Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ የጋለሞ-ሞሉድ መንገድ ግንባታን ለማጠናቀቅ ተስማሙ ************** ( | ECWC/ኢኮሥኮ/

ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ የጋለሞ-ሞሉድ መንገድ ግንባታን ለማጠናቀቅ ተስማሙ
**************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ የሚያገናኘው ወሳኝ መንገድ ጋለሞ - ሞሉድ ግንባታን ለማጠናቀቅ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።
በጋለሞ እና ሞሉድ መካከል ያለው የ35 ኪሎ ሜትር መንገድ የተሽከርካሪዎችን ዝውውር ለማፋጠን ያስችላል።
ስምምነቱ የተደረሰው በመጋቢት ወር መጀመሪያ ላይ የኢትዮጵያ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዶክተር አለሙ ስሜ ጅቡቲን በመጎብኘት ከጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ ጋር ባደረጉት ስምምነት ነው።
ዶ/ር አለሙ ስሜ የስምምነቱን አፈጻጸም ለመከታተል ጂቡቲ ይገኛሉ።
ዶ/ር ዓለሙ ስሜ የተመራው ልዑክ በጉብኝታቸው ወቅት የመንገዱን ግንባታ ለማፋጠን ከጅቡቲ ወደቦችና ነፃ ዞኖች ባለስልጣን ፕሬዝዳንት ከአቶ አቡበከር ኦማር ሃዲ እና ከልኡካቸው ጋር ተወያይተዋል።
ስምምነቱ የጋለሞ - ሞሉድ 35 ኪሎ ሜትር መንገድ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቅ የሚያደርግ ሲሆን፥ ተገቢውን ክፍያም ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን እንዲከፈል ተስማምተዋል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን በኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ የሚመራው የልዑካን ቡድን ከመጋቢት 20 እስከ 23 ቀን 2020 ዓ.ም ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማድረግ ከጅቡቲ ጉምሩክ ባለስልጣን አቻዎቻቸው ጋር በመገናኘት የተለያዩ ጉምሩክ ነክ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸው ይታወሳል።
ከሶስት ቀናት ውይይት በኋላ የጉምሩክን ውጤታማነት ለማሻሻል የመፍትሄ ሃሳቦችን በማቅረብ ስምምነት ተፈራርመዋል።
በጋለሞ-ሞሉድ መንገድ ላይ የተደረሰው ስምምነት እና የጉምሩክ ጉዳዮችን አፈታት ጉዳይ ኢትዮጵያና ጅቡቲ ንግድና ትራንስፖርትን ለማሳደግ በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን ከኤምባሲው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።