለማሰማራት ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን የጠቀሱት ፕሮፌሰር ብርሃኑ መተግበሪያው ይፋ መሆኑ ተጨማሪ አቅም ይፈጥራል ብለዋል:

http://Learn-english.moe.gov.et

ሙሉ ዜናው
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0Ku5booFse1fiuhoqoprTr9o7rQpCZZzvED9HeMr666bGZLSndtBEHgVUy2t4K6fjl&id=100064682287722

ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ